Friday, September 2, 2016

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የቤት ውስጥ ተቃውሞ በታሰበለት ቀን ይካሄዳል።


በአዲስ አበባ የሚካሄደው የቤት ውስጥ ተቃውሞ በታሰበለት ቀን ይካሄዳል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ለማውገዝ የተዘጋጀው የቤት ውስጥ ተቃውሞ እሁድ ነሐሴ 29 የሚካሄድ ሲሆን ይህ ቀን ማለትም እሁድ ብዙም ስራ የሌለበት በመሆኑ በየቤታችን ብንቀመጥ የምናጣው ነገር አይኖርም ሆኖም የብዙ አለማቀፋዊ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ጭር ብላ ስትውል ትግላችን የብዙ ሚዲያዎችን ትኩረት ከመሳቡም በላይ ለሕዝባችን አጋርነታችንን የምናሳይበት ትልቅ አጋጣሚ ነውና አዲስ አበባ የምንገኝ በሙሉ የትግሉ አጋር እንሁን።
መልእክቱን ሼር በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ። የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ የሚዲያ ተቋማት በሙሉ መልእክቱን ለሁሉም በማዳረስ የህዝብ አለኝንታነታቹህን አሳዩን

No comments:

Post a Comment