Thursday, September 8, 2016

ዛሬ በቂሊንጦ በህይወት ያሉ የእስረኞች ዝርዝር ተለጠፈ


ዛሬ በቂሊንጦ በህይወት ያሉ የእስረኞች ዝርዝር ተለጠፈ 
– አሁን ከቂሊንጦ እስር ቤት አከባቢ ከሚገኙ ምንጮቼ መረጃ ማረጋገጥ እንደቻልኩት፤ እዛው ቂሊንጦ የቀሩ፣ ወደቃሊቲ፣ ሸዋሮቢትና ዝዋይ እስር ቤቶች እንዲዘዋወሩ የተደረጉ እስረኞች ስም ዝርዝር በቦርድ ላይ ተለጥፏል።
በስፍራው በርካታ ፖሊሶችና አድማ በታኝ ወታደሮች ኖረው ጥብቅ ቁጥጥር ቢኖርም ስም ዝርዝሩን ለጠያቂ ክፍት ሆኖ ማየት ይቻላል።
ማስማት እንደቻልኩት፣ በህይወት የሚገኙ እንጂ የሞቱ እስረኞች ስም ዝርዝር አልተለጠፈም። ይህም ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ለማወቅ ለጊዜው አዳጋች ያደርጋል።
የሟቾች ስም ካለተለጠፈ ደግሞ በየእስር ቤቱ እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት ዝም ዝርዝሮች ውስጥ ስሙ የታጣ እስረኛ በተዘዋዋሪ እንደሞተ መገመት ቀላል ይሆናል።እንግዲህ ዛሬ የሞቱ ሰዎችንና በህይወት ያሉትን እስረኞች ለማወቅ ዕድሉ ሰፊ ነው
Image may contain: text

No comments:

Post a Comment