Tuesday, April 26, 2016

አዲስ አበባ ከዓለም ከተሞች ስድስተኛው ቆሻሻ ከተማ ተብላለች – [ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች



ፍካሬ ዜና ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 24, 2016 Weekly NEWS SUMMARY)
‪#አጫጭር‬ ዜናዎች
‪#በጋምቤላ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ በታጣቂዎች ተገደሉ
#ድርቁና ርሀቡ እየመረረና እየተባባሰ እንደሆነ ተነገረ
#ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ እያነጋገረ ነው
#የኤች አይ ቪ/ኤይድስ/ ስርጭት እየጨመረ መሆኑ ይፋ ተደረገ
#የብሔራዊ ባንክ ከግል ባንኮች የተበደረውን ገንዘብ በተባለው ጊዜ እንዳልመለሰ ታወቀ
#በተጭበረበረ ሰነድ መሬት የቸበቸቡ የወያኔ ካድሬዎች መከሰሳቸው ታወቀ
‪#የውጭ‬ አገር ዜናዎች
ADDIS ABABA
ፍካሬ ዜና
ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም.
አልፎ አልፎ ሁሉንም ነገር በልኩና ይዘቱ መገምገም መቻላችን አስፈላጊ መሆኑ መጠቀስ አለበት ። ዜና ስለ ወያኔ ማቅረቡ የሞኝ ነገር መልሶ መላልሶ ሊያሰኝብን ስለሚቃጣው የድግግሞሽ ወልፍ ይዞን ሳይሆን ሀቁ መነገር፣ መመዝገብ እንዲሁም ለታሪክና ትውልድም መተላለፍ ስላለበት መሆኑን ማስገንዘቡ የግድ ይሆናል ። ሀቁ ካልተመዘገበና ካልተነገረ የሕዝብና ሀገር ጠላቶች ነገ ምስክር የለም ብለው ሀሰት ሊያሰራጩ እንደሚችሉ የፋሺስቱ ደርግ መሪዎች መጽሃፍ ብለው ከሚያቀርቡት ወይንም ወያኔ በጫትና በገንዘብ ገዝቶ ከሚያጽፋቸው የብዕር ቅጥረኞች ክታቦች ሁሉ መረዳት እንችለላን ። ወያኔ የተለወጠው የለም — ትላንትም ገድሏል፤ዛሬም እየገደለ ነው ። ዘራፊና ከይሲ ቡድን ነው –ትላንትም ዛሬም ነገም ። ሀርና ሕዝብን ከከዳ ዓመታት አልፈዋል ። ያው ሁሌም ያው ስለሆነ ነጋ ጠባ ውሻ ሰው ነከስ የምንል እንደሚመስልብን እናውቃለን ። ሆኖም፤ የወያኔ ወንጀል ነጋ ጠባ መነገርና መታወቅ አለበት ። የታሪክና የትውልድ የሀቅ ቅርስ ጉዳይ ነውና ። የምንደጋገመው ወያኔ ወንጀሉና ክህደቱን ስለሚደጋግም ብቻ ነው ።
ወደ ዜናዎቹ እንሸጋገር
አጫጭር ዜናዎች
 ፎርብስ የተባለው የአሜሪካ መጽሄት ባካሄደው ጥናት አዲስ አበባ ከዓለም ከተሞች ስድስተኛው ቆሻሻ ከተማ
ተብላለች ። ኮሾ በሚባለውን በጥራቱ በጣም ዝቅተኛ በሆነው የመሶቦ (የወያኔ) ስሚንቶ የሚሰሩትና ነገ ፈራሽ
የሚሆኑ ሕንጻዎች የመራትና የውሃም አገልግሎት የሌላቸው ከመሆኑም በላይ አንዳንድ የዲያስፖራ ስግብግቦች
ግለሰቦች ኮንዶሚኒየም ብለው ስበዕናቸውን ሸጠው የያዟቸው ቤቶችና ሕንጻዎች አፍንጫ ተይዞ የሚገባባቸው
እንደሆኑ ማንም ያውቀዋል ። ቆሻሻ አንሺ መኪናዎችን ሊያስገቡ የጣሩ ግለሰቦች ወያኔ አግዶ አላሰራ ያለቸው በመሆኑ
እና ማዘጋጃ ቤት ተብዬው ደግሞ ችሎታ በሌላቸው የሙስና አባወራዎች በመሞላቱ፤ ሚሊዮኖች በመጥፎ ሁኔታ
በመኖራቸውና መንገድ አዳሪም በመሆናቸው (ዶሮን ሲደልሏት ዓይነት የጎዳና ተዳዳሪ ተብለው ይጠራሉ)፤ እንዲሁም
በቂ መጸዳጃ ቦታዎችና ውሃም በመጥፋቱ አዲስ አበባ ትገማለች ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ተመችቷቸዋል፤ወሃና
መብራትም በጄኔሬተር ማግኘት ይችላሉ የሚባሉት ያው የገዥው መደብ (የወያኔ አባላትና) አጋሮቾቻቸው መሆናቸው
የሚካድ አይደለም ተብሏል ።
 የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ እያደገ እየተመነደገ ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ ወያኔና አጋሮቹ በጠራራ ጸሃይ ድርቅ ብለው
የሚያናፉት ውሸት ነው በሚል ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት ዜጎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። ከአስር ሚሊዮን
ያላነሰ ሕዝብ ለረሃብ ተጋልጦ’፤ ሚሊዮኖች ሕጻናት ለሞት አደጋ ተዳርገው ፤ በቀን አንዴ መብላት ራሱ ብርቅ
