Monday, April 18, 2016

በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ያለው የጎሳ ግጭትና የወያኔ ሚና

በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ያለው የጎሳ ግጭትና የወያኔ ሚና


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በጃኮው እና በኒያኒያንግ አቅራቢያ ሰፍረው የነበሩ ወታደሮች ለምን አከባቢውን እንዲለቁ እንደተደረገ የወያኔ አገዛዝ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል::ጭፍጨፋውን ተከትሎ ለምንስ አከባቢዎቹን መክበብ እና ወጪ ገቢውን ማገድ አስፈለገ? ባለፈው አንድ አመት ብቻ ከመሃል ሃገር ከጅቡቲ በአፋር በር ከፖርት ሱዳን በሁመራ በኩል ወደ ትግራይ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ከባድ እና ቀላል የጦር መሳሪያዎች መጓጓዛቸው ሲታወቅ ይህን የጦር መሳሪያ መጓጓዝ ምናልባት ላያስገርመን ይችላል:: ዋናው የጦር መሳሪያው የተፈለገው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የጎሳ ጦርነት በማስነሳት ሕዝብ ሲገደል ሲሰደድ እና ሲታኮስ የሕወሓት አመራሮች መቀሌ ላይ በምስኪኑ የትግራይ ገበሬ ትከሻ ላይ ተቀምጠው መሳሪያውን ወደ መሃል ሃገር በማስተላለፍ ከፍተኛ እልቂትን ለመፍጠር የታቀደ ጉዳይ ነው::
ወደ ደቡብ ሱዳን ስንዞር ቤንዚኑ ወያኔ ከሰሜን ሱዳን ጋር በመተባበር ደቡብ ሱዳን ሰላም እንዳታገኝ እና የተፈጥሮ ሃብቷን ተጠቅማ እንዳትበለጽግ በጎሳ ጦርነት በማመስ ድፍርስ ሃገር ያልተረጋጋ መንግስት እንዲኖር ሕዝቡም እንዲገደል እና እንዲሰደድ እንቅልፍ ሳይተኙ ደፋ ቀና እያሉ ነው::የደቡብ ሱዳን መገንጠል ተከትሎ የተነሳው ከፍተኛ የሆነ የጎሳ ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆተሩ ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲሰደዱ በካምፕ ውስጥ በወያኔ ባለስልጣናት ትእዛዝ እንዲሰፍሩ የተደረጉት በብሄራቸው ተለይተው ነበር::በሰሜን ሱዳን እና በወያኔ እገዛ የታጠቁት የሙርሌ ጎሳ አባላት ከቀያቸው ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ የገቡትን እና ያልታጠቁ ኑዌሮች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ኑዌሮችን ጨምሮ በጅምላ በተደጋጋሚ ጨፍጭፈዋል::ባለፈው አርብ በማለዳ የጀመረው ጥቃት በሁለት ዙር በዛው አርብ እለት ማምሻውን መደገሙ በአከባቢው ላይ ድንበር ጠባቂ የሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች የሉም ወያ የሚያስብል ጥያቄ አስነስቷል::ወያኔ በአከባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት እና የተፈጥሮ ሃብት ጥቅም ያገኝበታል:: ይህ ጭፍጨፋ የተካሄደው በበረሃ ተጓዦች ላይ ሳይሆን በአንድ አከባቢ በሰፈሩ እና መንግስት አለበት በተባለ ሃገር ላይ ጥበቃ እና እርዳታ ይደረግላቸዋል ተብሎ በስማቸው በሚነገድባቸው የስደተኞች ካምፖች እና ብዙሪያ ባሉ መንደሮች ላይ መሆኑ የሕወሓት መራሹ አገዛዝ የሚከተለው ወታደራዊ እና የውጪ ፖሊሲ እድቀት በገሃድ ሲያመለክት ሕወሓት ከሰሜን ሱዳን ጋር በመሆን እያስፋፋ ያለው የደቡብ ሱዳን ሰላም የማደፍረስ አንዱ አካል መሆኑ ያሳያል::
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የቀድሞ ስርኣቶችን እስከመናፈቅ ያደረሳቸው የወያኔው አገዛዝ ዜጎችን ገዳይ ፖሊሲውና ለዜጎች ደንታ ቢስ መሆኑን ማሳየቱ ነው::ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው ቡማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የታጠቁ ሃይሎች የሆኑት የሙርሌ ጎሳዎች የደቡብ ሱዳንን ወታደራዊ ዩኒፎርም እንዲለብሱ ተደርጉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ እንዳለ ሲያመለክት ጭፍጨፋው ከተካሄደ በኋላ ቦታው በሕወሓት ወታደሮች ተከቦ በአከባቢው ምም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ጋዜጠኞች እንዳይደርሱ መደረጉ ደግሞ የወያኔን ሚና በግልጽ ይጠቁማል::ድንበሩን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የጋጃክ ኑዌር ጎሳ አባላትን መግደላቸው የወያኔ ሴራ ሲሆን ሕዝብ ሲጨፈጨፍ በአከባቢው ያልነበሩ ወታደሮች የጨፍጫፊዎቹ ተልእኮ ከተጠናቀቀ በኋላ አከባቢውን መክበብ ሕወሓት የተጫወተችውን ሚና ያሳያል::በጃኮው እና በኒያኒያንግ ሰፍረው የነበሩ ወታደሮች ለምን አከባቢውን እንዲለቁ እንደተደረገ የወያኔ አገዛዝ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል::ወያኔ ሰሜን ሱዳን በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ እልቂቶች እንዲከሰቱ እየሰሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ድንበር ተከፍቶ የደቡብ ሱዳ ስደተኞች እና በአከባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሲጨፈጨፉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም::ለዚህ መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ እው የሕወሓትን አገዛዝ ማስወገድ አራት ነጥብ – ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment