Monday, September 26, 2016

በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል::

እንደተፈራው በደብረማርቆስ ደመራ ላይ ሕወሓት ብጥብጥ አስነስታ ብዙ ወጣቶችን አሰረች – ስነ ሥርዓቱ ተቋረጠ – ባህርዳር ተኩስ ይሰማል
(ዘ-ሐበሻ) በደብረማርቆስ ከተማ በተደረገ የደመራ በዓል ላይ የሕወሓት መንግስት እንደተፈራው ብጥብጥ አስነስቶ በርካታ ወጣቶችን ማሰሩ ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከስፍራው እንደዘገቡት ከሆነ በደብረማርቆስ ደመራ ላይ የሕወሓት መንግስት ሆን ብሎ ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ ወጣቶችን ዳመራ በጠበጡ በሚል አስሯል:: እንዲሁም በርካታ ወጣቶች እንደተቀጠቀጡም የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል::
እንደ ምንጮቻችን ገለጻ የሕወሓት መንግስት የአማራውን ወጣት ለትግል ተነሳሽነቱን ለማኮላሸት በዚህ የደመራ ስነ ሥነስርዓት ላይ ባዘጋጃቸው ሰዎች ሆን ብሎ እንዲበጠበጥ አድርጓል:: ቀደም ብሎ ሕወሓት ይህን በማደረግ ወጣቶችን ለማሰር እንዳቀደ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል:: ተኩሱ እየተሰማ ያለው በባህር ዳር ቀበሌ 13 መኮድ አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ እንደሚገኝም ታውቋል:: ዘ-ሐበሻ ተኩሱ ለምን እና እንዴት እንደተፈጠረ በማጣራት ላይ ናት::

No comments:

Post a Comment