0
(BBN Radio) በኢትዮጵያ ለጥጥ ልማት ተብለው ለባለሀብቶች የተሰጡ መሬት ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ እና ገንዘብ ስራ አልዋለበት ተባለ፡፡ የጨርቃ ጨርቅና ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለጥጥ ለማልማት ተብለው ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ ለባለሀብቶች ብድር ያበደረው ገንዘብ ምን ላይ እንደዋለበት አለመታወቁን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ለጥጥ ልማት ተብለው ከተሰጡት መሬቱ ምን ላይ አንደዋለ ለማጣራት አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ በተለያዩ ክልሎች ተዘዋውሮ እያጣራ መሆኑን ታውቋል፡፡ ህወሀት መራሹ በጋምቤላ ክልል ለልማት ተብሎ ነዋሪዎቹን በማፈናቀል ብዙ የዘር ጭፍጨፋ ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ በጋምቤላ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተሰጡት መሬት እንዳለማ እና ገንዘቡ ለተባለለት አላማ እንዳልዋለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት ፌደራል መንግስቱ በውክልና የክልሎችን ሰፋፊ ለም መሬቶች ተረክቦ ለውጭ ባለሃብቶችና ዓለም ዓቀፍ የእርሻ ኮርፖሬሽኖች በርካሽ በሊዝ ሲያከራይ መቆየቱ ብርቱ ትችት አስከትሎበት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ኢሀዴግ እየደረሰበት ያለውን ኪሳራ ተከትሎ ለኢንቨስተሮች ለግብርና ስራ የሚውሉ ሰፋፊ ለም መሬቶችን ላልተወሰነ ጊዜ መስጠት ማቆሙን ይታወሳል፡
No comments:
Post a Comment