Wednesday, September 7, 2016

ባህር ዳር ተቃውሞ እያሰሙ ነው።


ባህር ዳር ተቃውሞ እያሰሙ ነው።

በባህርዳር ያለፈውን ተቃውሞ ተከትሎ እስከ 5000 የሚደርሱ ከዘጠኝ አመት ታዳጊ ህፃን እስከ 80ዎቹ አባት እና እናት የታሰሩበት ባህር ዳር ዛሬ ማለዳውን በአባይ ማዶ ከዲዛይን እና ቁጥጥር አባ ማዶ መጋዝን የታሸጉ ንፁህ ዜጎችን ወደ ብር ሸለቆ ወያኔ ለመጫን ያደረገውን ጥረት ተከትሎ ነው፡፡
ህዛባዊ እሪታ እና እለቅሶ የአባይን ድልድይ ዘግቶት ያረፈደው በአሁኑ ስዓት ወጣቶች ከፊታቸው የተደቀነውን መሳሪያ ሳይፈሩ እናቶች የቀድሞው ክልል ም/ቤትን እየዞሩ ተቃውሞ እያሰሙ ነው። በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሐን ዜጎችን ወደ ብር ሸለቆ መንግስት ለመውሰድ እና በዚያም የማስቀየት እርምጃውን ለመቀጠል በማሰብ በምክር የሚለቃቸውንም እራሳቸውን በመላጨት ከዚህ በኃላ ዳግመኛ በህዝባዊ አመፅ ቢገኙ ሊረሸኑ እያሰፈረመ እየለቀቀቻው ነው፡፡
የከፍተኛ አመፅ አካል ናቸው ያላቸውን በቀን አንድ ዳቦ እና ሁለት ዳቦ በማቅረብ ፤ በርሃብ እዚያ እየበሉ፤ እየተፀዳዱ፤ እየተኙ ሞራላዊ ስብራት በማድረስ አመፁን ለማብረድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገው ነው፡፡

No comments:

Post a Comment