Saturday, September 24, 2016

“ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ/ የእባብ ልጅ እባብ” አቶ ጁነዲን ሳዶ ነበር ያሉት !!!


ከኢህአዴግ ጋር በትልቅ የስልጣን ኮርቻ የነበሩና ዛሬ እራሳቸውን ከፓርቲው ያራቁ ወደተቃውሞም የገቡ ሊደነቁ የሚገባቸወ ናቸው ።ቢሆንም ቅሉ ከመንግስት ጋር ተጣልቶ የሸሸ የድሮ ባለስልጣን ሁሉ እንደ ሀቀኛ መቁጠርና ማጀገን ግን ጅልነት ነው::

የአቶ ጁነዲን ሳዶን ለአብነት እንይ ከዚህ ቀጥሎ የማወራላችሁ በጊዜው እዚያው ሰብሰባ ላይ በአካል ከነበረና የአቶ ጁነዲን ሳዶ ስም ሲነሳ እጅጉን የሚያመው አንድ Õደኛየ ነው: ጊዜው በ1997 ዐም የምርጫ ወቅት ነበር:: አቶ ጁነዲን ሳዶ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆኑትን የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ ፖለቲካዊ ስብከት እያደረገ ነው በሰብሰባው የነፍጠኛው ስርዐት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል፣ የነፍጠኛ ስርዐቱ የኦሮሞ ህዝብ ጠላትነት ብዙ ተሰበከ ከዚያም ለጥቆ አሁን ያሉት የነፍጠኛ ልጆችም ከአባቶቻቸውእንደማይለዩ እንደውም ተደራጅተው የነፍጠኛውን ሰርዐት ለመመለስ እየጣሩ እንዳሉና ይሀንን መፍቀድ አንደሌለባችው ብዙ ተባለ::

በዚሁ ብዙ ሰው በስሜት ተናጠ: በመሀል አንድ ተማሪ ተነስቶ “ታድያ የዛሬ ዐመት የነበረን ነገር ካሁኑ ጋር እነዴት በቀጥታ ማገናኘት ይቻላል? እንዴት ያሁኑ የአማራ ተወላጆች ከዚያኛው ጋር በቀጥታ መገናኘት ተጠያቂም ማድረግ ይቻላል?” ብሎ ጠየቀ::
አቶ ጁነዲን ሳዶ የሰጡት መልስ እጅግ አሸማቃቂ ነበር ቃል በቃል “ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ/ የእባብ ልጅ እባብ” ነበር ያሉት::
እጅግ አደገኛና መሰሪ አገላለፅ ነበር ያስፈራል!

እንደነጁነዲን ሳዶ ዐይነቶች ጥላቻን የሚዘሩና ሌላ በርካታ በደል በህዝብ ላይ ያደረሱ ሰዎች ከመንግስት ጋር ተጣልተው መፅሐፍ ፅፈው ወይም በሌላ መልክ ተከስተው ይቅርታ ቢጠይቁ !እንደኔ ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም::

1 comment:

  1. 25 አመት ሙሉ ትውልድን የሚያጋጭ ታሪክ ሲፈጥር ኖሮ፣ የቂም ሐውልት ካቆመ በኋላ የአዞ እምባ ቢያነባ አይገባኝም። ደግሞም ይቅርታ የጠየቀው የእሮሞ ህዝቦችን ብቻ ነው። አሁንም ዘረኝነቱ ይንጸባረቃል። በየትኛውም አለም ያሉ ፖለቲከኞች ሲጸጸቱ ተመልሰው ፖለቲካ ውስጥ አያቦኩም። በዚያው ይሰናበታሉ። ( resign) ያደርጋሉ። ጁነዲን ግን ገና ያልጨረሰው ማተራመስ ያለ ይመስላል። የውስጥ አጀንዳው በአማራ ላይ ያነጣጠረ ነው። እስኪ ልብ በሉ አንድ ስለሰዎች መጨቆን እቆረቆራለሁ የሚል ያውም የተማረ ሰው, ስልጣን ከያዘ በኋላ ዲሞክራሲን ለማምጣት ይሰራል እንጁ እንዴት የዘር ፖለቲካ ያራግባል? ይልቅ መድረክ እየሰጡ ባያስገረሹበት ጥሩ ነው።

    ReplyDelete