(ዘ-ሐበሻ) የስመጥሩው አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ሊካሄድ መሆኑ ተሰማ:: ከላስ ቬጋስ ከተማ ይጀመራል የተባለው የኤፍሬም የሙዚቃ ኮንሰርት ሜይ 21 በሚኒሶታ እንደሚካሄድም ታውቋል::
የላስቬጋስ ኮንሰርት ሜይ 10 እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ይፋ ያደረጉ ሲሆን በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ የኤፍሬምን የሙዚቃ ኮንሰርት የሚያዘጋጁት ዘ-ሐበሻ; ሶል ዲዛይን እና ፕሮሞሽን እንዲሁም ራስ ላውንጅ ፕሮሞሽን እንዳስታወቁት ሜይ 21 በሴንት ፖል ዳንሰርስ ስቱዲዮ ይካሄዳል:: አብሮትም አቢሲኒያ ባንድ ወደ ሚኒሶታ ይመጣል::
ኤፍሬም በሲያትል; በዋሽንግተን ዲሲ; በአትላንታ እና በተለያዩ ከተሞችም በዚህ የበጋ ወራት ኮንሰርቶቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል::
ኤፍሬም የቀድሞው ሥራዎቹን እንደአዲስ ከሮሃ ባንድ ጋር በመሆን እንደአዲስ ካወጣ በኋላ በተለያዩ ስቴቶች እየዞረ ኮንሰርቱን ሲያቀርብ የመጀመሪያው ይሆናል:: በተለይ ሚኒሶታ ኤፍሬም ለመጨረሻ ጊዜ የመጣው ከ9 ዓመት በፊት በመሆኑ አድናቂዎቹ በጉጉት ይጠብቁታል
No comments:
Post a Comment