በሆነበት ሁኔታ ፤ የድህነትና የኑሮ ውድነት መጠን ሰማይ ነክቶ፤ ብዙሃኑ ለስቃይ ተዳርጎ ኤኮኖሚው አደገ ብሎ
መለፈፍ በሕዝብ ላይ መቀለድ ነው ያሉ ክፍሎች ሁኔታው ለገዢዎቹ–በተለይም አንዳንዶች የአድዋ ገዢ መደብ ነን
ለሚሉት-ግን አመቺና አመርቂ መሆኑ ሊካድ የሚችል አይደለም ብለዋል ። የሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ የውሃ ሽታ
ሆኖ የኑሮ ውድነት ግን ሰማይ ጠቀስ ሆኖ መቀጠሉን የጠቀሱት ታዛቢዎች ይህ አገዛዝ ኢትዮጵያን ወድ ውድቀት
እንጂ ወደ ዕድገት አልወሰዳትም ሲሉ ያረጋግጣሉ ። ረሃቡን በአየር ጠባይ ለማላከክ ጥረት ቢደረግም የወያኔ
የፖለቲካና የኤኮኖሚ ፖሊሲ ሀገሪቷን ለአስከፊ ሁኔታ መዳረጉን መደብቅ አይቻልም ተብሏል ።
 ለአራት ጊዜ ያህል አመላልሶ ካደከማቸው በኋላ የወያኔ አቃቤ ህግ በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ዋና ጸሀፊ በአቶ
በቀለ ገርባ እና በሌሎች 22 ሰዎች ላይ የሽብረተኛነት ክስ የመሰረተ መሆኑ ታወቀ። ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም.
በተሰየመው የየፖሊካ ፍርድ ቤት ላይ የወያኔው አቃቤ ህግ እነ አቶ በቀለ ገርባን በኦሮሞ አካባቢዎች ለተነሳው
ህዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ ተጠያቂ ናቸው ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሉ ክሶች አቅርቦባቸዋል። በዚህ የክስ
መዝገብ ላይም አንድ የኬኒያ ዜጋ አብሮ መከሰሱ ታውቋል። ተከሳሾቹ አመጽ ለመቀስቀስ ተሰማርተዋል በሚል
ተጨማሪ የሽብረተኛነት ክስ የተከሰሱ ሲሆን አቃቤ ህጉ ተጨማሪ ቀን በመጠየቁ ለሚያዚያ 18 ቀን ተቀጥሯል።
 በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የፖለቲካና ወታደራዊ ሁኔታ ውጥረት ውስጥ ይከተዋል ተብሎ የሚሰጋው የጦር ሠፈር
አሰብ ላይ መቋቋሙን ወታደራዊ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ምንጮች አስታውቀዋል። ሻዕቢያ በአሰብ ወደብ አቅራቢያ
ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬት የጦር ሰፈር አገልግሎት የሰጠ ሲሆን የተባበሩት አረብ
ኤምሬትም በአሰብ ወደብ ላይ አንድ የባህር ኃይል የጦር ሠፈር እየገነባች መሆኗ ተደርሶበታል። የባህር ኃይሉ የጦር
ሰፈር ለ30 ዓመት ኮንትራት የተገነባ ሲሆን ለሻዕቢያ የተሰጠው ክፍያ ግን አልተገለጸም። ሻዕቢያ በየመን የእርስ
በርስ ጦርነት ከአረብና ከገልፍ አገሮች ጎን በመቆም 400 ወታደሮቹን በሁቲዎች ላይ ማዝመቱ ይታወቃል። ሳኡዲ
አረቢያም ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጎን በመሆን ቀይ ባህርን ሙሉ በሙሉ በአረብ አገሮች ቁጥጥር ስር በማድረግ
በምስራቅ አፍሪካ የፖሊቲካና ወታደራዊ ተጽእኖዋን ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ናት ተብሏል። የአረብና የገልፍ
አገሮች በተለይም ሳኡዲ አረቢያና የአረብ ኤምሬት የኢራን ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴን ለመገደብ የአሰብ
ወደብን እንደመንደረደሪያ እየተጠቀሙበት መሆኑ ተገልጿል።
 የሶማሊያው አልሸባብ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓም ስድስት የወያኔ ወታደሮችን መንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጅ
መግደሉን አስታውቋል። የፈንጅ አደጋውን በደቡባዊ ባይ ግዛት ውስጥ አውደሊን ከተማ አቅራቢያ መሆኑን የገለጹ
ሲሆን በጥቃቱ ወቅት የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ያሰማራቸው ሰላም አስከባሪ በወታድር አጀብ ይጓዝ እንደነበረና
ከሞቱት የወያኔ ወታደሮች ውስጥ ከፍተኛ አዛዦች እንደሚገኙበት አብራርቷል። በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሰላም
