Tuesday, April 26, 2016

እንግሊዙ‬ ዕለታዊ ጋዜጣ 18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በድርቅ መጠቃታቸውን ገለጸ – የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች April 26, 2016 |



ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 25, 2016 NEWS)

‪#‎የእንግሊዙ‬ ዕለታዊ ጋዜጣ 18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በድርቅ መጠቃታቸውን ገለጸ
‪#‎በጋምቤላ‬ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በወጡት ዜጎች ላይ የወያኔ ወታደሮች ግድያና የአካል ጉዳት አደረሱ
‪#‎የግብጹ‬ ሲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደራጆችን አስጠነቀቁ
‪#‎በብሩንዲ‬ የተናጠል ግድያው እየቀጠለ መሆኑ ተነገረ
‪#‎የዳርፉር‬ ግዛት በአምስት አሰተዳድር ክልሎች እንድትከፋፈል ሕዝቡ አጽድቋል በማለት የሱዳን መንግስት መግለጫ ሰጠ

ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የእንግሊዙ ዕለታዊ ጋዘጣ ዘ ቴሌግራፍ የእርዳታ ድርቶችንና በመስክ ላይ ያሉ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ያለው ድርቅና ረሃብ ከ18 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን እያጠቃ መሆኑን ግልጽ አድርጓል። እስከ አሁን ድረስ በወያኔና በዕርዳታ ድርጅቶች በኩል የረሃብና የድርቁ ተረጅ ወገኖች ቁጥር እስከ 12 ሚሊዮን ይገመት እንደነበር ይታወቃል። በአዲሱ አሀዝ መሠረት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 20 ከመቶ የሚሆነው በአሁኑ ጊዜ የእርዳታ ፈላጊ አድርጎታል። የወያኔ ባለስልጣኖች የተረጅውን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ደፍረው ባያናግሩትም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ለረሃብና ለድርቁ የሚሰጠው ዕርዳታ ከተረጅው ቁጥር ጋር አይመጣጠንም በማለት አድበስብሰው ለማለፍ ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እየተነገረ ነው።
File Photo
File Photo

Ø በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች በመቶ የሚቆጠሩ ገድለው በመቶ በሚቆጠሩ ህጻናት አፍነው ከወሰዱና በሺ የሚቆጠሩ ከብቶችን ከነዱ ወዲህ በጋምቤላ ያለው ዘግናኝ እልቂት የዓለም ሕዝብ ዓይንና ጆሮ እየሳበ ነው። በጃዊ ስደተኛ ጣቢያ አቅራቢያ አንድ ኢትዮጵያዊ አሽከርካሪ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና አደጋ በማድረሰ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል በሚል ምክንያት በካምፕ ውስጥ የነበሩት ስደተኛች አብዛኞቹ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው የሚታወስ ሲሆን ድርጊቱን ለመቃወም አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የወያኔ ፖሊሶችና ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ ግድያና የመቁሰል አደጋ ማድረሳችው ታውቋል። ለተቃውሞ ከወጡት መካከል 5 መገደላቸውና ከ 15 በላይ መቁሰላቸው ተገልጿል። በጋምቤላ ውጥረቱ እየከረረ ሲሆን ቁጣውም እየባሰ መምጣቱ ይነገራል ወያኔ በስደተኞቹ ስም የሚሰጠው ገንዘብ እንዳይጓደልበት ጥቃቱን ችላ ከማለቱም በላይ እያባባሰው ይገኛል።
Ø በግብጽ በተለያዩ ቡድኖች የተድራጀና የተቀናጀ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ስልፍ መታቀዱን ተከትሎ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሲሲ ሰልፉን ለማስቆም በቴሌቪዥን ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። የግብጽ ሕዝብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ መዳከምና እንዲሁም የጸጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ በሚወስዱት አፈና ምክንያት መማረሩን በመግለጸ ተቃውሞ እያሰማ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት በግብጽ ቁጥጥር ስር ያሉ ደሴቶችን የሲሲ መንግስት ለሳኡዲ አረቢያ መስጠቱ ደግሞ ምሬቱ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል። የተለያዩ ቡድኖች የተቃውሞ ስልፍ ለማድረግ መወጣናቸው በመታወቁና ሰልፉም ሊያስከትለው የሚችለው ከፍተኛ ችግር ስጋት ስለፈጠረ ፕሬዚዳንት ሲሲ በይፋ ማስጠንቀቁያ መስጠት ተገደዋል። በንግግራቸው ላይ “የግብጽን መጥፋት የሚፈልጉ ኃይሎች እንደገና ጸጥታዋን ለማድፍረስ እየተዘጋጁ ነው ካሉ በኋላ የኛ ተግባር የህዝቡን ደህንነትና ጸጥታ መጠበቅ ስለሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። የጸጥታ ኃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የተሰማሩ ሲሆን ሰላማዊ ስልፎችን ያደራጃሉ፤ ግለሰቦችን ይቀሰቅሳሉ ብለው የሚገምቷቸውን ግልሰሰቦችን ጋዜጠኞችንና የህግ ባለሙያዎችን ከየቤታቸው በመልቀም ያሰሯቸው መሆኑ ታውቋል። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከ 1000 ሰዎች በላይ የተገደሉ ሲሆን ወደ 40 ሺ የሚገመቱ ሰዎች መታሰራቸውም ይነገራል።

Ø በብሩንዲ የተናጠል ግድያው እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ..ም የብሩንዲ ምክትል ፕሬዚዳንት የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል ካሩዛ እና ባለቤታቸው በመኪና ልጃቸውን ትምህርት ቤት ካደረሱ በኋላ ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ተነግሯል። ለድርጊቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም። ባለፈው ነሐሴ ወር የፕሬዚዳንቱ የግል የጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። እሁድ ሚያዚያ 15 ቀንም የብሩንዲ የሰብአዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከቤተክርስቲያን ሲወጡ ቦምብ ተወርውሮባቸው ሳይጎዱ በህይወት ሊያመልጡ ችለዋል። በብሩዲ በተለይ በከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች ላይ የሚካሄደው የተናጠል ግድያ የብሩንዲን ፕሬዚዳንት አስተዳደር እያናጋው ነው ተብሏል። የብሩንዲ የውስጥ ችግር ከጀመረ ጀምሮ ከ400 በላይ የሆኑ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።

በተያያዘ ዜና ሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በብሩንዲ እየተካሄዱ ባሉ ወንጀሎች ላይ ክስ ለመስረት አቃቤ ህጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናትና ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል። የመጀመሪያ ደረጃው ጥናት እንደተጠናቀቀ ሙሉ የሆነው የምርመራና ማስረጃ የማሰባብ ስራ የሚጀመር መሆኑና ጥፋተኛ ናቸው ተብለው የሚከሰሱ ሰዎችም ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተነግሯል።

Ø በዳርፉር ለሶስት ተከታታይ ቀኖች በተካሄደ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ አብዛኛው ሕዝብ ዳርፉር በአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መደገፉን የሱዳን መንግስት ገልጿል። በመንግስቱ መግለጫ መሰረት በተካሄደው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበው መካከል በምርጫው የተሳተፈው 97 በመቶ የሚሆነው እንደሆነ ሲነገር ድምጽ ከሰጠው መካከል ደግሞ 98 በመቶ የሚሆነው መራጭ ዳርፉር ለአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መርጧል ተብሏል። በርክታ ተፈናቃዮች ድምጽ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታና ኃይልና ማስፈራሪያ በሰፈነበት ሁኔታ የሚካሄድ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ እውነተኛ የሕዝብ ፍላጎት አያንጸባርቅም በማለት አማጽያኑ ኃይሎች ምርጫው እንዳይካሄድ አድማ ያደረጉ ሲሆን የምዕራብ አገሮችም የጸጥታው ሁኔታ ለነጻና ርቱዓዊ ምርጫ ምቹ ባለመሆኑ ምርጫው መካሄድ የለበትም ማለታቸው ይታወሳል። የሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ምርጫው የአረብ አገሮችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ባሉበት የተካሄደ በመሆኑ የሕዝቡን እውነተኛ ስሜትና ፍላጎት ያንጸባርቃል እያሉ ናቸው።

No comments:

Post a Comment