Monday, September 19, 2016

ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግስት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥


ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግስት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥
የአማራ ተጋድሎ ወጣቶችን በማሰርና በማሸማቀቅ ዓይቆምም፥
==================================
ወጣት ንግስት ይርጋ፥ አርብ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ ተነስታ፥ በታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ ወደ ሚገኘው ቤቷ ስታመራ መንገድ ላይ ታፍና ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ የማሰቃያ ቤት መወሰዷ ታውቋል።

ወጣት ንግስት ይርጋ ተፈራ፥ ሰሞኑን ጎንደር በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ ባደረገችው የማስተባበር ተሳትፎ በከተማው ታዋቂነትን ያተረፈች፥ ገና በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የምትገኝ፥ ምንም ወንጀል የሌለባት ወጣትና ፍትህ ፈላጊ ታዳጊ ዜጋ መሆኗ ነግሯል።

ወጣት ንግስት ወደ ትግሉ የገባችውና በሕዝብ ዓይን ጎልታ መታየት የጀመረችው፥ የወልቃይት ማንነት ኮሚቴዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ዓፍነው ለመውሰድ በመጡ የወያኔ ታጣቂዎችና በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመከላከል እርምጃ ምክንያት ጎንደር ላይ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ፥ ሰልፍ በመምራትና በማስተባበር ባደረገችው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነበር።

ይህች ወጣት ንግስት የአማራ ተጋድሎ በመባል የሚታወቀውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የተቀላቀለችው ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤት ጓደኛ ለመጠየቅ ሂዳ ባየችው የወጣት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ብዛትና የአማራ እስረኞች ስቃይ፥ በተለይም ከገጠሪቱ ጎንደር ባልሰሩት ወንጄል ታፍነው ተወስደው መዳረሻቸው ሳይታወቅ ለእረጅም ጊዜ ያለጠያቂ ሲሰቃዩ ላየቻቸው ወገኖቿ ጩኸትና የመከራ ድምጾች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ያጫወተቻቸው የትግል አጋሮቿ ይናገራሉ።
ትግሉ ይቀጥላል፥ ሕዝብ ያሸንፋል፥

No comments:

Post a Comment