አስከባሪ ኃይል አልሸባብ አደረስኩ ስለሚለው ጥቃት የተናገረው ነገር የለም። የወያኔ አገዛዙም እንደተለመደው
የተነፈሰውና ያለው ነገር አልተመዘገበም።
በጋምቤላ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ በታጣቂዎች ተገደሉ፡፡
 ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ሌሊቱን ለቅዳሜ አጥቢያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር ጥሰው የገቡ ሙርሌ የሚባል ጎሳ አባላት
እንደሆኑ የሚነገርላቸው የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱና ሙሉ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቁ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ
ግለሰቦች የአካባቢው ኗሪዎችን የጨፈጨፉ ሲሆን ሁለት መቶ አስር የሚጠጉ ሴቶችንና ህፃናትና አፍነው እንደከብት
እየነዱ ወስደዋቸዋል፡፡ በዚህ አደጋ ከሰማንያ ሰዎች በላይ ጽኑ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እነዚህ ድንበር አቋርጠው
ይህን አሰቃቂ ጭፍጨፋ የፈጸሙ ከደቡብ ሱዳን ግሬት ስቦር ከሚባል ክፍለ ሀገር ተነስተው ጆርና ኦኛላ በሚባሉ
አቅጣጫዎች 175 ኪሎ ሜትር ተጉዘው ወደ ኑዌርና አኙዋክ አካባቢወች በመዝለቅ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ
አረመኔ ኃይል ይህን ዘግናኝ አደጋ ከፈጸመ በኋላ ከሁለት ሺ በላይ ከብቶችን እየነዳ የተመለሰው በእግር መሆኑ
ታውቋል ይህ ሁሉ ሲሆን የጋምቤላ ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ፈጣን የሆነው የወያኔ አረመኔ አጋዚ የሚባለው ጦር
እንኳን ሕዝብን መታደግ ቀርቶ ዝር አለማለቱ የወያኔን ፀረ-ሕዝብነት የሚሳይ መሆኑን ወቅታዊ የፖለቲካ ተንታኞች
ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ዘግናኝ አደጋ አስራ አምስት ቀናት በፊት የከብቶች ዘረፋና በኗሪዎቹ ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን
የሚገልጹ የአካባቢው ኗሪዎች ወያኔ ሆን ብሎ የጋምቤላ ገበሬዎችን መሣሪያቸውን ገፎ ከማስደፈር አልፎ
እያስገደላቸው እንደሆነ በምሬት ይገልጻሉ፡፡ ወያኔ የአዞ እምባውን ቢያንጠባጥብም የሕዝቡን የተሰበረ መንፈስ
ሊጠግን እንደማይችል ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ የጋምቤላ ሕዝብን እርስ በእርስ እያፋጀና አንዱን ጎሳ በመደገፍ
በርካታ ጋምቤላዎችን እንደጨፈጨፈ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
የተገደሉትና ታፍነው የተወሰዱት አልበቃ ብሎ በደቡብ ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ሌሎች 14 ኢትዮጵያውያን
መገደላቸው ተነግሯል።ግድያው የተፈጸመው ከጋምቤላ ከተማ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ጃዊ የስደተኞች ካምፕ
አቅራቢያ መሆኑ የተነገረ ሲሆን መንስኤው አንድ ኢትዮጵያዊ ሹፌር በአንድ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና
አደጋ በማድረሱ ነው ተብሏል። በአራቢያው የነበሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በመኪና አደጋው ምክንያት የሞተውን
ግለስብ ለመበቀል በገጀራ በድንጋይና እና በቢላዋ 14 ኢትዮጵያውያንንን በጭካኔ የገደሉ ሲሆን የወያኔ የፖሊስም
ሆነ የወታደር ኃይል በአካባቢው ዝር ሳይል ቆይቷል።
ድርቁና ርሀቡ እየመረረና እየተባባሰ እንደሆነ ተነገረ፡፡
 በየሳምንቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድርቁና ርሀቡ እየተባባሰ በመሄድ ላይ እንደሆነና የእዳታ ገንዘብ እንደሚያስልግ
የዓለምን ህብረተሰብ እየወተወቱ ነው፡፡ ከውጪ የተገዛው ስንዴ ጂቡቲ ወደብ እንደደረሰና የማጓጓዣ እጥረት
እንዳጋጠመ በመጥቀስ ችግሩ እየመረረ ባለበት በሱዳኑ ወደብ በፖርት ሱዳንና በሰሜን ሶማሌ በሀርጌሳ ወደብ የእርዳታ
