አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ኤፕሪል 14 ቀን 2016 በዩቱብ ያሰራጩት ቪዲዮhttps://www.youtube.com/watch?v=AV-Twe0a9jM የሚያሳየው በጥቅሉ መልዕክቱ አንድ ነው። ይሄውም:- የናሽቪሉን ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን መነሻ አድረገው ያው የተለመደዉን የካድሬነት መልክታቸዉን ለማስተለልፍ ነው። ‘እስካሁን ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ ያልተጠቃለላችሁ አብያተ ክርስቲያናት እድሉ ሳያመልጣችሁ ቶሎ ኑ’ ለማለት ነው። የአዲስ አበባው ሲኖዶስና ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ይህን አይነቱን ጥሪ ማስተላለፍ እዉነት ለሰማያዊው መንግስት ከሚሰራ አባት የሚጠበቅ ነውን? አባ መላኩ ፍርድ ቤት ቀርበው ጠበቃው ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። ጠበቃዉም ከመልሳቸው ያገኘውን ተጨባጭ መረጃ ይዞ የቤተክርስቲያኑን ምዕመናን ለመከፋፈልና ለማበጣበጥ በጣልቃ ገብነት የተጫወቱት ሚና የህግ ጭብጥ እያሲያዘው ስለሆነ አይቸኩሉ፣ ይደረስበታል እንላለን።
አባ መላኩን ህዝበ ክርስቲያኑ ለረጅም ጊዜ ጥሩ አድርጎ ያውቃቸዋል። በተለይም አቋም በመለዋወጥ አንዴ ከዚሂ አንዴ ደግሞ ከዚያ ሲሉ ከሰማያዊው መንግስት ይልቅ ከምድራዊዉ መንግስት ጥቅም ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ጵጵስና ነው ብለው ስላመኑ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት ባልጠበቀ መንገድ ከገቡት የዘመኑ ጳጳሳት አንዱ ናቸው። ያሁኑ ደፋ ቀና ደግሞ “ይህን ያህል አብያተ ክርስቲያናት ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ ስላመጡ አጋጣሚው ከተገኘ የፓትሪያርክነት ስልጣን በታሳቢነት” እንዲያዝላቸው ፈልገው እንደሆነ እናውቃለን። አዎ፣ የእርስዎ ቢጤ አባቶች በቤተክርስቲያናችን፣ በገዳማቱ በምዕመናኑና ለእውነት በቆሙ አባቶች ላይ በየጊዜው በመንግስት የሚሰነዘረዉን ጥቃት ሰምቶ እንዳልሰማ፣ አይቶም እንዳላየ ቸል በማለት በአቋራጭ ለሹመትና ለሃብት በቅታችኋል። በዚህም ከሰማያዊው መንግስት ይልቅ ለምድራዊው መንግስት መቆማችሁን አረጋግጣችኋል።
አባ መላኩ ፍርድ ቤት ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ መደረጉ እንዲህ አስደንግጧቸው ባስቸኳይ ማስተባበያ ሲያሰራጩ መንፈሳዊ አባትነታቸዉን ረስተው ከምድራዊው መንግስት ጋር በመሰለፋቸው ነገ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ያን ያህል የተጨነቁ አይመስሉም። ስለ ናሽቪል ደብረ ቀራኒዮ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብዙም የሚያውቁት ስለሌለ መሰረት የሌላቸውን መረጃዎች ሲያቀርቡ ተደምጠዋል። የቤተ ክርስቲያኑ ህገ ደንብ ከሚያዘው ውጭ ከተመረጠበት ዘመን በላይ በካድሬዎች ጩኸትና ሁካታ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆየው የአስተዳደር ቦርድ ባቀነባበርው ድርጅታዊ አሰራር ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ የመቀላቀሉን ጥያቄ የ250 ምዕመናን ዉሳኔ አድረግው አቅርበውታል።
ቤተ ከርስቲያናችን 1995 ዓ.ም ሲመሰረት አባላቱ ጥቂት ከመሆናቸውም በላይ አብዛኞቹ የፖለቲካ ስደተኞች ነበሩ። በመሆኑም ህገደንቡን ሲያዘጋጁ ባንድ በኩል መንፈሳዊ አባት መሳይ ካድሬዎች እንዳይፈነጩብን ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የሰጣቸው የመንግስትና የደህንነት ሰራተኞች ጽህፈት ቤት እንዳይሆን በመስጋት ጥንቃቄ አድርገን ነበር። ለዚህ ነው ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ አገር ቤት ዉስጥና ውጭ አገር የሚገኙት ሁለት ሲኖዶሶች በቃለ አዋዲው መሰረት ባንድ ተዋህደው አንድ ወጥ አመራር እሲኪኖር ድረስ የሁለቱንም ሲኖዶስ አባቶች ተቀብለን እናስተናግዳለን፣ ቡራኬአችውንም እንቀበላለን ስንል በህገደንባችን መግቢያ ላይ ያሰፈርነው።
