Wednesday, September 21, 2016

በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ተከትሎ ለንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።


በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ተከትሎ ለንግድ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።
በጎንደር እና በባህር ዳር የተጠራውን የቤት ውስጥ መቀመጥ ኣድማ ከኣቅሙ በላይ የሆነበት የወያኔው ኣገዛዝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በሚል በየንግድ ድርጅቶች በተዘጎ በሮቻቸው ላይ ማስታወቂያ መለጠፉንና ድርጅቶን ካልከፈቱ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰምቷል።
የሕዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ በጉልበት ለመቀልበስ የሚሮጠው የወያኔ ኣገዛዝ ሕዝቡ ትእግስቱ ስላለቀ ስልጣኑን እንዲለቅ በተደጋጋሚ ኣድማዎች ተቃውሞውን እየገለጽ ይገኛል።የባህርዳርና የጎንደር ኣድማው ቀጥሎ ያለ ሲሆን የኣማራው ሕዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ሕወሓት ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ስልጣኑንም ለሕዝብ እንዲያስረክብ እንዲሁም የወልቃይት ምድርና ሕዝብ ማንነቱ ታውቆ በትግራይ ክልል የተነጠቀው መሬት እንዲመለስ በመታገል ላይ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment