Tuesday, September 6, 2016

“አንድ ኢትዮጵያ የሚል መንግስት ከመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ ይበላላል” – በአውስትራሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ባለስልጣናት በየቀኑ እውቀታቸውን የሚያስገምት ቃለምልልስ በመስጠት ላይ ናቸው:: ከዚህ ቀደም የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አማራውን እና ኦሮሞውን እሳትና ጭድ ሲል ነበር:: ዛሬ ደግሞ በአውስትራሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም ኢሕ አዴግ ወርዶ አንድ ኢትዮጵያ የሚል መንግስት ከመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበላላል አለች:: የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ ሚስት የሆነችው ትርፉ በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ወሬ ከነስዬ አብርሃ እየለቀመች ለነመለስ ታመላልስ ነበር እየተባለች በሕወሓት ካድሬዎች ትታማ ነበር::ለዚህም ውለታዋ መለስ ሹመት ሰጥቷት ነበር:: የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የነበረችው የዛሬዋ አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ተገምግማ የነበረ ቢሆንም ሳትከሰስ ወደ አውስትራሊያ እንደሄደች ይነገራል:: ስለወልቃይት; ኮ/ል ደመቀ; ጃዋር መሐመድና ታማኝ በየነ አሳፋሪ ነገር ተናግራለች::

No comments:

Post a Comment