በዚህ አቋማችን ሁለቱንም አንቀበልም ከሚሉት አብያተ ክርስቲያናት የተለየን ነበርን። አዎ፣ በአንዱ ሲኖዶስ ስር ሆነን በሌላው ላይ ድንጋይ መወርወር አልፈለግንም። ምክንያቱም በሁለቱም ሲኖዶስ ስር የሚገኙት አባቶች ይህችው የተዋህዶ እምነታችን በዘመናት ውስጥ ያፈራቻቸው ቅርሶች ናቸው በሚል ነው። እነ አባ መላኩ ጣልቃ እየገቡ እና ካድሬዎቻቸዉን አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) April 14 2016 ለናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት የተሰጠ መልስ ገጽ 2 ከ 2 ከናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስትያን ምዕመናን ለአስተያየትዎ፡ nashvilleeotc2015@gmail.com ይላኩልን።
እያሰለፉ ሰላም እስከ ነሱን ጊዜ ድረስ በዚህ አቋማችን ያለምንም ችግር ላለፉት ሃያ ዓመታት ባአንድነትና በፍቅር አብረን ኖረናል፣ ክፉን እና ደጉን ተጋርተናል። በናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ጠፍቶ ሁከት የጀመረው ባንድ በኩል በዲቪና በነፃ ትምህርት እድል ሰበብ የሚመጡ፣ እንዲሁም በመንግስት ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ንብረት ያፈሩ የመንግስት ካድሬዎችና ደጋፊዎች በቁጥር እየጨመሩ በመሄዳቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ አባ መላኩን የመሳሰሉ ለምድራዊው መንግስት የቆሙ አባት ተብዮች የቤተከርስቲያናችንን መተዳደሪያ ደንብ ተቀብለውና ፈርመው ከተቀጠሩ በኋላ በስውር ለቆሙለት አላማ በመስራታቸው ነው።
እኛ አሁንም ቢሆን እንደክርስቲያንነታችን ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፣ ለዚህም ተግተን እንጸልያለን፣ እንሰራለን። እንደ አባ መላኩ ለምድራዊው ጥቅም ስንል በአቋም አንገለባበጥም። አባ መላኩ በዚህ በቪዲዮ መልክታቸው “ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ እንግባ ሲሉ 250 አባላት በድምጽ ብልጫ ወሰነው ጥያቄ አቀረቡልኝ” ሲሉ የደብዳቤ መረጃ አሳይተዋል። በመሆኑም ሁሉ ነገር በህጋዊ መንገድ እንደተከናወነ ለማሳመን ይጥራሉ። ከዚህ ሁሉ ክንዋኔ በፊት ግን የካድሬዎችን ስድብና ወከባ መቋቋም አቅቷቸው በይሉኝታ ቤተክርስቲያናቸውን ጥለው የሄዱና ሌላ አብያተ ክርስቲያን የመሰረቱ አያሌ አባላት መኖራቸው ሊታወቅ ይገባል። ይሄም ብቻ አይደለም፣ አብላጫ ድምጽ ለማግኘት ሲባል በካድሬዎች ከፍተኛ ድረጅታዊ ስራ ተሰርቷል።
አንድ ወር ባልሟላ ጊዜ ዉስጥ ቤተ ክርስቲያን ደርሰው የማያውቁ ከ አርባ የሚበልጡ አዳዲስ አባላት ተመዝገባዋል፣ ለሁለት አመት እንዲያገለግል የተመረጠው የአስተዳደር ቦርድ ከአባ መላኩ የተሰጠውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲል ብቻ ያለ ምዕመናን ፍላጎት ከአራት አመት በላይ ቆይቷል። ስለዚህ በግንባር ሲታይ የአባ መላኩና የአበሮቻቸው የቦርድ አባላት ከሳሽ አንድ ሰው ይምሰል እንጂ አያሌ ምዕመናን ከበስተ ጀርባችን አሉ። የሰውን ልጅ ሰብዓዊ መብት ጥያቄ በቁጥር አሳንሰው ለማቅረብ ይሞክሩ እንጂ የህግ የበላይነት ባለበት ሃገር አንድም ሰው ቢሆን የመክሰስ መብት የተጠበቀ ነው። አባ መላኩ ከሳሻችን አንድ ሰው ነው ሲሉ ሊያንኳስሱት ቢሞክሩም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አባ መላኩ (አባ ፋኑዔል) በመሳሰሉ ለምድራዊው ጥቅም በአደሩ አባት ተብዮዎች ጣልቃ ገብነት ሰላም ያጡ የአያሌ አብየተ ክርስቲያናት ምዕመናን በመንፈስ በአካልም ከእኛ ጋር ሆነው ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተሉ ናቸው። (የህጉ ሂደት ያሰገኝውን ተጨባጭ ውጤት ይበልጥ ለማወቅ ከፈለጉ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በሚፈቅደው መሰረት ወደ ፊት እናሳዉቃለን።)
ከምድራዊው መንግስት ይልቅ ለሰማያዊው መንግስት ተግተው ይስሩ! ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ከናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን ምእመናን
ለአስተያየትዎ፡ nashvilleeotc2015@gmail.com ይላኩልን።
No comments:
Post a Comment