Thursday, September 15, 2016

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊ ወያኔን ወነጀሉ


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ የድርጅቱ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኃላፊ ባደረጉት ንግግር የወያኔ አገዛዝ በዜጎቹ ላይ እየወሰደ ያለው አፈናና ግድያ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሰላማዊ መንገድ ተቃዋማቸውን በሚያሰሙ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ግድያና ጭፍጨፋ እንዲሁም እስራት መካሄዱ ፤ መዳረሻቸው የጠፋ ዜጎች በብዛት መኖራቸው፤ ህጻናትን ጨምሮ ዜጎች የሚደርስባቸው የጅምላ እስራት፤ በሲቪል ማህብረሰብ በነጻ እንዳይደራጅ መከልከሉ በሚድያ እና በተቃዋሚዎች ላይ ገደብ መኖሩ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በጣም አሳሳቢ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ነጻና ገለልተኛ የሆነ አካል ጉዳዩን እንዲመረምር የቀረበውን ጥያቄ የወያኔ አገዛዝ ውድቅ ያደረገው መሆኑን ተናግረው በአገዛዙ በኩል ግን የውጭ ኃይሎች ሴራ መሆኑን በመግለጽ በራሱ መንገድ ምርመራ እንደሚያካሄድ በመጥቀስ የተመድን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment