Thursday, September 8, 2016

የሽምግልና እና ውይይት ጉዳዮችን አስመልክቶ ከ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ!


ድምፃችን ይሰማ

የሽምግልና እና ውይይት ጉዳዮችን አስመልክቶ ከ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ!
ረቡእ ጳጉሜ 2/2008

የመግለጫው የፒዲኤፍ ሊንክ፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል በጽሑፍ፡-
**************************
**************************
የሽምግልና እና ውይይት ጉዳዮችን አስመልክቶ ከ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ!
‹‹ሰላም ከማይገባው መንግስት ጋር ውይይት ይፈይዳልን!?››
ረቡእ ጳጉሜ 2/2008 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
ህዝበ ሙስሊሙ ከአምስት ዓመታት በፊት የመብትና የፃነት ጥያቄያዎችን ሲያነሳ መንግስት ምላሽ ይሰጠኛል የሚል ተስፋ ነበረው፡፡ በመሆኑም መፍትሄ እንዲያፈላልጉለት ወኪሎቹን መርጦ ወደ መንግስት ልኳል፡፡ የሕዝቡን አደራ በውክልና የተቀበለው ኮሚቴም በጠረጴዛ ዙሪያ በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር መፈትሔ ለማፈላለግ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በር አንኳኩቷል፡፡ ውይይቶችንም ከተለያዩ አካላት ጋር አድርጓል፡፡ በተለይም በየካቲት 26/2004 ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጋር ካካሄደው ውይይት በኋላ በርካቶች ‹‹ከኢህአዴግ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ለህዝቡ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ይገኛል›› የሚለው ተስፋቸው ላይ ጥርጣሬ ማሳደር ጀመሩ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተለያዩ የመንግስት አካላት ቀደም ሲል የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች ህጋዊነት በመሰከሩበት አንደበታቸው መልሰው ጥያቄዎቹን ሆነ ብለው እያዛቡ ማቅረብና የህዝቡን ወኪሎች መወንጀል በመጀመራቸው ነበር፡፡ ነፃነቱን የጠየቀውን ህዝብ እና ወኪሎቹን በአክራሪነትና በሽብርተኝነት ፈርጀው ‹‹በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ መንግስት ለማቋቋም የሚያሴሩ ናቸው›› ብለው እስከመወንጀል ደረሱ፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነም እንኳ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በትዕግስት የተሰነዘሩባቸውን የሐሰት ውንጀላዎች በግልፅ ከማስተባበልና እውነታውን ከማሳወቅ በተጨማሪ የአገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች እውነቱን ተረድተው በሰለጠነና በሰላማዊ የውይይት ሂደት ለህዝቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ ባለመታከት ጥረታቸውን ቀጠሉ፡፡ ሆኖም መንግስት በሰላማዊ መንገድ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ፋንታ ህዝቡ በመላ አገሪቱ ያካሂዳቸው የነበሩትን የሰደቃና የአንድነት ዝግጅቶችን በኃይል አደናቀፈ፡፡ ቀጥሎም ሐምሌ 6/2004 ሌሊት በአወሊያ መስጊድ ለሰደቃ ዝግጅት በተገኙ ምዕመናን ላይ ጥቃት ሰንዝሮ በርካቶችን አቁስሎ የአወሊያ ተቋምን ንብረት አወደመ፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችንም አሰረ፡፡ የኃይል እርምጃው ቀጥሎ ከሐምሌ 12/2004 ጀምሮ ባሉት ቀናት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትንና የሂደቱ ደጋፊ እና ተባባሪ የሆኑትን ሙስሊሞች ‹‹የሽብርተኝነት ወንጀል ፈፅመዋል›› በሚል አሰረ፡፡ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለወራት አስከፊ ስቃይና ድብደባ አደረሰባቸው፡፡