እህልና መድሀኒት ለማስገባት ወያኔ መደራደሩ ተሰምቷል፡፡ በኢትዮጰያ ሃያ ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት ወለል
በታች የሆነ ኑሮን፣ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል በሚሉት የኑሮ አረንቋ እየማቀቀ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት
የምግብ ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡ ከረሀብና ከድርቅ ጋር የተገኙ ጥናቶች የሚያካሄዱ ተመራማሪዎች እንደሚሉት
ከድህነት ወለል በታች የሚኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ሃምሳ ከመቶ ከፍ ማለቱን አስረግጠው ያስረዳሉ፡፡ የዓለም
የምግብ ድርጅት እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ ማለትም የዚህ የፈንጆቹ አመት የ2016 ማለቂያ ድረስ ርሀብተኛውን
ሕዝብ ለመመገብ 435 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ለጋሾችን እየተማጸነ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡
ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ እያነጋገረ ነው፡፡
 ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን እንዳወከና እንዳስተጓጎለ ታይቷል፡፡ ወያኔ
ለዚህ እጥረት የሰጠው ሰበብ ከጅቡቲ 150 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ የጣለው ነጎድጓዳማ ዝናብ በደፈናው መንገዱን
በመዝጋቱ እንደሆነ ቢግልጽም ታዛቢዎች እንደሚሉት መንገዱ በጎርፉ በመወሰዱ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንዲህ ያለው
አውራ መንገድ ከግንባታው ጀምሮ በተለየ ጥንቃቄ ሊገነባ ይገባው እንደነበር የሚጠቅሱ ታዛቢዎች ይህ አንዱ የቻይና
የግንባታ ውጤት እንደሆነ ማስረጃ መሆኑንም ያስረዳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በየቀኑ የቤንዚን ፍጆታ ከ 1.2 ሚሊዮን
ሊትር በላይ ሲሆን የናፍጣ 6.5 ሚሊዮን ሊትር፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 2 ሚሊዮን ሊትር፣ የነጭ ጋዝ 260 ሺ ሊትር
በላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተከሰተው ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት የተከሰተው ናፍጣ ላይ በመሆኑ በርካታ ሥራዎች
ተስተጓጉለው መሰንበታቸው ታውቋል፡፡ ሃምሳ ከመቶ የሚሆነው ነዳጅ የሚጫነው ከኩየት ሲሆን ለጊዜው ባልታወቀ
ምክንያት ነዳጅ የጫነችው መርከብ መድረስ ከሚገባት ቀን ከአስር ቀናት በላይ ዘግይታ ጅቡቲ ወደብ መድረሷም
ሌላው ምክንያት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ፡፡
የኤች አይ ቪ/ኤይድስ/ ስርጭት እየጨመረ መሆኑ ይፋ ተደረገ፡፡
 ወያኔ በሽታንና ርሀብን ለፖለቲካ ትርፍ ለግኘት ሲል የሚያቀርበው የውሸት መረጃ በየጊዜው ድርጊቱ እያጋለጠው
መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የኤች አይ ቪ ህሙማን ቁጥር መቀነሱን ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ እንዲህ ያለው የሀሰት
መረጃ እየቀረበ ባለበት የእርቃን ዳንኪራ ቤቶች፣ በመታሻ ቤት ስም የወሲብ ቤቶች፣ በጫት መቃሚያ ቤቶች ስም
የወሲብ ቤቶች፣ እንዳሸን በአዲስ አበባና በመላው ሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ሳይቀር በፈሉበት ሁኔታ ኤች አይ ቪ
ይስፋፋል እንጂ ከቶውንም ሊቀንስ አይችልም የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ አደንዛዥ እጾችን ከካናቢስ እስከ ሄሮይን
የሚወስዱ ሱሰኞች እየተበራከቱ ባሉበት ኤች አይ ቪ እንደ ሰደድ እሳት አገርን ይወራል እንጂ አይቀንስም፡፡ በቅርቡ
