Sunday, April 24, 2016

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን 3ኛ ወጣ | አትሌት ትዕግስት ቱፋ 2ኛ ወጣች


Filed under: News Feature,Sport,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች | 


(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በተደረገው የለንደን ማራቶን የኬንያ አትሌቶች በወንዶችም ሆነ በሴቶች አሸናፊ ሆኑ:: ኢትዮጵያውያኑ ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች 3ኛ ሲወጣ በሴቶች አትሌት ትዕግስት ቱፋ 2ኛ ወጥታለች::
ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ፈይሴ ታደሰ በውድድሩ ላይ እንዲህ ወድቀው ነበር:: (ፎቶ ከሬውተርስ)
ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ፈይሴ ታደሰ በውድድሩ ላይ እንዲህ ወድቀው ነበር:: (ፎቶ ከሬውተርስ)
የዘንድሮውን የለንደን ማራቶን ያሸነፈው ኬናዊው ኢሉድ ኪፖቾጌ ሲሆን ውድድሩን 02:03:05 ጨርሷል:: 2ኛ የወጣው ሌላኛው ኬንያዊ አትሌትም ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀበት ሰዓት 02:03:51 ሆኗል::
ለሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ድሎችን በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ሲያስገኝ የነበረውና አሁን ፊቱን ወደ ማራቶን እያዞረ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ይህን የለንደን ማራቶን በ02:06:36 በመግባት 3ኛ መውጣቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል:: ኤርትራዊው ግርማይ ገብረሥላሴ በ02:07:46 4ኛ ሲወጣ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጥላሁን ረጋሳ በ02:09:47 በመግባት 6ኛ ወጥቷል:: እንዲሁም በ 02:10:45 በመግባት አትሌት ሲሳይ ለማ 7ኛ; ኤርትራዊው አትሌት ገብሬ ክብሮም በ 02:11:56 በመግባት 10ኛ ወጥቷል::
ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያዊያኑ አትሌቶች ጋር (ፎቶ ሬውተርስ)
ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያዊያኑ አትሌቶች ጋር (ፎቶ ሬውተርስ)
በሴቶች ማራቶን ኬንያዊቷ አትሌት ጀሚያ ሱምጎንግ በ 02:22:58 በመግባት አንደኛ ስትወጣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ት ዕግስት ቱፋ በ02:23:03 በመግባት 2ኛ ወጥታለች:: 3ኛ የወጣችውም ኬንያዊቷ ፎሎረንስ ኪፕልጋት ስትሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሰለፈሽ መርጊያ በ02:23:57 በመግባት 5ኛ; ማሬ ዲባባ በ 02:24:09 በመግባት 6ኛ; ፈይሴ ታደሰ በ02:25:03 በመግባት 7ኛ ወጥተዋል:

No comments:

Post a Comment