Thursday, April 21, 2016

ከደቡብ ሱዳን የመጡ ኑዌሮች በጋምቤላ 15 ኢትዮጵያውያንን ገደሉ



(ዘ-ሐበሻ) ከዛው አካባቢ የመጡ ሰዎች እንደሚናገሩትበጋምቤላ ከኑዌር; አኝዋክ; ዲንቃ ወይም ሌላ የጋምቤላ ብሔረሰብ አባላት ውጭ ያሉት ለምሳሌ ኦሮሞ; አማራውና ትግሬው ወይም ሌላው የሚጠራው “ሐበሻ” በሚል ነው:: ባለፈው አርብ የሙርሌ ጎሳ አባላት የተባሉ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የኑዌር ተወላጅ የሆኑ ከ200 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንን ገድለው; 125 ህፃናትን እና ሴቶችን አፍነው የወሰዱበት አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ ትናንት ሐሙስ ጠዋት በድጋሚ በጋምቤላ የተከሰተው አሳዛኝ ዜና አነጋጋሪ ሆኗል::
የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ እንዳመለከቱት ከደቡብ ሱዳን የመጡ ናቸው የተባሉት የኑዌር ተወላጆች በጋምቤላ 15 ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል:: ከነዚህም ሟቾች መካከል ሴቶች እንደሚገኙበት የገለጹት እማኞች አካባቢው አለመረጋጋቱ ታውቋል::  እንደ እማኞቹ ገለጻ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል… በርካቶችም ቆስለዋል::መንግስት በአኝዋኮች እና በኑዌሮች የርስ በ እርስ ግጭት የተነሳ ሁለቱንም ጎሳዎች ትጥቅ ያስፈታ በመሆኑ ሕዝቡ ራሱን ለመከላከል አለመቻሉን ያነጋገርናቸው ወገኖች ገልጸዋል::
ከደቡብ ሱዳን የመጡት ኑዌሮች በተለምዶው “ሐበሾች” የሚባሉትን ኢትዮጵያውያንን የገደሉት ወደ 10 ሰዓት ገደማ ሐሙስ እለት መሆኑም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያሳያል::
Share0

No comments:

Post a Comment