Saturday, September 3, 2016

‹በሶሻል ሚዲያ በሚለቀቀው ፎቶአችን እንድንሸማቀቅ እያደረገን ነው ሲሉ የቆቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከድር ሙስጠፋ ገለፁ


‹‹በሶሻል ሚዲያ በሚለቀቀው ፎቶአችን እንድንሸማቀቅ እያደረገን ነው ሲሉ የቆቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከድር ሙስጠፋ ገለፁ
ያሬድ አማረ
*******************************************************
በሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ወረዳ በሀግሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በትላንትናው እለት ነሐሴ 27/2008 ዓ.ም በስሩ ከሚገኙ ከመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ጋር በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ከድር ሙስጣፋ ‹‹ በሶሻል ሚዲያ የሚለቀቀው ፎቶአችን አስደግፈው የሚሰሩ ዜናዎች እንድንሸማቀቅ እያደረገን ነው›› በማለት በግልፅ ስጋታቸውን ለተሰብሳቢው መናገራቸውን በስብሰባው ላይ ተካፋይ የነበሩ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
እንደ ምንጮቻችን ገለፃ በአሁኑ ወቅት በመላ ሃገሪቱ እየተካሄደ የሚገኘውን ህዝባዊ የአመፅ እንቅስቃሴ የልማት ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ችግር ሳይሆን የስልጣን ጥያቄ ነው ማለታቸው በመንግስት ሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ እንደፈጠረም ለመወቅ ተችሎዋል ፡፡ የቆቦ ወረዳ የካቢኔ አባላት መረጃዎች ለህዝብ ይፋ እየወጡ መምጣታቸው በተለይም በሶሻል ሚዲያው የሚለቀቁት ምስሎቻችን አስደግፈው የሚሰሩ ዜናዎች እንድንሸማቀቅ እያደረግን ከመሆኑም በላይ በቀጣይ እንቅስቃሴዎቻችን ላይ ጥላ እዲያጠላበት እያደረገን ነው ማለታቸውን ተክትሎ አስተዳዳሪው በትላንትናው እለት በውይይት መድረክ ላይ በይፋ ከመግለፃቸው ባሻገር በዚህ ሂደት ውስጥ ከተራው ነዋሪ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ መዋቅር ውስጥ መኖሩን እናውቃለን በማለት በውጪ ሆንው በወረዳው ቸግር እንዲፈጠር አደርግዋል ያሏቸውን አካላትም በመኮነን መግለፃቸውን ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል፡፡
Image may contain: 1 person , people smiling , sunglasses

No comments:

Post a Comment