BBN News | በአማራ ክልል ክረምት ላይ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወጣቶች፣ በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አቀረቡ፡፡ በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ የሚገኙ ተከሳሾች ‹‹አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ ሽብርተኛ ቡድን ተልእኮ በመቀበል እና የሽብር ቡድኑ አባል በመሆን በአማራ ክልል ውስጥ ከ2008 መጨረሻ እስከ 2009 መጀመሪያ ከ200 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረግ›› የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በትላንቱ የፍርድ ቤት ቀጠሮአቸው የሁሉም ተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ ለችሎት በፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለአቃቤ ህግም የመቃወሚያው ቅጂ እንዲደርሰው መደረጉ ተጠቁሟል፡፡
‹‹የአማራ ህዝብ አሸባሪ አይደለም፡፡›› የሚል ቲሸርት ለብሳ በጎንደሩ ተቃውሞ ላይ የተስተዋለችው ወጣት ንግስት ይርጋን ጨምሮ ሌሎች ስድትስት ሰዎች የሽብርተኝነት ክስ እደተመሰረተባው ይታወቃል፡፡ ወጣቶቹ በዓቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው፣ በ1996 የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32[1] (ሀ) እና (ለ)፣ አንቀፅ 38 እና በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3 (4) እና (6) ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል ተብሎ ነው፡፡
ተከሳሾች እጃቸው ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ያለምንም ክስ ለአራት ወራት የቆዩ ሲሆን፣ ከዚያም ከሶስት ሳምንት በፊት የሽብርተኝነት ክሱ ሊመሰረትባቸው ችሏል፡፡ ተከሳሾቹ በተመሰረተባቸው ክስ ላይ ያቀረቡትን ተቃውሞ ተከትሎ ዓቃቤ ህግ በቀጣይ ቀጠሮ አስተያየቱን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ በዚህም መሰረት ቀጣዩ ቀጠሮ የካቲት 7 ቀን 2009 እንዲሆን ተደርጓል፡፡

No comments:
Post a Comment