Monday, February 6, 2017

ጎግል የአመቱ የዓለማችን ውድ ብራንድ ሆኗል


 

ብራንድ ፋይናንስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው የ2016 እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የዓለማችን ታዋቂ የንግድ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ጎግል በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡

ተቋሙ በ500 የዓለማችን ታዋቂ የንግድ ምልክቶች ዙሪያ የሰራውን ጥናት ጠቅሶ ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው፣ ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 የገበያ ዋጋውን በ24 በመቶ በማሳደግ፣ 109.5 ቢሊዮን ዶላር በማድረስ ቀዳሚነቱን ይዟል፡፡ ጎግል በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት 2016 የአለማችን እጅግ ውድ ያለው የንግድ ምልክት ሊሆን የበቃው፣ በአመቱ ያስመዘገበው የማስታወቂያ ገቢ በማደጉ ምክንያት ነው ያለው ዘገባው፤ የኩባንያው የማስታወቂያ ገቢ በዓመቱ የ20 በመቶ እድገት ማሳየቱንም አስታውቋል፡፡

ለአምስት ተከታታይ አመታት የአለማችን ቁጥር አንድ ውድ የንግድ ምልክት ሆኖ የዘለቀው አፕል በበኩሉ፣ በ2015 የነበረው 145.9 ቢሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ በአመቱ የ27 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ ወደ 107.1 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ በማለቱ ወደ ሁለተኛ ደረጃ የወረደ ሲሆን፣ ታዋቂው አማዞን በ106.4 ሚሊዮን ዶላር ሶስተኛ ደረጃን መያዙ ተነግሯል፡፡ ኤቲ ኤንድ ቲ በ87 ሚሊዮን ዶላር አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ታዋቂው ማይክሮሶፍት ኩባንያ በ76.3 ሚሊዮን ዶላር አምስተኛ ደረጃ መያዙን ዘገባው ገልጧል፡፡

No comments:

Post a Comment