ጉዳዩ ያሳሰባቸው የአገር ሸማግሌዎች መንግስት ጋር በመቅረብ ጉዳዩ በሰላማዊ ሂደት እንዲፈታና ታሳሪዎቹም እንዲለቀቁ ወተወቱ፡፡ መንግስትም ለቀረበለት ሰላማዊ ጥሪ እምቢተኝነቱን በመግለፅ ታሳሪዎቹን ‹‹በሽብርተኝነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል የሐሰት ክስ መስርቶ ጥቅምት 19/2005 ወደ ቃሊቲ አወረዳቸው፡፡ በዚያም በእነሱና በቤተሰቦቻቸው ላይ የተለያዩ ወከባዎችንና ትንኮሳዎችን አደረሰባቸው፡፡ የፍርድ ሂደቱም የዳኞችን ካባ በደረቡ ካድሬዎች በዝግ እንዲካሄድ አስወሰነ፡፡ በዝግ ችሎት በሐሰት እንዲመሰክሩ ያሰለጠናቸውን ምልምል ምስክሮችን በማቅረብም አስመስከረ፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ በጥያቄዎቹ መቀልበስና ወኪሎቹ ተወንጅለው በመታሰራቸው ቁጣውን በማሰማቱ በመላ አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ለድብደባ፣ ለእስራትና ለስደት ተዳረጉ፡፡ ከፊሎችም የመንግስት ‹‹የፀጥታ ኃይላት›› ባደረሱባቸው ጥቃት ህይወታቸውን አጡ፡፡ በርካቶችም በሐሰት ተከስሰው እስራት ተፈረደባቸው፡፡ ጥቂቶች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ቢፈቱም በርካቶች ግን ዛሬም ድረስ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡
መንግስት ለሰላማዊ ሂደት ፈቃደኛ ባለመሆን የእብሪትና የአምባገነንነት ጎዳናውን በቀጠለበት ጊዜም እንኳ የተለያዩ ወገኖች ‹‹የመንግስትን ልብ ማራራት ብንችልና ጉዳዩ በሰላማዊ ውይይት ቢፈታ›› በሚል ተስፋ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት ሽማግሌዎች በተጨማሪ የዳያስፖራ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት የራሳቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ ልዑካኖቻቸውን ወደ አገር ቤት በመላክም የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናትን አነጋግረዋል፡፡ በ2006 አጋማሽ ላይ ከአምባሳደር ግርማ ብሩ ጋር በመሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመገኘት ታሳሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በዚሁ ጊዜ ለታሳሪዎቹ ‹‹ደህንነታችሁን ለማየት ነው የመጣነው›› ከማለት ውጪ የገለፁላቸው ነገር አልነበረም፡፡ ታሳሪዎቹን በእስር ላይ እያሉ የጎበኟቸው ብቸኛው የመንግስት አካል አምባሳደር ግርማ ብሩ ብቻ ሲሆኑ ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ በሽምግልና ጉዳይ ታሳሪዎችን ያነጋገራቸው አንድም አካል የለም፡፡ የዳያስፖራ ልዑካንም ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ያደረጉትን ውይይት ይፋ አላደረጉም፡፡
በርካቶች የሙስሊም ዳያስፖራ ልዑካንን ወደ አገር ቤት መምጣትና የአገር ቤት የሽማግሌዎችን እንቅስቃሴ ጭምጭምታ በመስማት የተጀመረ ድርድር (ሽምግልና) እንዳለ ማሰብ ጀመሩ፡፡ ኢህአዴግም ይህንን ለጊዜ መግዣና ህዝቡን ለማደናገር ተጠቀመበት፡፡ ህዝቡ ከተለያዩ መስጊዶች ‹‹ከፍተኛ ተቃውሞ ያደርጋል›› ብሎ በሚሰጋበት ሰሞን ሸማግሌዎቹ ጋር ንግግር ይጀምርና ሂደቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ መልሶ ችላ ይላቸው ነበር፡፡ በመሆኑም በርካቶች ከኢህአዴግ ባህሪና ማንነት በተጨማሪ በይፋም ሆነ በስውር በሚያደርጋቸው ሴራዎች ምክንያት ለጥያቄዎቹ ተገቢ ምላሽ ይገኛል ብለው ለማመን ተቸግረው ነበር፡፡ ጥቂቶች ቢሆኑም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዑለሞች፣ አዛውንቶች፣ ምሁራንና ባለሀብቶችን ያቀፉት ደግሞ የሽምግልና ሂደቱ መቀጠል እንዳለበት በማመን ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡ በመሆኑም በህዝቡ መካከል በዚሁ የሀሳብ ልዩነት የተነሳ ክፍፍል እንዳይፈጠር ሲባል ብዙሃኑ ‹‹በሽምግልና ሂደት መፍትሄ ለማምጣት እንሞክራለን›› የሚሉትን ከመቃወም ተቆጥበው ትግሉ የሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ጥረታቸውን ቀጠሉ፡፡ በሸምግልናና በድርድር መፍትሔ እናመጣለን ያሉትም የራሳቸውን ጥረት ቀጠሉ፡፡
በሽምግልና ችግሩን እንፈታለን ያሉት ወገኖች ጥያቄዎችን በመያዝ በየተራ የአገሪቱን ከፍተኛ አመራሮችን ጎበኙ፡፡ በሂደታቸውም ካናገሯቸው መካከል አቶ አባይ ወልዱ፣ አቶ አቦይ ስብሐት፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ አቶ ደመቀ መኮነን፣ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ፀጋዬ በርሄ እና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሚገኙበት ይነገራል፡፡ ሁሉም ባለስልጣናት ሽማግሌዎቹን ሲያናግሩ በጥቅሉ ኢህአዴግ ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር መጋጨቱ ስህተት እንደነበርና ለችግሩ መፍትሄ መስጠት እንደሚፈልግ፣ ታሳሪዎቹ በሽብርተኝነት ቢከሰሱም የሽብር ወንጀል እንዳልፈፀሙ በመናገር የሽማግሌዎችን ልብ ለማግኘት እንደጣሩ ይነገራል፡፡ በተለይም ሐምሌ 15/2006 ሽማግሌዎቹ ከአቶ ኃይለማርየም ደሳለኝ ጋር አምስት ሰዓታትን የፈጀ

No comments:

Post a Comment