ብሔራዊ የኤች አይ ቪ ጽህፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው በየአመቱ ከሃያ ሺ በላይ አዲስ የኤች አይ ቪ ህሙማን
እየተመዘገቡ እንሆነና ይህም የማይመዘገበውን እንደማይጨምር ይፋ አድርጓል፡፡ ለህመሙ ቅርበት ያላቸው ሀኪሞች
እንደሚስረዱት ቁጥሩ በእጥፍ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ የወያኔ ባልስልጣኖች እነ ጄኔራል ባጫ ደበሌና ሳሞራ
ዩኒስን ጨምሮ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ናቸው የሚልም ዘገባ መደመጡ ይታወሳል ብለዋል ታዛቢዎች።
የብሔራዊ ባንክ ከግል ባንኮች የተበደረውን ገንዘብ በተባለው ጊዜ እንዳልመለሰ ታወቀ፡፡
 በወያኔ አስገዳጅነት ብሔራዊ ባንክ ከግል ባንኮች ለዓባይ ግድብ ግንባታ 45 ቢሊዮን ብር በሰነድ መበደሩ ይታወሳል፡
፡ ይህ ገንዘብ እስከ ዛሬ ሳይመለስ ከርሞ ሰሞኑን የቦንድ ግዥውን ከፈጸሙ አምስት አመት ለሞላቸው ባንኮች ብቻ
ወደ ሦስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተመላሽ እንደተደረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ባንኮቹ ከዚህ ገንዘብ የሚያገኙት ወለድ
ሦስት ከመቶ ብቻ በመሆኑና ገንዘባቸው በእጃቸው ቆይቶ ቢሆን እያበደሩ በርካታ ትርፈ ያገኙበት እንደነበር የሚገልጹ
ከፍተኛ የባንክ ባለሙያዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው እስካሁን ባንኮች ብድር ሲያበድሩ ሃያ ሰባት
ከመቶውን ለብሔራዊ ባንክ ሰነድ ግዢ እንዲያውሉ ይገደዳሉ፡፡ ይህ የባንኮቹ እድገት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሰ
መሆኑ ይነገራል፡፡
በተጭበረበረ ሰነድ መሬት የቸበቸቡ የወያኔ ካድሬዎች መከሰሳቸው ታወቀ፡፡
 ወያኔ የመልካም አስተዳደር ዘመቻ በሚል ቧልት ጉልቻዎቹን ከቦታ ቦታ እየቀያየረና አንዳንዱን ደግሞ ለይስሙላ
ዘብጥያ እያወረደ ይገኛል፡፡ በኦሮሞ አካባቢዎች በብዙሀን መገናኛ ወደ ሰባት መቶ የሚጠጉ ኃላፊዎችን ካሉበት
ኃላፊነትና ከሥራ ያሰናበተ መሆኑን ቢገልጽም ሀቁ ግን ከቦታ ቦታ፣ ከከተማ ከተማ እያዛወረ መሆኑን ተረድተናል፡፡
በአዲስ አበባ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማዎች 26 መሬት አስተዳደር ላይ የሚሠሩ ሠራቸኞች 84.9 ሚሊዮን
ብር ገቢ በማሳጣት ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲህ ያለው ክስ ለይስሙላ ከመቅረብ ባለፈ
የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ቃሲም ፊጤ የተባለ አዲስ አበባ መሬት አስተዳደር
ኃላፊ የነበረ በመሬት ማጭበርበር ተከሶ በአባ ዱላ ትእዛዝ ከእስር በነፃ እንዲሰናበት መደረጉ አይረሳም፡፡ ይህ ቃሲም
የተባለ ዘራፊ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የዝርፊያ ቦታ በሆነው የኦሮሞ መሬት አስተዳደር ኃላፊ ሆኖ መሾሙ የወያኔን
የመልካም አስተዳደር የህፃናት የእቃ እቃ ጨዋታ ያደርገዋል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡
የውጭ አገር ዜናዎች
 ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ በጁባ ይገባሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የደቡብ ሱዳን
የአማጽያን መሪ ሪክ ማቻር በታቀደው ቀን ጁባ ሳይገቡ ቀርተዋል። ለጉዟቸው መዘግየት ምክንያት የሆነው ሬክ
ማቻርን አጅቦ በሚሄደው ኃይል ብዛትና ይዞት በሚሄደው የመሳሪያ ብዛትና ዓይነት ላይ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣኖች
ጋር ስምምነት ባለመደረሱ ነው ተብሏል። ተመድ እና የምዕራብ መንግስታት ሪክ ማቻር ቅዳሜ ወደ ጁባ እንዲሄዱ
ቀን ቢቆርጡም እቅዱ ሊከበር እንዳልቻለ ማወቅ ተችሏል። አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓም በነፍስ ወከፍ ኤኬ
