ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ ። እንደ ቀነኔሳ አይነት እና እንደ ሌሊሳ ፈይሳ አይነት ።
ይህንን አይነት ክፍፍል ካርል ጁንግ ከ psychological attitudes እና moral altitude የተገኘ ልዩነት ነው ይላል ።
ዋናው እና መሰመር ያለበት ጉዳይ ሰው ስለሮጠ ብቻ ጤነኛ ነው ማለት እንደማይቻል ነው ። እንደውም እኔ እስከማስታውሰው ፥ ለምን እና ለማን እንደሮጠ የማየቅ ሰው ካገኘህ በእርግጠኝነት እብድ ነው ። ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሮጥ ሰው ፖለቲካ እና ስፖርት ለየቅል ነው ካለ ፥ ሃገር መወከል ራሱ ፖለቲካ እንደሆነ የማያውቅ ነው ።
እንኳን ለሜዳሊያ የሚሮጥ ይቅርና ፥ ፖሊስ አባሮት የሚሮጠው እንኳ ነብሱን ወክሎ ነውና የሚሮጠው ሩጫው ፖለቲካ ነው !
ራስን በጣም ከመውደድ የተነሳ ስለ ሌሎች ሞት እምብዛም መሆን ፥ ከሰዋዊ ስሜት መነጠል ነው ። ይህ ደሞ በሽታ ነው ። ከሰው ተፈጥረህ ስለ ሌሎች ስቃይ በድን ከሆንክ ፥ ጉዳይህ አልተጠናም እንጂ አንተ የ Personality disorder ተጠቂ ነህ !
ሃኪሞች በአደጋ ምክንያት ህብለ ሰረሰሩ በመሰበሩ በድን የሆነን ሰው ጤንነቱ ላይ ለውጥ እንዳለ ለማወቅ በድን የሆነውን እካሉን እየቆነጠጡ « ይሰማኻል ወይ ? » ይሉታል ፥ በኤሌክትሪክ ሾክ አድርገው ሞርታር ኒዮሮኖቹን ሊያስነሱ ይሞክራሉ ፥ እያየህ ስትበድን
« ይታይሃል ወይ » ትባላለህ ፥ እየሰማህ ስትደነቁር ፥ « አሁን የምለው ይሰማኻል ወይ?» ተብለህ ትጠየቃለህ ። በህዝብ ሞት ላይ ስለ ግል ህይወት ስትል ስትደደብ « ይገባሃል ግን ያልከው » የሚል ጥያቄ ይመጣል !
« ይታይሃል ወይ » ትባላለህ ፥ እየሰማህ ስትደነቁር ፥ « አሁን የምለው ይሰማኻል ወይ?» ተብለህ ትጠየቃለህ ። በህዝብ ሞት ላይ ስለ ግል ህይወት ስትል ስትደደብ « ይገባሃል ግን ያልከው » የሚል ጥያቄ ይመጣል !
ጤነኛ ሆኖ ከማበድ ፥ እብድ ሆኖ ጤነኛ መሆን ይሻላል ! ይህንን ለመረዳት ግን በመጀመሪያ ጥሩ ጤነኛ መሆን ያስፈልጋል!
የነ ቀነኔሳ Personality disorder symptomatology ከምልክትነት ወደ ፅኑ በሽታነት የተሸጋገረው ግን እንዲሁ በዝምታ የሚያሻግር ፥ ድልድይ የሆነ ቻይ ህዝብ መሃል ስለሚኖሩ ነው ። ያ ባይሆን ቀነኔሳ በግል አውሮፕላን አይንቀሳቀስ ፥ ህዋ ላይ አይኖር ፥ በእንደ ኩሩቤል ወ ሱራፍል በ አክናፋት አይበር ። ህዝቡ ነው በሽታውን በ ትልቅነት ለውጦ ፥ ህመሙን በ አንቱነት አግዝፎ እንዲህ በአደባባይ እንዲያብድ ያደረገው! እንጂ እሱ እንዲህ እብደቱ ከቁጥጥሩ ውጭ ባልሆነ ! And so ነው ያለው ያ እብድ !
ቴዲሾ « ቀነኔሳ እንበሳ » ነበር ያለው ? ይኽ ምን አንበሳ ነው « ሀበሳ » እንጂ ! ጭቁን ሃብታም !
ኄኖክ የሺጥላ
No comments:
Post a Comment