አይ ወያኔ!
ነብሰ ገዳዩ ወያኔ ሸዋ ላይ ግብዓተ መሬቱ እንደሚፈጸም ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ምንም ዓይነት የተሰበሰበ ሕዝብ እንዳይኖር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ሆኖም የውሸትና የቅጥፈት አባት ነውና እንደለመደበት አዲስ አበባ ውስጥ መሰብሰብ ይቻላል የሚል ርካሽ ፕሮፓጋንዳውን ለማሰራጨት፣ ትናንትና መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የደመራ በዓልን ለማክበር በተሰበሰበው ኦርቶዶክሳዊ መሃል በሺሕዎች የሚቆጠር አጋዚና የሲቪል ልብስ የለበሱ ሰላዮችን መድቦ ሲያበቃ፣ ‹‹ደመራው በደመቀና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል›› የሚል ቱልቱላውን ሲነፋ ተስተውሏል፡፡ ወያኔ ማለት ይህ ነው! ውሸት፣ ቅጥፈት! ክህደት! አፈና! ግድያ!
ትናንትና ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ የአዲስ አበባ ሕዝብ በየቦታው ሲፈተሽ ውሏል፡፡ አጋዚ ሁሉንም መንገዶች ጠርቅሞ በመዝጋቱ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ ችግር የነበረ ሲሆን፣ ሕዝቡ በተለይም ሥራ ላይ የዋለው ሲቪል ሰርቫንት በእግሩ እንዲኳትን ተገዷል፡፡ ወያኔ ተርበትብቷል! በየቤተክርስቲያኑ እየተዘዋወረ ዘማሪያኑንን ሲያስጠነቅቅ እንደነበርም ታውቋል፡፡
ወሮበላው ወያኔ አዲስ አበባ ላይ ምንም ዓይነት ነገር እንዲነሳ አይፈልግም፡፡ ሆኖም የአዲስ አበባ ሕዝብ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መነሳቱና የወያኔን ግብዓተ መሬት መፈጸሙ አይቀርም!!! የአዲስ አበባ ሕዝብ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጊዜያት በተናጠል እየተነሳ ተመትቷል፡፡ አሁን ግን ብቻውን አይደለም!! የአማራና የኦሮሚያ ክልል ሰፊ ሕዝብ አለለት!
በመሠረቱ አዲስ አበባ ውስጥ ወያኔን ለማንበርከክ ቀላል ነው! ጀግኖቹ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተከተሉትን ዝርዝርና የማያቋርጥ የትግል ስትራቴጂ መጠቀም፣ የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ እየተጠቀመባቸው ያሉ የትግል ስታራቴጂዎችን ከአዲስ አበባ ሁኔታ አንጻር አስተካክሎ መጠቀም፣ ስኬታማውን የቱኒዚያ ሕዝብ የአመጽ ስትራቴጂ ከአዲስ አበባ አንጻር ቃኝቶና ሌሎችን ዘዴዎች ጨምሮ መጠቀም ወዘተ. ይቻላል፡፡ ይህን ሁሉ በቅርቡ የምናየው ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአማራና ኦሮሞ ሕዝቦች የበለጠ እንደሆነ እንጂ ያነሰ አልተጨቆነም፡፡ ይህ ሕዝብ በ1997 ዓ.ም. ወያኔን አንቅሮ እንደተፋውና ከዚያን ጊዜ ወዲህ በለየለት አፈና ውስጥ የሚኖር ሕዝብ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ብዙሃኑ አዲስ አበቤ ወያኔ እንዲቀበርና በላዩ ላይ ሙጃ እንዲበቅልበት ይፈልጋል፡፡ 2009 ብዙ ያሳየናል!!!!