Monday, April 25, 2016

የደቡብ ሱዳን የአማፅያን የጦር አዛዥ ጀኔራል ሲመን ዱዋልና ወታደሮቻቸው ጁባ ገቡ::




BBN News April 25, 2016
የደቡብ ሱዳን እርስበር ጦርነት መንስዔ የነበሩት አማፅያን የጦር አዛዥ ጀነራል ሲመን ዱዋልና ወታደሮቻቸው ጁባ መግባታቸው ታወቀ፡፡ የአማፅያኑ መሪ ሪክ ማቻር ዛሬ ከጋምቤላ ወደ ጁባ ያመራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የአማፅያኑ የጦር አዛዥ የሚታስከትሏቸውን ወታደሮችና የሚይዟቸውን የጦር መሳሪያ አይነት በተመለከተ በተፈጠረው አለመግባባት የደቡብ ሱዳን ጥምር መንግስት ምስረታ ከአንድ ሳምንት በላይ እንዲራዘም ተደርጎ የነበረ ሲሆን ኤኬ 47 ክላሽንኮቭ የጦር መሣሪያ የታጠቁ 195 ሰዎች እና 20 መትረየስ እንዲሁም 20 ባዙቃ ይዘው መጓዝ እንደተፈቀደላቸው ሱዳን ትሪቢን ዘግቧል።
simon
ከኢትዮጵያ የጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሱት ሪየክ ማቻር የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ሲቀሰቀስ መዲናዩቱ ጁባን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የሸሹት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪየክ ማቻር ከባላንጣቸው እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሆነው በምክትል ፕሬዚዳንትነት የሽግግር መንግሥት እንደሚመሰርቱ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የሙርሌ ጎሳ አባላት በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙት አሰቃቂ ግድያ፣ በሳልባ ኪርና በሪክ ማቻር መካከል ያለው የስልጣን ፍትጊያ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል አንድ አትላንቲክ ካውንስል የተባለ ጋዜጣ ዘገበ።
በኑዌር ብሄረሰብ ላይ ጥቃት ያደረሱት የሙርሌ ብሄረሰብ አባላት በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ መሆናቸውና በዲንቃ ጎሳ አባላት መታጀባቸው የሪክ ማቻር ጎሳ አባላት በአንድ በኩል የሳልባ ኪር ጎሳ አባላት በሌላ በኩል አካባቢውን በመሳሪያ ሲያጥለቀልቁ እንደቆዩ አመላካች ሊሆን እንደሚችል አትላንቲክ ካውንስል የተባለው ጋዜጣ እትሙ አስነብቧል። ከዚህ የጦር መሳሪያ ዝውውርም የሙርሌ ጎሳ አባላት ተጠቃሚ ሳይሆኑም እንዳልቀረ ጋዜጣው ባወጣው ዘገባው አስፍሯል።
ሰሞኑን የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ አወሳስቦታል ያለው አትላንቲክ ካውንስል ጋዜጣ፣ ከሶስት ወር በፊት በአኙዋክና በኑዌር ጎሳዎች መካክል ግጭት ተከስቶ በርካታ ሰዎች ለሞት እና ለመቁሰል እንዲሁም ንብረት መውደም እንዳስከተለ ጋዜጣው ትንታኔ ሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪም እኙዋኮች በደርግ ጊዜ ማለትም እኤአ በ1980ዎቹ ጀምሮ በአካባቢው ከሰፈሩት ከደገኞች ጋር አልፎ አልፎ ግጭት ይገቡ እንደነበረ ጋዜጣው በዘገባው አስፍሯል።
በጋምቤላ ክልል መንግስት በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት መካከለም በተለያዩ ጊዜያት ቅራኔዎች እንደነበሩ የተነተነው አትላንቲክ ካውንስል፣ በአካባቢው ጸጥታ በማስፈን ሂደትም ደገኞቹ ወታደራዊ መሪዎች ውሳኔ ሰጪ በመሆን የክልሉን ስልጣን ጠቅለው ወስደዋል ብሏል። እኤአ በ 2003 ዓም የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ አኙዋክ ነዋሪዎችን ከገደሉ በኋላ በፌዴራል በክልሉ መንግስታት መካከል አለመተማመን በእጅጉ ሰፍኖ እንደቆየ ጋዜጣው በዘገባው አትቷል።
ይህ ሁሉ ተደማምሮ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደተገለሉ አይነት ስሜት ሊፈጥርባቸው እንደሚችልና ከደቡብ ሱዳን ጎሳዎች ሌላ ጥቃት ሊደርስባቸው እንደማይችል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደማይሰማቸው ጋዜጣው አብራርቷል።

No comments:

Post a Comment