የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ሰራተኞች ውይይታቸውን አቋረጡ፡፡
ስብሰባው በዝምታ አድማ በመመታቱ ምክንያት ነው እንዲቋረጥ የተገደደው ፡፡ ስብሰባው የሚመሩት አማራ ክልል ም/ሬዝዳንት እና የበአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን ተስብሳቢውን በየአቅጣጫው ችግራችን ስር የሰደደ ነው ለውጥ እናደርጋለን ከአባላት ውጭ ያሉትን ሁሉ እንሾማለን ፤ አባል እናጠራለን ቢሉም ሰሚ አጠው፤ ከግማሽ ቀን በላይ በተረገው የዝምታ አድማ ስብሰባው እና በቀረቡት ሰነዶች ላይ ሚፈለገው ውይይት ላይ ተናጋሪ በመታጣቱ ምክንያት ያለ ስበሰባው ኢህ,አዴግ ያለመውን ግብ ሳይመታ ተበትኗል፡፡
በአሁኑ ስዓት በመላው አማራ እና ኦሮምያ አካባቢ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የግጭት ምንጭ ይሆናሉ ተብሎ በመታሰቡ ኢህአዴግ ለሰራተኞች እና ለመምህራን ምግብ እና ተጨማሪ ወጭዎችን እየሸፈነ ለማወያየት ቢሞክርም ፤ በወሎ ዩኒቨርስቲ ፤ በባህር ዳር ፤ በደብረ ማርቆስ ፤ በደብረ ታቦር ያለው ሁኔታ ስጋት እንደጣለው አጠቃላይ የግምገማ ሰነዱ በግብረ መልስ በተቀመረው የውሎ ሪፖርት ላይ ተመልክቷል፡፡
በባለፉት ሃያ አምስት አመታት የነበሩ የመልካም አስተዳደር፣የክራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣የትምክህትና ጠባብነት አደጋዎች እንደዚሁም ሃይማኖትን ሽፋን የሚያደርገው አክራርነት ፈተናዎች አሁንም ቅርፃቸውን ቀይረው ወይም በሌላ ተተክተዉ ስላሉ ፈተናዎችን ለማለፍ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እዲያገዙኝ ሲል ቢጠይቅም የሚያግዘው አጧል፡፡
አመራሩ ሁሉም በኪራይ ሰብሳቢነት የተዘፈቀበት ስዓት በመሆኑ ይህም ዜጎች በመንግስት እምነት እንዳጡ እና መንግስት በጥልቅ እንደሚታደስ በመሪዎቹ በኩል ቢገልፅም ይህንን የሚቀበለው በማጣቱ በ2009 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ የአመፅ መነሃሪያ የሚሆኑ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ኢህአዴግ ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡
************************************/
በ2009 ዓ.ም በስነ ምግባርና ስነ ዜጋ ትምህርት አንድ ተጨማሪ ምዕራፍ ጨመረ፡፡
ምዕራፉ መቻቻል የሚል ይዘት ሲኖረው ፤ የስነ ዜጋ ስነ ምግባር ትመህርት ግብረ ገብነትን የማስተማር አቅመ የለው ተብሎ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሳልፎ እንደተገመገመ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው ብለው ያስተማሩ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ እና በምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኙ 13 መምህራን ከመምህርነት ሙያቸው መባረራቸው ትምህርት ሚንስቴር በከፍተኛ ትምህርት የውይይት ጉባኤ ገልፆል፡፡
ክራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት የትምህርት ተቋሞቻችን በስነ ምግባርና ስነ ዜጋ ትምህርታቸው ውስጥ ያልደከሙበትን ለመብላት የሚደረግ ጥረትና አስተሳሰብ ቀጣይ ትውልድ እንዲጠየፈው በማድረግ ሙስናንና ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚታገልና የማይሸከም ዜጋ ማፍራት ያለመ ቢሆንም ይህንን የማሳካት አቅም የለውም ሲሉ መምህራን በውይይታቸው ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment