Saturday, April 16, 2016

የአማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ ቴሌቪዥን ተጀመረ




ከኤቢኤን የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ከሁሉ አስቀድመን አስከዚች እለት እና ሰዓት በ ሕይወት አቆይቶ ያደረሰንን ብሩክ የአማራ አምላክ ልናመሰግን እንወዳለን፣ ክብር ምስጋና ለገነነ ስሙ ይሁን። የአማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ ዓርብ ሚያዝያ 07 በይፋ የ ቴሌቪዥን ሥርጭቱን ጀመረ።

የአማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ ከማንኛውም ድርጅትም ይሁን ቡድን ነፃ የሆነ በ ዋናነት በ አማራ ሕዝብ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ ሃሳቦችን የሚያቀርብ እና የሚያስተናግድ የ ቴሌቪዥን ዝግጅት ነው ።
የአማራ ሕዝብ ላለፉት አያሌ አመታት ሕዝባዊ ሓርነት ትግራይ በተባለው ድርጅት መሪነት እየደረሰበት ያለው ግፍ እና እንግልት ፅዋውን ሞልቶ በመፍሰስ ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ ህዝቡ ከ መረጃ እጥረት የተነሳ ክንዱን አስተባብሮ እራሱን ሲከላከል አልታየም።ለዚህ ነው የ አማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ የ ቴሌቪዥን ስርጭትን መጀመር ያስገደደው ።
በመሆኑም የ አማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ በ አማራ ሕዝብ ጉዳይ ላይ ያገባኛል ከሚል ማንኛውም አካል ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁነቱን በዚህ አጋጣሚ ሊገልጥ ይወዳል ።
በተባበረ ክንድ ጠላትን በቀላሉ ማሸነፍ እንደሚቻል የሚያምነው የ አማራ መገናኛ ብዙሃን መረብ ሁሉም የ አማራ ልጅ የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ ዛሬ ነገ ሳይል በህብረት እና በአንድነት ለትግል እንዲነሳ ጥሪውን ያስተላልፋል። የ አማራ ወጣቶች የ ቅዱስ አባታቺን ፃድቁ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ፈለግ ተከትለን አስፈላጊውን የሕይወት መስዋእትነት ከፍለን በሕዝባችን ላይ የተቃጣውን የፈፅሞ መጥፋት አደጋ እናስወግድ።
Breaking News Amara Broadcasting Network (ABN) TV starts
We would like to announce the establishment of Amara broadcasting network TV. It is launched this last Friday(April 16,2016GC or April07,2008EC). We’ve been working on this for some time and we are so excited to finally announce that the start of this broadcasting with you all. There will be a new episode every day.
Share0  278  2 
 Share2

Sponsored by Revcontent

TRENDING ARTICLES

No comments:

Post a Comment