Tuesday, April 19, 2016

ከመቀሌ የመጣ ከባድ መኪና እና ወደ አላማጣ የሚጓዝ ሚኒባስ ተጋጭተው የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 

(ዘ-ሐበሻ) በየቀኑ መልካም ዜና የማይሰማባት ሃገር እየሆነች በመጣችው ዛሬም ከባድ አደጋ ተከስቷል:: በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ያለቁት ወገኖቻችን ሃዘን ሳይቆርጥልን ዛሬ ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ዜና ተከስቷል:;
የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ዛሬ በሰሜን ወሎ በቆቦ ከተማ እጅግ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ደርሷል:: አደጋው የተከሰተው በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 ሰዓት ሲሆን የአደጋው መነሻም የሁለት መኪኖች ግጭት ነው::
የአይን እማኞች እንደሚናገሩት ከመቀሌ ከተማ ሸቀጣ ሸቀጥ የጫነ ከባድ መኪና ከነተሳቢው ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረና ከቆቦ ወደ አላማጣ 16 ተሳፋሪዎችን ጭኖ የሚሄድ በተለምዶ አባዱላ የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ቆቦ ከተማ ላይ ተጋጭተው እስካሁን የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል::
በዚህ መኪና አደጋ እግረኞች እና በሳይክል የሚጓዙ ሰዎችም ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል:: ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን::

1 comment:

  1. I am regular visitor, how are you everybody? This article posted at this web site is actually pleasant. rentalmobil bogor

    ReplyDelete