47 አውቶማቲክ መሳሪያ ከታጠቁ 190 አጃቢዎች እና 20 መትረየሶችና ከ20 አርፒጂ ጋር እንዲገቡ ስምምነት ላይ
የተደረሰ በመሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር
እንደገለጹት ሚስተር ሪካ ማቻር የሚጓዙበት አውሮፕላን ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚፈቀድለት ከጋምቤላ አውሮፕላን
ማረፊያ ከመነሳቱ በፊት የሚመጡት ሰዎች ቁጥርና የያዙት መሳሪያ በስምምነቱ መሰረት መሆኑን የዓለም አቀፍ
ድርጅት አባላት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ ብቻ ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እንዲሁም
አሜሪካ እንግሊዝ እና ኖርዌይ ሚስተር ሪክ ማቻር እንዲመለሱ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተነግሯል።
 በዚህ ሳምንት በሱማሊያ ውስጥ አንዲት የሰማንያ ዓመት አሮጊትና ዘጠኛ አመት ያላት የልጅ ልጃቸው ታመው
በአንድ መኪና ወደ ሞቃዲሾ ሲወሰዱ የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ወታደሮች በመንገድ ላይ ተኩስ
ከፍተው አሮጊቷንና የልጅ ልጃቸውን እንዲሁም በመኪና ውስጥ የነበሩትን ሌሎች ሁለት ሰዎች በመግደላቸው
የታችኛው ሸብሌ ግዛት ነዋሪዎች ድርጊቱን በማወገዝ ተቃውሞ አሰምተዋል። የሰላም አስከባሪው ኃይል ባለስልጣኖች
6
ድርጊቱ የተፈጸመ መሆኑን ያመኑ ቢሆንም ወታድሮቹ ተኩስ ሊከፍቱ የቻሉት መኪናው እንዲቆም ቢጠየቅ ለማቆም
ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው ብለዋል።
 በዚህ ሳምንት በምዕራብ አፍሪካ በምትገኘው ጋምቢያ ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በእስር ላይ እንዳሉ
መገደላቸው ዓለም አቀፍ ተቃውሞንና ውግዘትን አስከትሏል። የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን ባወጡት መግለጫ
የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት በእስር ቤት ውስጥ መገደላቸው በእጅጉ ያሳዘናቸው መሆኑን ገልጸው ስለአገዳደላቸው
አስቸኳይ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓም የጋምቢያ ወጣቶችና ሌሎች
ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ውስጥ የምርጫ ሕግና ሂደት እንዲሻሻል የሚጠይቁ ሃሳቦችን በማቅረብ ትእይንተ ህዝብ
ባደረጉበት ወቅት ሲሆን በእስር ቤት የተገደሉትና ሌሎች በርካታ ስልፈኞች በፖሊስ መያዛቸው ታውቋል።
ከተያዙት መካከል የተቃዋሚው ፓርቲ መሪዎችን ጨምሮ 36 የሚሆኑ ሰዎች በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ
ቤት የቀረቡ መሆናቸው ተገለጿል።
 በብሩንዲ በስልጣን ያለው ገዥ ፓርቲ አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ መምጣታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ
ተነገረ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የገዥው ፓርቲ አባላት የሆኑ አራት ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው
የሚታወስ ሲሆን በዋና ከተማዋ አንድ የኮሎኔል ማዕረግ ያለው ወታደራዊ መኮንንም በዚህ ሳምንት የተገደለ መሆኑ
ታውቋል። ኮሎኔል አማኑኤል ቡዙቦና የተባለው መኮንን የተገደለው ከአንድ ሌላ ሰው ጋር በሞተር ቢስክሌት
እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ላይ ሲሆን አብሮት የነበረውም ሰው ተገድሏል። በብሩንዲ ውስጥ የርስ በርስ ግጭት
ከተጀመረ ወዲህ ወታደራዊ መኮንኖች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በተደጋጋሚ እየተገደሉ መሆናቸው ሲታወቅ
