Thursday, September 22, 2016

ሻንበል ከበደ አስረስ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ከ2ሺህ ተሰብሳቢ ድምፁን አስከብሮ በልዩነት የወጣ ብቸኛ የብአዴን አመራር


Image may contain: 1 person , suit
ሻንበል ከበደ አስረስ ተሰብሳቢውንም ሰብሳቢውንም ያቁነጠነጠ ጀግና
ሻንበል ከበደ አስረስ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ከ2ሺህ ተሰብሳቢ ድምፁን አስከብሮ በልዩነት የወጣ ብቸኛ የብአዴን አመራር
ይህ ግለሰብ ታሪኩም እንደዛሬው ገድሉ የሚያስደምም ነው አሉ። ተሰብሳቢውንም ሰብሳቢውንም ያቁነጠነጠ ጀግና።
ብአዴን ያዥጎደጎደውን የአንድ አመት የስልጠና ማንዋል የሚመስል የአቋም መግለጫ አልቀበልም በማለት ድምፄን በልዩነት መዝግቡልኝ ብሎ አማራዊ ክብሩን ያስጠበቀ ወንድ።
አረንዛው ዳሞቴ የህወሃትን የበላይነት በማስረጃ የሞገተ፣የትግራይን እና የአማራን የኢኮኖሚና ፖለቲካ እንዲሁም ማህበራዊ ዘርፍ የእድገት ልዩነት በራሳቸው ሪፖርት መረጃን እየተነተነ ሰብሳቢዎቹን ምላሽ ያሳጣ እውነተኛ የህዝብ ልጅ ነው።
በተለይም በመንገድልማት፣ በኮንስትራክሽን፣ በቴሌ፣በ ደህንነት፣በመከላከያ ፣በኢኮኖሚው ዘርፍ…..የህወሃትን በዝባዥ የበላይነት በደንብ ያሳየ ነው።ይህ ሰው ልበ ሙሉና አንደበተ ርቱዕ ነው።ወልቃይት ደም ታፋስሳለች ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ አማራ ትመለስ በማለት ቀጭን ትዕዛዝ መሰል አስተያየቱን የሰነዘረ ነው።
.ይህንን ሁሉ ከተናገረ በኋላ አሽከሩ ብአዴን የህወሃት የበላይነት አለመኖሩን፣የአማራ ተጋድሎ የፀረ ሰላምና ትምክህቶች ነው….ብሎ ሲያነበንብ ሻንበላ ሆየ እኔ የለውበትም ከዚህ መግለጫ ብሎ በአቋሙ ፀና ።

No comments:

Post a Comment