የአሜሪካ ሴናተሮች “ኢትዮጵያ ውስጥ አለ” ያሉትን አፈና አወገዙ – VOA

የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።
የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የገባውን የደኅንነት ውል መልሶ እንዲፈትሽ ይጠይቃል።
የሴናተሮቹ የውሣኔ ሃሣብ መግለጫ ሰነድ ረቂቅ (pdf) አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ የኃይል እርምጃዎችን እንዲያቆምና አጥፊዎች እንዲጠየቁ ያሳስባል።
No comments:
Post a Comment