Friday, April 15, 2016

የህወሓት በቀል በመቐለ ህዝብ – ከአምዶም ገብረሥላሴ

 


mekele
ባለፈው ወር ከ2500 በላይ የባጃጅ ሹፌር ወጣቶች ለ4 ተከታታይ ቀኖች የስራ ማቆም ኣድማ መትው እንደነበር ይታወቃል።
ህወሓት የባለ ባጃጆቹ ኣድማ ከፍተኛ ድንጋጤና “ተደፈርኩ” የሚል የእብሪት ስሜት የጫረበት ከመሆኑም በላይ የመቐለ ህዝብ ለኣድማ መቺ ወጣት ልጆቹ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጉ ቂም እንዲቋጥርበት ምክንያት ሁነዋል።
ህዝቡ ለወጣቶች የስራ ማቆም ኣድማ የሰጠው የሞራል ድጋፍ ያበሳጨው የመቐለ ኣስተዳደር የህዝቡን የሚበቀልበትና የሚቀጣበት ኣዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ መመርያ በማውጣት በላዩ ላይ ጭኖበታል።
ኣዲሱ የበቀል ታሪፍ ከ35 ሳንቲም እስከ 1 ብር ከ45 ሳንቲም ጭማሪ ኣሳይተዋል።
* በመቐለ የነዳጅ ዋጋ የቀነሰ ቢሆንም የመቐለ መስተዳድር ሓላፊዎች ህዝቡ ለባጃጁ ኣድማ የሰጠው ታላቅ ድጋፍ ምክንያት ንዴት ስለጨመሩ የበቀል ታሪፉ በህዝቡ ላይ እንዲጫን ተደርጓል።
ኣዲሱ የበቀል ታሪፍ በምስሉ እንደምትመለከቱት በህዝቡ ላይ ተጭነዋል።
“ወደ ህዝብ መተኮስ የጀመረ ውድቀቱን ኣፋጠነ” ሜ.ጀ. ሓየሎም
ነፃነትና ኣብ ኢድና እያ…!

  • ይህን ጽሁፍ አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ በፌስቡክ ገጹ ያስተላለፈው ነው

No comments:

Post a Comment