Add caption |
የልዑል ዓለሜ ዘገባ
ደቡብ አፍሪካ ጆሓንስበርግ የሚገኘዉ የመድሓኒያለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤና አስተዳደሩ ወዳልተፈለገ መጠቃቃት እየሀዱ ይገኛሉ ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጉዳዩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየወሰደዉ ሲሆን የትግራይ ተወላጆችን በመጠቀም አንድ ሌላ ግሩፕ እንዲፈጠር እያደረገ ነዉ 17 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸዉ በፖሊስ እየታደኑ ሲሆን 3 ግለሰቦች….
1 ሔኖክ ገ/ሚካኤል
2. ታምሬ ተምትሜ
3. አቶ ኤፍሬም
በጆሓንስበርግ ሴንትራል ፖሊስ ጣቢያ (Johannesburg central police station ) በትናንትናዉ እለት በቁጥጥር ስር ሲዉሉ ሁለት ማንነታቸዉን ለመጥቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች ከተላኩባቸዉ ዘራፊዎች የግድያ ሙከራ አምልጠዋል በኢትዮጵያ የሚገኘዉ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ ሉቃስ የአጎት ልጅ እና የወያኔ ብሔራዊ መረጃ ባልደረባ የሆኑት አባ ጾመ ልሳን ሰበካ ጉባኤዎችን ምድረ ፌስታል ሻጭ ሁሉ ይህ መነኩሴ የሚገድል ህዝብ ነዉ አዉቃለዉ በማለት የተሳደቡበት የድምጽ መረጃ እጃችን የገባ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንባሲ አንባሳደር በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያኑን እያመሱ ያሉት ግንቦት 7ቶች ናቸዉ በማለት ወንጅለዋል።
አባ ጾመ ልሳንና የኢትዮጵያ ኢንባሲ በመተባበር ቤተ ክርስቲያኗን መሪ አልባ ያደረጓት ሲሆን በጆሐንስበርግ የሚኖረዉን መሐበረሰብ በሰፍርና በዘር እየለዩ በመጥራት እያባሉትና እያጋጩት ይገኛሉ።
አብዛኛዉን ሕዝበ ክርስቲያን ይህ ሁኔታ እጅግ ያሳዘነዉ ከመሆኑም በላይ በገዛ ገንዘባችን እኛዉ በለግሰዉ እንደዚህ የሚባሉ ከሆነ ምን ልንሰራ እንሄዳለን በማለት ቅሬታቸዉን የገለጹ ሲሆን እለት በእለት እየተፈጠረ የሚገኘዉን ይህን አሳሳቢ ጉዳይ የሚያበርድ አባት ወይም ሽማግሌ በመጥፋቱ ምክንያት ጉዳዩ ወዳልተፈለገ መጤፋፋት ኢያመራ ይገኛል
No comments:
Post a Comment