Saturday, April 23, 2016

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች April 23, 2016 | Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: Zehabesha ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 22, 2016)

ርዕሰ ዜና
·       በጋምቤላ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ በማውገዝ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው
·         የጋምቤላው ፍጅት ልዩ ል ዓለም አቀፍ ተቋሞች አወገዙ
·         በጋምቤላው እልቂት የደቡብ ሱዳን ባላልጣኖች እርስ በርስ መካሰስ ጀምረዋል
·   አምነስቲ ኢንተርናሽናል የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም በሺያ እመነት ተከታዮች ላይ ያካሄደውን ፍጅት አወገዘ
·         ሂውማን ራይትስ ዎች የግብጽ ፖሊሶች በእስረኞች ላይ የሚፈጽሙትን ሰቆቃ አጋለጠ
·         የቻዱ ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ ተባለ
·         36 የጋምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ክስ ተመሰረተባቸው
ሚያዚያ  14 2008 ዓ ም
Ø በጋምቤላ የደረሰውን አሰቃቂና ዘግናኝ እልቂት በመቃወም ዜጎች በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሰንጋ ተራ በሚባለው አካባቢ ተማሪዎች ፊታቸውን ጥቁር ቀለም በመቀባት በጋምቤላ የደረሰውን ፍጅት በመቃወወም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ እየጠየቁ ባለበት ሰዓት ከሆቴል ደ  አፍሪክ ከሚባለው ሆቴል አካባቢ የነበረው የወያኔ የፖሊስ ኃይል ተማሪዎቹን በዱላ በመደብደብ ማባረሩን በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። እነዚህ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና  በራሳቸው ፍላጎት ለወገኖቻቸው ሞትና መታፈን የቆሙ ወገኖች መደብደባቸው ብቻ ሳይሆን ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።

Ethnic Murle gunmen
Ø በጋምቤላ የተፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት ተከትሎ ልዩ ልዩ አገራትና ድርጅቶች የውግዘት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት ፍጅቱን በማውገዝ የታገቱት ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቁን የዘገብን ሲሆን ሀሙስ ዕለትም የአውሮፓው ህብረት በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት ህጻናት እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል። የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኖች ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተው የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በአስቸኳይ የታገቱት ልጆች ወደ ቤተሰባቸው እንዲመለሱ ጥረታቸውን እንዲጨምሩና ፍጅቱን ያካሄዱት ለህግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።


Ø የጋምቤላውን እልቂት ተከትሎ የደቡብ ሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች እርስ በርስ መካሰስ መጀመራቸውታውቋል። የሱዳኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ጀኔራሎችለጋምቤላው ፍጅት የቦማ ግዛት ኃላፊዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። የቦማ ግዛት ገዥ ባባ ሜዳ ለጥቃቱ ጀርባእንደሆኑ የመርሌ ጎሳ አባል የሆኑት ሌ/ጄኔራል ዲቪድ ዋዩ ተናግረው መረጃውን ከአካባቢው መሰብሰባቸውንገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የቦማ ግዛት ኃላፊዎች ለእልቂቱ የጦር መሳሪያ በማቀበል በኑር ጎሳ አባላት ላይ ጥቃቱእንዲፈጸም አስተባብረዋል በማለት የቦማ ባለሥልጣኖች የያገተቱን ህጻናት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።የቦማ ግዛት ኃላፊዎች ግን የተሰነዘረባቸውን ክስ በማስተባበል በጋምቤላው ጥቃት እጃቸው እንደሌለና በግዛቱያሉ ታጣቂዎችም የደቡብ ሱዳን ጦር አባል ሆነው መካተታቸውን ተናግረዋል።


