Tuesday, September 27, 2016

በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤


በአብቁተ አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤
የባህር ዳር ከተማ ወጣት ተወካዩችን በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የመሰብሰቢያ አዳራሽ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ባወያየበት ሰዐት ከወጣቶች የተሰነዘረው አሰተያየት የክልሉን ፕሬዝዳንት አስለቀሰ፡፡

ከተሰበሰቡ ወጣቶች መካከል ‹‹እኛ ስለአማራ ሕዝብ ቆሰልን፤ ሞትን፤ ተገደልን፤ ደማችን አፈሰስን አንተስ ለእኛ ለአማሮች ምን አደረክልን? እኛ ጓደኞቻችንን ቀብረናል፡፡ የሞተው ግን ያንተም ወንድም ነው፡፡ በዚህ ስዓት ብር ሸለቆና ሰባታሚት በቶርቸር ስነ ልቦናቸው የሚሰለቡት የእኛ ወንድሞች ናቸው፤ አንተ መቼ ነው የምትደርስልን?›› በማለት በስሜት ሲናገር ገዱ አለቀሰ፡፡ እንባውን አዝረከረከ፡፡ ከማይግራፎኑ ድመፁ ጎልቶ ተሰማ፡፡

No comments:

Post a Comment