
በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በእስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት።
ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ መስከረም 12 2009 ዓ.ም በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም ብሎ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበታል። ፍ/ቤቱ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮውን በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ሰጥቷል።
ስንታየሁ ቸኮል፣ የታሰረበት ክፍል ውስጥ እንዲፀዳዳ እየተደረገ እንዳለ ለፍ/ቤቱ አቤቱታውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል።
ስንታየሁ ቸኮል ከነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment