(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ከደቡብ ሱዳን እንደመጡ በተነገረላቸው የሙርሌ ጎሳ በመጡ ታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱት ህፃናት ያሉበትን ስፍራ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማወቁን እና መክበቡን አስታወቀ::
የመንግስት ሚድያዎች ዛሬ እንደዘገቡት ከኢትዮጵያ ታግተው የተወሰዱት ህፃናት በአሁኑ ወቅት ጆር እና ቆቅ በተባሉ አካባቢዎች እንደሚገኙ ሲገለጽ በዚህም አካባቢ መከላከያ ሰራዊትቱ ህፃናቱን ለማስልቀቅ በታጣቂዎቹ ላይብ ጥቃት ከፍተው አካባቢውን መክበባቸውን አስታውቀዋል::
በጋምቤላ በነዚህ ታጣቂዎች ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ቆይታለች:: ከዚህ በተጨማሪም 125 ህፃናት እና ከ2 ሺህ በላይ ከብቶችም መወሰዳቸው መዘገቡ አይዘነጋም::
Share1 6168 0
Sh
No comments:
Post a Comment