የመንግስቱን ስልጣን በያዘው ኃይልና በተቃዋሚዎች መካከል እርቅ እስካልሰፈነ ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል
ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ።
 በኮንጎ ብራዛቪል ፑል ተብሎ በሚጠራው ደቡባዊ ግዛት ከሶስት ሳምንት በፊት የመንግስት ወታደሮች በሄሊኮፕተር
አማካይነት ባካሄዱት የአየር ድብደባ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉ መሆናቸውን በዚህ ሳምንት
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት አጋልጧል። የአየር ጥቃቱ ኒንጃ የተባሉት
የቀድሞ የሚሊሺያ ቡድን አባላት ቀደም ብሎ በሰነዘሩት ጥቃት 17 ሰዎችን መግደላቸው ተከትሎ የተደረገ መሆኑን
የመንግስት ቃል አቀባይ ቢገልጽም ሄሊኮፕተሮቹ የአየሩን ድብደባ ያካሄዱት በመኖሪያ ቤቶች፤ በትምህርት ቤቶች
በአብያተ ክርስቲያን እና በህክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ላይ በመሆኑ ከሰላሳ የበለጡ ሰላማዊ ሰዎች
ተገድለዋል በማለት አምነስቲ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
 በደቡብ አፍሪካ ላለፉት አራት ዓመት ከመስሪያ ግዥ ጋር ተያይዞ ፕሬዚዳንት ዙማ እና ሌሎች ባለስልጣናት ከፍተኛ
ሙስና ፈጸመዋል በሚል ቀርቦ የነበረው ክስ ሲያጣራ የነበረው ኮሚሽን ስራውን መፈጸሙንና ፕሬዚዳንቱን ነጻ
ማውጣቱን በዚህ ሳምንት ፕሬዚዳንት ዙማ በሰጠቱ መግለጫ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን
2008 ዓ.ም በሰጡት መግለ ኮሚሽኑ ዘገባውን ያቀረበው ከአራት ወራት በፊት ቢሆንም አሁን ለሕዝብ ይፋ ሆኗል
ካሉ በኋላ ባደረገው ምርመራ መሰረት በእሳቸውም ሆኖ በሌሎች ላይ ምንም ጥፋት ያላገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ዙማ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በነበሩበት ወቅት እሳቸውና አማካሪዎቻቸው ከዓለም አቀፍ የመስራሪያ
ሻጭ ድርጅቶች በርካታ ገንዘብ ወስደዋል ተብለው ተከሰው የነበሩ ሲሆን አማካሪያቸው በተመሳሳይ ክስ የአስራ
አምስት ዓመት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑና ተቃዋሚዎች በአቃቤ ህጉ ላይ ያልሆነ ተጽእኖ አምጥተዋል በሚል
ምክንያት በዙማ ላይ የነበረው ክስ እንዲነሳ ተድርጎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ዙማ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው
ከተመረጡ በኋላ ጉዳዩን እንዲመረምር አዲስ ኮሚሽን ቢያቋቁሙም፤ አካሉ ኃይል እና ስልጣን ኖሮት አለተጽእኖ
ስራውን ሊያከናውን የሚችል አይደለም በማለት አንዳንድ ወገኖች ሲያጣጥሉት እንደነበር አይዘነጋም።
 ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ይፋ ባደረገው
ዘገባ በግብጽ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞች ሰቆቃዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው መሆኑን አጋልጧል። ድርጅቱ
ይፋ ባደረገው ዘገባ ባለፈው የካቲት ወር ህገ ወጥ በሆኑ የተቃዋሚ ስልፎች ላይ ተሳትፋችኋል፤ የንብረትና መዝረፍና
የማቃጠል ወንጀል ፈጽማችኋል ተብለው በአሌክሳንድሪያ የታሰሩ ዜጎች በእስር ላይ እያሉ ከፍተኛ ድብደባና የአካል
ስቃይ የደረሰባቸው መሆኑን ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ዘግቧል። ከ20 በላይ በሚሆኑ እስረኞች ላይ ድብደባ
የተፈጸመባቸው መሆኑ የተነገረ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ህጻናት መሆናቸው ተነግሯል። የግብጽ
ባለስልጣኖች ዘገባው የፈጠራ መረጃው የያያዘ ነው በማለት አጣጥለውታል። ወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን
