Tuesday, April 19, 2016

ኢትዮጵያ ዉስጥ ርሃብተኛው አምስት ኪሎ ደርሷል; ወያኔና አሽቋላጮቹ ዳላስ ላይ ልማት እያልን እንጫወት ይሉናል



ከዳላስ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ
የወያኔ ኢምባሲና የዳላስ አልማ ቻርተር ብሎ ራሱን የሚጠራ ቡድን ስብሰባ መጥራታቸውን አሜሪካ በሚገኘው ቆንሲላ ስም የተጻፈ ለተወሰኑ ሰዎች የተላከ ጥሪና የመግቢያ ትኬት ደረሰን።
ቦታው፤
Hyatt Place Dallas
5101 George Bush HWY
Garland, TX 75040
በ4/24/16 ዕሁድ ቀን ሁለት ስዓት ላይ
እንግዳው አቶ ደመቀ መኮንን የተባለ የወያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴር ነው። ይህ ሰው ለዚህ ሹመት የበቃው 1600 ኪሜ የሚረዝመዉን ያገራችን መሬት ለሱዳን አሳልፎ የሰጠውን የወያኔ-ትግሬዎች ስምምነት በመፈረም ነው። ወያኔዎች ዝለል ሲሉት ምን ያህል ከፍታ? ብሎ የሚጠይቅ ሆድ አደር ነው። ደመቀ።
ደጋሾቹ፦
አንደኛ ተኮላ መኮንን የተባለ የቀድሞው ስመ ጥር አየርውለድ አባል የነበረ -ድርጊቱ በጀግንነታቸው የሚታወቁትን ያን ብርቅየ ትውልድ ስም የሚያጠለሽ። ዳላስ ዉስጥ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ለምን በወየናኔው ሲኖዶስ ስም ካልሆነ ብሎ ክስ መስርቶ በፍርድ ቤት የተረታ። ከሱ አልፎ ትክለሃይማኖትን በመሰለ ቅዱስ ስም የሚጠራን ታቦት ተለጣፊ ያደረገ መሰሪ ፍጥረት ነው።
ሁለተኛው ጽሃይ ጽድቅ የሚባል የምዕመናኑን ገንዘብ መዋጮ ሰብስቦ ለወያኔ እጅ መንሻ ያስረከበና ሸራተን ላይ በውጭ የሚንቀሳቀሱትን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ስም በቲቭ ይዘልፍ የነበረ።
ሶስተኛው አባቡ የሚባል ባህርዳር ላይ ህንጻ አለኝ ብሎ ነጻነቱን አሳልፎ የስጠ ሆድ አደር ናቸው።
በደረሰን መረጃ መሰረት ስብሰባው በዳላስ አካባቢ ለሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች በክልሉ ስለሚደረጉ ንግድና ኢንቨስትመንት፣በቤቶች ልማት ፕሮግራሞችና በክልሉ ስለሚደረጉ ልማቶች ለመወያየት ነው።
ይህ ያጼ ቴዎድሮስን የትውልድ ቦታ ቋራን አስልፎ ለሱዳን ያስረከበ ባንዳ፣ የወልቅይት ህዝብ “አገር አልባ” ሆኖ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ከወያኔ ጋር በሚተናነቅበት ወቅት አማራውን አሰባስበን ልማት ልናስፋፋ ነው ይለናል።
ነገሩ ግን ወዲህ ነው። የወልቃይት ህዝብ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበት፣ ከትውልድ ትውልድ ከኖረበት መሬት አየተፈናቀለ፣ አማራነቱን ትቶ ትግራዋይነትን ካልተቀበልክ ተብሎ በሚጋዝበት፣ በሚታሰርበት፣ ሴቶቹ ተገደው በሚደፈሩበትና በግፍ በሚገደልበት ወቅት ኑ! ተሰብሰቡና ስለልማት እናውራችሁ ይሉናል። እነ ደመቀ።
በተወሰኑ ባገሪቱ ክፍሎች በተከሰተው ድርቅ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ወገኖቻችን በርሃብ አያለቁ ባሉበት ወቅት እነ ተኮላ የተባሉ ጉዶች ኑ! ተሰብሰቡና ባማራው ክልል ስለሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ እናውራችሁ ይሉናል።
ከመሬታችን ተፈናቅለን ለማኝ መሆን በቃን ያሉ የኦሮሞ ወገኖቻችን አንደቅጠል እየረገፉ ባሉበት ወቅት ኑ! አገሪቷ እየለማች ነው እድሉ እንዳያመልጣችሁ ይሉናል፣ እነ ጽሃይ ጽድቅ።
በኦሞ ውንዝ አካባቢ የሚኖሩ የሙርሲ ወገኖቻችን እንደ እንስሳ አንገታቸው ታስሮ ባስቃቂ ሁኔታ በሚጋዙበት ባሁኑ ወቅት እነኝህ ሆዳሞች ተሰብስበን ገዳዩን የወንበዴ መንግስት በልማት ስም ይበልጥ እያወድልንና አያደነደን ህዝባችን አናስጨርስ ይሉናል።
መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚጠይቁ ዜጎች ላይ ሃይሉን ለማሳየት ደክሞ የማያውቅ መንግስት፣ ሰራዊታችን ካለም አራተኛ ነው አያለ የሚያቅራራ መንግስት፣ ከሶስት ቀን በፊት ጋምቤላ ዉስጥ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች 208 ሰዎች ሲገሉ ምንም አይነት መልስ ያልሰጠ የወንበዴ መንግስት ዳላስ ድረስ ዘልቆ ኑና ኣለም ባንክንና ኣይ.ኤም.ኤፍን ባሞኘሁበት ምህታታዊ የዕድገት አሃዝ ላሞኛችሁ ይለናል።
የዳላስ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ያለወያኔ አመራርና የሆድ አደሮች ግፊት ለወገን ደራሽ መሆናቸውን አስመስክረዋል። የህዝብ መብት ሳይከበር፣ ያንድ ብሄረሰብ ሁሉንም ያገሪቱን ልማታዊ መዋቅሮችና ወታደራዊ ሃይሉን በተቆጣጠረበት ሁኔታ፤ አገር አንደማይለማ አነሱም ያውቁታል አኛም አይጠፋንም። አነኝህን የታሪክ አተላዎች በጠሩበት ቦታና ጊዜ ተገኝተን አድቡ ልንላቸው ይገባል።
የአማራው፣ የኦሮሞ፣ የሙርሲው፣ የጋምቤላው በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝባችን ደም ዳላስ ድረስ ይጮሃል!

No comments:

Post a Comment