(ዳዊት ዘሚካኤል)
ወደብ አሽቀንጥሮ፤
እንደ አባቱ ጓሮ።
ድንበር የትም ጥሎ፤
”ምን ይረባል!”ብሎ።
የአንድነት ብርሃን፥ የነፃነት ፀሃይ፤
ሲያሣድድ ባ’ያሌ፤
ሲያስጠብቅ በጀሌ፣ በሃገር እንዳይታይ
በ’ምክን’ አልቦ ምክንያት፤
‘ሞት’ ወገኔን በላት
የጋምቤላን እናት
ሰደድ እሳት ላሣት።
በእንዲህ ያለ አገዛዝ፣
በእንዲህ ያል ቁልቁለት፤
የ’ሞቱ’ ሠንሠለት፤
”ነገ አይመጣም” ማለት
‘ራስን ማሞኘት፤
አውቆ ተላላነት።
አሁን መላ ምቱ፥ ዛሬ መላ እንምታ
የታሠርንበትን ፍርሃት እንፍታ
ዕንባም ይታበሣል፥ በ”ለምን?” ከፍታ፤
ዛሬስ መላ ምቱ፥ አሁን መላ እንምታ
‘ሞት’ ያሣቀፈንን፥ ፍርሃት እንፍታ።
No comments:
Post a Comment