ከመጣ ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወስደው አሰቃቂ እርምጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በየጊዜው የተገለጸ
ሲሆን ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር የሚገኙ እስረኞችን በድብደባ ገድላችኋል ተብለው በርካታ የግብጽ ፖሊሶች
ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው መሆኑ ይታወሳል። በተያያዘ ዜና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሀመድ ሞርሲ
የካታር መንግስት ሰላይ ናቸው የሚል ቀርቦባቸው ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የሚቀርቡ መሆኑ
መሆኑ ተነግሯል። ካታር የሚስተር ሞርሲን አስተዳደርና የግብጽን የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ስትረዳ
መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን የፕሬዚዳንት ሲሲ አስተዳደር ካታር በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች በሚል ክስ
ትታሰማ መቆየቷም ይታወቃል። በፕሬዚዳንት ሲሲ እና በተባባሪዎቻቸው አማካይነት በተካሄደ ወታድራዊ መፈንቅለ
መንግስት በስልት ከስልጣናቸው የተነሱት ሞርሲ ከዚህ ቀደም በሶስት የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የሞት ፍርድ፤
የእድሜ ልክ እስራትና የሃያ አመታት እስራት የተበየነባቸው መሆኑ ሲታወቅ ይህኛው ክስ አራተኛው መሆኑ ነው።
ሞርሲ እና ሌሎች አስር ሰዎች የግብጽ የጸጥታ ሁኔታን የሚመለከቱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ
ተቀብለው ከካታር ሸጠዋል የሚል ክስ አቃቤ ህጉ ያቀረበባቸው መሆኑ ታውቋል።
 አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በዚህ ሳምንት ባወጣው ዘገባ ባለፈው ታህሳስ
ወር የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም 350 የሚሆኑ የሺያ እስላም ተከታዮችን ገድሏል፣ አስከሬናቸውን በአንድ ጉድጓድ
ውስጥ በጅምላ ቀብሯል፣ እንዲሁም ድርጊቱን ለመሸፈን የተለያይ እርምጃዎችን ወስዷል በማለት ወንጅሎታል።
የሰብአዊ ድርጅቱ በመግለጫው ላይ ሟቾቹ የተገደሉት የአንድ ወታደራዊ ክፍል መሪ የነበሩትን ጄኔራል ለመግደል
ሙከራ ሲያደርጉ ነው በሚል ከናይጄሪያ መከላከያ ተቋም የተሰጠውን ምክንያትም መሰረተ ቢስ ነው በማለት
አጣጥሎታል። የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል በአምነስቲ የቀረበው ዘገባ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ
አለመሆኑን ገልጾ ዘገባውን ከማውጣቱ በፊት ስለዝርዝሩ ሊያሳውቀንና አስተያየታችንን ሊጠይቅ ይገባው ነበር
ብሏል።
በተያያዘ ዜና በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በተሰደዱ ዜጎች ካምፕ አጠገብ አንዲት የቦኮ
ሃራም አጥፍቶ ጠፊ ባፈነድችው ቦምብ ሰባት ሰዎች የተደሉ መሆናቸውን የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቃል አቀባይ
ሐሙስ ዕለት ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። የቦምቡ ፍንዳታ የደረሰው ባለፈው ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን 2008
ዓም በንጋቱ ላይ ሲሆን ማይዱጉሪ ከተባለው ከተማ 130 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የናይጄሪያና የካሜሩን ወሰን ላይ
ነው። ቦምቦችን ለማፈንዳት ቦኮ ሃራም ከላካቸው ሁለት ሴቶች መካከል አንደኛዋ የያዛቸውን ቦምብ ሳታፈንዳ እጅ
ከፍንጅ ተይዛለች ተብሏል። ቦኮሃራም አእምሮ የሚመረዝ እጽን እየሰጠ ቦምብ እንዲያፈነዱ የሚልካቸው ሴቶችና
ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ ይታወቃል

No comments:

Post a Comment