(ዘ-ሐበሻ) በርካታ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ወደ ዝግጅት ክፍላችን እየደወሉና እየጻፉ “ስለ አበባ ተስፋዬ የሚወራው እውነት ነው ወይ?” ሲሉ ጥይቀውናል:: ዘ-
ሐበሻ ወደ አዲስ አበባ የተለያዩ የዜና ምንጮቿ ጋር ደውላ ለማረጋገጥ እንደቻለችው አባባ ተስፋዬ ላይ እንደሚወራው አይደለም:: አባባ ተስፋዬ ትናንት ከተሸለሙና መልካም ቀን ከማሳለፋቸው በስተቀር በሰላም እየኖሩ ነው:: ወደቀ ሲባል ተሰበረ የሚሉ ወገኖች በሶሻል ሚድያዎች አባባ ተስፋዬ እንዳረፉ አድርገው ቢያስወሩም እርሳቸው ግን በሕይወት አሉ::
አባባ ተስፋዬ በአሁኑ ወቅት 93ኛ ዓመታቸው ሲሆን ትናንት እርሳቸውን በሕይወት እያሉ ለመዘከር በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የ10 ሙያዎች ባለቤት መሆናቸው ተወስቷል:: ከ10 በላይ ሙያ ባለቤት እንደሆኑም በዝክር መድረኩ ላይ ተወስቷል። ተዋናይ፣ ድምጻዊ፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲ (የልጆች ተረት)፣ ተረት ተናጋሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ የምትሃት ባለሙያ እንዲሁም ሌሎችም::
ረዥም ዕድሜ ይስጥልን::
No comments:
Post a Comment