Ø ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓም አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ባወጣው ዘገባ ባለፈው ታህሳስ ወር የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም  350 የሚሆኑ የሺያ እስላም ተከታዮችን ገድሏል፣ አስከሬናቸውን በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በጅምላ ቀብሯል፣ እንዲሁም ድርጊቱን ለመሸፈን የተለያይ እርምጃዎችን ወስዷል በማለት ወንጅሎታል። የሰብአዊ ድርጅቱ በመግለጫው ላይ ሟቾቹ የተገደሉት የአንድ ወታደራዊ ክፍል መሪ የነበሩትን ጄኔራል ለመግደል ሙከራ ሲያደርጉ ነው በሚል ከናይጄሪያ መከላከያ ተቋም የተሰጠውን ምክንያትም መሰረተ ቢስ ነው በማለት አጣጥሎታል። የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል በአምነስቲ የቀረበው ዘገባ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ አለመሆኑን ገልጾ ዘገባውን ከማውጣቱ በፊት ስለዝርዝሩ ሊያሳውቀንና አስተያየታችንን ሊጠይቅ ይገባው  ነበር ብሏል። ትክክለኛ መረጃ አለን ካሉ ያቅርቡና ያሳምኑን የሚል ቃልም አሳምቷል።  ባለፈው ታህሳስ ወር የኢስላሚክ ሙቭመንት ኦፍ ናይጄሪያ የተባለው የሺያ ሙስሊም ድርጅት  አባላት በሰሜን ናይጀሪያ ውስጥ በጸሎት ላይ እያሉ በነበረት ወቅት የወታደራዊ ተቋም መሪ የየሆኑት ጄኔራልን አጅቦ የነበረው ኮንቮይ በአካባቢው እንዳያልፍ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በማሰማታቸው ወታደሩ በወሰደው የበቀል እርምጃ ከ350 ሰዎች በላይ ለመግደል ችሏል ተብሏል። ይህንንም ሀቅ ባለፈው ሳምንት አንድ የናይጄሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን የመሰከረ  መሆኑ ተገልጿል። አምነስቲ ኢንተናሽናል በዘገባው ላይ ፕሬዚዳንት ቡሃሪ በጉዳዩ ላይ ምርመራ ተካሄዶ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ብለው ቃል ቢገቡም እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም ሲል  ዘግቧል። እንዲያውም በተጻራራው  የናይጀሪያ የዜና አውታሮች ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን  በዘገቡት ዜና ካዱና በተባለችው ከተማ 50 የሚሆኑ የሺያ እምነት ተክታይ አባላት አንድ ወታደር ገድለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው እየተጠየቀ መሆኑ ተገልጿል።
በተያያዘ ዜና በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በተሰደዱ ዜጎች ካምፕ አጠገብ አንዲት የቦኮ ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ባፈነድችው ቦምብ ሰባት ሰዎች የተደሉ መሆናቸውን የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቃል አቀባይ ሐሙስ ዕለት ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። የቦምቡ ፍንዳታ የደረሰው ባለፈው ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን 2008 ዓም በንጋቱ ላይ ሲሆን ማይዱጉሪ ከተባለው ከተማ 130 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የናይጄሪያና የካሜሩን ወሰን ላይ ነው። ቦምቦችን ለማፈንዳት  ቦኮ ሃራም ከላካቸው ሁለት ሴቶች መካከል አንደኛዋ የያዛቸውን ቦምብ ሳታፈንዳ እጅ ከፍንጅ ተይዛለች ተብሏል። ቦኮሃራም አእምሮ የሚመረዝ እጽን እየሰጠ ቦምብ እንዲያፈነዱ የሚልካቸው ሴቶችና ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ ይታወቃል።

Ø ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ይፋ ባደረገው ዘገባ በግብጽ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞች ሰቆቃዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው መሆኑን አጋልጧል። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ህጻናት መሆናቸውንም ገልጿል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቱ ይፋ ባደረገው ዘገባ ባለፈው የካቲት ወር ህገ ወጥ በሆኑ የተቃዋሚ ስልፎች ላይ ተሳትፋችኋል፤ የንብረትና መዝረፍና የማቃጠል ወንጀል ፈጽማችኋል ተብለው  በአሌክሳንድሪያ የታሰሩ ዜጎች በእስር ላይ እያሉ ከፍተኛ ድብደባና የአካል ስቃይ የደረሰባቸው መሆኑን ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ዘግቧል። ድርጅቱ ከ20 በላይ በሚሆኑ እስረኞች ላይ ድብደባ እንደተፈጸመ መረጃ የደረሰው መሆኑን ገልጾ የግብጽ መንግስት ከፍተኛ ድብደባ የፈጸመባቸው እስረኞች በቁጥጥር ስር መደረጋቸውን በመጀመሪያ ክዶ የነበረ መሆኑን የሰብአዊ መብት ድርጅት መግለጫ ያጋልጣል። የግብጽ ባለስልጣኖች ዘገባው የፈጠራ መረጃው የያያዘ ነው በማለት አጣጥለውታል።  ወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወስደው አሰቃቂ እርምጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በየጊዜው የተገለጸ ሲሆን ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር የሚገኙ እስረኞችን በድብደባ  ገድላችኋል ተብለው በርካታ የግብጽ ፖሊሶች ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው መሆኑ ይታወሳል።

Ø የቻዱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዲቢ ለአምስተኛ ጊዜ በምርጫ አሸንፈው ስልጣን የተቀዳጁ መሆኑ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ተነገረ። ኢድሪስ ዲቢ  የድምጹን 60 ከመቶ በማግኘት  17 የሚሆኑ ተወዳዳሪዎቻቸውን አሸንፈው ነው ድል ተቀዳጅተዋል የተባለ ሲሆን ያገኙት ከድምጹ 50 ከመቶ በላይ በማግኘታቸው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ማካሄድ አላስፈለጋም። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫው የተጭበረበረ ስለሆነ አንቀበለውም ብለዋል። በርካታ የምርጫ ሳጥኖች የተሰረቁ መሆናቸውንና ፤ ወታደሮችን ጨምሮ ኢድሪስ ዲቢን  በመቃወም ድምጽ የሰጡ ግለሰቦች መታሰራቸውና መዳረሻቸው መጥፋቱን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ነው ቢሉም በርካታ ሰዎች ያልተዋጠላቸው መሆኑ ታይቷል። በምርጫው ወቅት የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በሞባይል ስልኮች መልክቶችን መለዋውጥ ሳይቻል ቀርቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት አራት የሲቪል ማህበራት መሪዎች ሕዝቡን ለስላማዊ ስልፍ አነሳስታችኋል በማለት መታሰራቸው ይታወሳል። ምርጫው የተካሄደው የሆስፒታል ሰራተኞች የትምህርት ቤት አስተማሪዎችና የዩቢቨርስቲ ፕሮፈሰሮች የተወዘፈ ደሞዛቸው እንዲከፈል የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ነው። ቻድ በ1995 ዓም በአገሪቱ የተገኘውን የነዳጅ ምርት መጠቀም ብትጀምርም 13 ሚሊዮን የሚሆነው የአገሪቱ ዜጋ ከድህነት በታች በሆነ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚኖር ሲሆን  ከቻድ ዜጎች መካከል ከ 10 ሩ  ሰባቱ መጻፍ እና ማንበብ እንደማይችሉ መረጃዎች ይፋ አድርገዋል።


Ø 36 የጋምቢያ  የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ሐሙስ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው በልዩ ልዩ ወንጀሎች የተከሰሡ መሆናቸው ተገለጸ፡፤ የዩናይትድ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሚስተር ዳርቦይ ከተከሰሱት መካከል አንዱ ሲሆኑ ተካሶቹ በስድስት የተለያዩ ክሶች የተከሰሱ መሆናቸውና በዋስ ለፈቱ መቻላቻውና አለመቻላቸው በሚቀጥለው ሳምንት እስከሚወሰን ድረሰ በእስር ቤት እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑም ተነግሯል። የዩናይትድ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ጸሐፊ ሚስተር ሳንዴንግ እና ሌሎች ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ያልተፈቀደ ሰላማዊ ስልፍ አደራጅታችኋል በሚል ሰበብ የታሰሩ መሆናቸው ሲታወቅ ግለሰቡና ሌሎች ሁለት ሴቶች በእስር ቤት በድብደባ ህይወታቸው ያለፈው መሆኑ ተነግሯል። የፓርቲው መሪ ሚስተር ዳርቦይ እና ሌሎች ተከሳቾች የታሰሩት ባለፈው ቅዳሜ ቀደም ብለው የታሰሩት አባሎቻቸው የታሰሩበት ምክንያት አለአግባብ አለመሆኑን ለመግለጽ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ ነው ። የአፍሪካ የሂውማን ራይትስ ኮሚሽን እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የታሰሩትን  ለመጎብኘት እንዲችሉ ፈቃድ የጠየቁ መሆናቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment