Wednesday, April 20, 2016

ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ሳውዲ ገብተዋል ! – ነቢዩ ሲራክ

====================
የአሜሪካና የሳውዲ ግንኙነት ከየት ወደ የት ? 
ለግንዛቤ የሚሆን አጭር ምልከታ
==============
* እጎአ በ1933 ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የጀመሩት ሳውዲ አረቢያና አሜሪካ ባደረጉት መልካም ግንኙነት ተደጋግፈው የቀጠሉ አጋር ሀገሮች ናቸው ።
* እጎአ በ1944 ሳውዲ የናጠጠች ሃብታም ሃገር ያደረጋትን የነዳጅ አውጭ ድርጅት አራምኮን በመመስረት ከአሜሪላ ጋር የመሰረተችው ጠንካራ ግንኙነት ለኢኮኖሚው መሰረት መጣሉ ይጠቀሳል ።
* ተጠናክሮ በቀጠለው ግንኙት ሳውዲ በ2015 ከአሜሪካ ያስገባቻቸው መኪና ፣ ማሽነሪዎችና አውሮፕላኖች ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች 22, 080 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይገመታል ።
* በአንጻሩ አሜሪካ በ2015 ወደ ሳውዲ ያስገባቸው ነዳጅና ከመዳክ ምርት ጋር ተዛማጅ የሆኑ የተለያዩ ተረፈ ምርቶች 19,690 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይገመታል ።
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በሳውዲ ለሁለተኛ ጊዜ መጎብኘታቸው መሆኑ ይጠበቃል ። ኦባማ ከአመታት በፊት ሳውዲን ሲጎበኙ ባደረጉት ንግግር የገቡትን ቃል ባለመፈጸማቸው አሁን አሁን አረቦች ብዙም አይቀበሏቸውም ። ከመንግስታት ጋር ግን በመደጋገፍ ደረጃ ተቀባይነታቸው አልወረደም ።
ፕሬዚደንት ኦባማ በዚህ ጉብኝታቸው በመካከለኛው ምስራቅ ሸሪክ ሀገሮች ጋር በፖለቲካው ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ዋንኛ ትኩረት ያደርጉበታል ተብሎ የሚጠበቀ ው የሶርያ ጉዳይ ሲሆን የየመን ጉዳይ ይነሳል ! የኢራን ጉዳይም ይነሳል ! አረቦች
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓም

No comments:

Post a Comment