Wednesday, April 20, 2016

በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ


በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ::
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – የጋምቤላ ፖሊስ እና ልዩ ሃይል ወደ ካምፕ ሆን ተብሎ ሰብስቦ ማስገባትን መሳሪያ ማስፈታትን ወታደሩን ክፍል ከድንበር አከባቢ ሰብስቦ ስብሰባ ግምገማ ማስገባትን አስታኮ ባለፈው አርብ እለት በተከታታይ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው በገቡ እና ከባድ እና ቀላል መሳሪያ በታጠቁ የመርሊ ጎሳ አባላት እና የደቡብ ሱዳንን ወታደራዊ ልብስ ለብሰው በግድያ እና በአፈና ላይ በተሰማሩ ታጣቂ ሃይሎች የተወሰደውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ተከትሎ የሕወሓት አገዛዝ በወንበዴዎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ብሎ በሃሰት እየቀጠፈ መሆኑን እና በድንበሩ አከባቢ ምንም አይነት የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ እንደሌለ በአከባቢው የሚገኙና በአቶ ቶዋት ፓል ቻይ የሚመራው የአኙዋክ ኑዌር አማራ እና ኦሮሞ ብሄሮች የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር/Ethiopia United Patriots Front (EUPF)/ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት አባላት የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች ገልጸዋል::
Minilik Salsawi's photo.
በቡማ በኒያኒያንግ ጋጃክ እና ጃኮው በሚባሉ አከባቢዎች እና የድንበር አዋሳኝ ቦታዎች የሚኖሩ እና ጉዳዩን በጥልቀት የተመለከቱ የአይን እማኞች የሆኑን የግንባሩ አባላት የመከላከያ ሰራዊት እየገደለ እየማረከ ነው እየተባለ የሚወራው የወያኔ የሃሰት ቅጥፈት እንደሆነና በአከባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ ከለመኖሩም በላም ወደ ድንበር አከባቢዎች የተጠጋ ጦር እንደሌለና ከምእራብ እዝ የተመደቡ የሰራዊቱ አባላት የሕወሓት ኢንቨስተሮችን ደህንነት በመጠበቅ ስራ ላይ እንደተሰማሩ ገልጸው በኢትዮጵያውያን እና በደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ የደረሰው ጥቃት ይደገማል የሚል ስጋት እንዳጠላ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::የጋምቤላ የፖሊስ እና የልዩ ሃይል ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ተሰብስቦ ካምፕ እንዲገባ መደረጉ መሳሪያ እንዲፈታ መደረጉ የጋምቤላ ፖሊስ መኮንኖች ለስብሰባ በሚል ሰበብ ክልሉን ለቀው ወደ መሃል አገር መጠራታቸውን የገለጹት ምንጮቹ ሕዝቡ በሕወሓት አገዛዝ ላይ እምነት ስላሌለው ቀየውን እየጣለ ወደ መሃል ሃገር እየተሰደደ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል::
ከባድ እና ቀላል መሳሪያዎችን ታጥቀው ጥቃቱን ያደረሱት ገዳዮች በሕወሓት መኮንኖች በሱዳን ናይል ግዛት ደማዚን አቅራቢያ እንደሰለጠኑ ጥርጣሬ እንዳላቸው የገለጹት ምንጮች አመጣጣቸውም ከደማዚን መስመር ቀጥታ ወደ ቡማ እንደነበር አስረግጠው ተናግረዋል::ምንጮቹ አክለውም ዋናው አለማ የጋምቤላ ሕዝቦን ሰላም ማሳጣት እና ሰው ተረጋግቶ እንዳይኖር ሽብር መፍጠር መሆኑን ጠቁመው የደቡብ ሱዳን የፖለቲከኞች ድርድር ወደ መጠናቀቅ መቃረቡ ሌላው የሕወሓት እና የደቡብ ሱዳን ስጋት በመሆኑ አከባቢውን የጦርነት ቀጠና በማድረግ በብሄር ግጭት የመጣ ከስምምነት ሊደርሱ የተቃረቡትን እንደገና ወደ ብጥብጥ እንዲያመሩ በማድረግ ላይ አተኩሮ በአከባቢው ሕወሓት እና ሰሜን ሱዳን ያላቸውን የግል ጥቅም ለማስከበር የታቀደ ነው::አከባቢው አሁንም ውጥረት እንዳጠላበት እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment