Sunday, April 24, 2016

በርካታ‬ መምህራን የስራ መልቀቂያ አቀረቡ ተባለ | የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 


ሚያዚያ 15 ቀን 2008 ዓ.ም
Ø በጋምቤላ ንጹሃን ዜጎች ድንበር ተሻግረው በመጡ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች እልቂት ከተፈጸመባቸው አንድ ሳምንት ባስቆጠረበትና በታጣቂዎቹ ታግተው የተወሰዱ ህጻናት ጉዳይ አሁንም ምንም ምላሽ ባላገኘበትና እንዲሁም ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ድርጊቱን አውግዞ ህጻናቱ አለምንም ቅደመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረበ ባለበት ሰዓት ደቡብ ሱዳናውያን አሁንም 14 ኢትዮጵያውያንን መግደላቸው ታውቋል። ግድያው የተፈጸመው ከጋምቤላ ከተማ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ጃዊ የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ መሆኑ የተነገረ ሲሆን መንስኤው አንድ ኢትዮጵያዊ ሹፌር በአንድ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና አደጋ በማድረሱ ነው ተብሏል። በአራቢያው የነበሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ለአደጋው ምላሽ በአቅራቢያው የነበሩ 14 ኢትዮጵያውያንን በጭካኔ ገድለዋል። በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት ደቡብ ሱዳናውያን ግድያውን የፈጸሙት በገጀራ በድንጋይ በቢላዋ መሆኑ ሲታወቅ አንድም የወያኔ ፖሊስ ሆነ ወታደራዊ ኃይል ወደ አካባቢው አለመላኩ ብዙዎችን አስገርሟል።
File Photo
File Photo
Ø ከአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በተገኘው መረጃ በመንግስት ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ሲያገለግሉ የነብሩ 1500 የአዲስ አበባ መምህራን የስራ መልቀቂያ አስገብተው 700 ያህሉ መሰናበታቸው ተገልጿል። መምህራኑ በሚደርስባቸው የፖሊቲካ ጫና የደሞዝ ማነስና ዓይን ያወጣ የዘር መድልዎ የተነሳ በመማር ማስተማሩ ሂደት መቀጥል ባለመቻላቸው ሥራውን ለመልቀቅ መገደዳቸው ታውቋል። መምህራን ወያኔ ባሰማራቸው የደህንነት መስርያ ቤት ባልደረባ ምመህራንና በወያኔ ስር በተደራጀ የወጣት ማህበራት ሰላዮች ክትትል እንደመደረግባቸው ታውቋል።
Ø የታንዛኒያ ባለስልጣኖች በታንዛኒያ የእስር ዘመናቸውን የጨረሱትን 74 ኢትዮጵያውያን በኬኒያ ድንበር ላይ በመጣላቸው በኬኒያ እና በታንዛኒያ መካከል ውዝግብ የቀሰቀሰ ከመሆኑ በላይ የኬኒያ ፖሊስ ስድስት ኢትዮጵያውያንን በህገ ወጥ መንገድ አገር ውስጥ ገብተዋል በማለት ማሰሩን አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም.በሰጠው መግለጫ ገልጿል።  እንደ ኬኒያ ፖሊስ ከሆነ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሞምባሳ በኩል አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊጓዙ ሲሉ በጥቆማ መያዛቸው ሲታወቅ ከስደተኞቹ ጋር አንድ የኬኒያ ሹፌርም አብሮ ተይዟል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ኬኒያ በመግባት ወንጀል ሲከሰሱ የኬኒያው ሾፌር ደግሞ ስደተኞችን በማስረግ ወንጀል እንደሚከሥ ተጠቁሟል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በብዙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የከፋ መከራና ስቃይ ይደርስባቸው እንደነብር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ስደተኛነታቸው እንደ ጥፋት እየተቆጠረ መታሰር እየተለመደ በመጣቱ ድምጽ አልባ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁሉም ወገን በሚችለው አቅሙና መንገድ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ኤጄንሲ እንዲያሳውቅ ሀገር ወዳድ ዜጎች ጥሪ ያቀርባሉ።
Ø የሶማሊያው አልሸባብ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓም ስድስት የወያኔ ወታደሮችን መንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጅ መግደሉን አስታውቋል። የፈንጅ አደጋውን በደቡባዊ ባይ ግዛት ውስጥ አውደሊን ከተማ አቅራቢያ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በጥቃቱ ወቅት የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ያሰማራቸው ሰላም አስከባሪ በወታድር አጀብ ይጓዝ እንደነበረና ከሞቱት የወያኔ ወታደሮች ውስጥ ከፍተኛ አዛዦች እንደሚገኙበት አብራርቷል። በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል አልሸባብ አደረስኩ ስለሚለው ጥቃት የተናገረው ነገር የለም። የወያኔ አገዛዙም እንደተለመደው የተነፈሰውና ያለው ነገር አልተመዘገበም።
Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሚስተር ሪክ ማቻር ቅድሜ ሚያዚያ 15 2008 ዓ.ም.  ጁባ እንዲገቡ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሰጠውን ቀነ ቀጠሮ አሁንም ያልተከበረ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዓመት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ሚስተር ማቻር ጁባ እንዲገቡ ታቅዶ የነበረው ሚያዚያ 10 ቀን 2008 መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አጅበው በሚገቡ ወታደሮች ብዛት ላይ እና ሊይዟቸው በሚችሉ የመሳሪያ ዓይነቶች ላይ ከሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ስምምነት ባለመደረሱ ጉዟቸው የዘገየ መሆኑ ተነግሯል፡፤ ትናንት አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓም በነፍስ ወከፍ ኤኬ 47 አውቶማቲክ መሳሪያ ከታጠቁ 190 አጃቢዎች  እና 20 መትረየሶችና ከ20 አርፒጂ ጋር እንዲገቡ ስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር እንደገለጹት ሚስተር ሪካ ማቻር የሚጓዙበት አውሮፕላን ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚፈቀድለት ከጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ከመነሳቱ በፊት የሚመጡት ሰዎች ቁጥርና የያዙት መሳሪያ በስምምነቱ መሰረት መሆኑን የዓለም አቀፍ ድርጅት አባላት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ ብቻ ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እንዲሁም አሜሪካ እንግሊዝ እና ኖርዌይ ሚስተር ሪክ ማቻር እንዲመለሱ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተነግሯል።

Ø በግብጽ የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሀመድ ሞርሲ የካታር መንግስት ሰላይ ናቸው በሚል ቀርቦባቸው የነበረው ክስ ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን ሊታይ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ዝግጅት ያስፈልጋል በሚል ለሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም.  ያስተላለፈው መሆኑ ተነግሯል። ካታር የሚስተር ሞርሲን አስተዳደርና የግብጽን የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ስትረዳ መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን  የፕሬዚዳንት ሲሲ አስተዳደር ካታር በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች በሚል ክስ ትታሰማ መቆየቷም ይታወቃል። በፕሬዚዳንት ሲሲ እና በተባባሪዎቻቸው አማካይነት በተካሄደ ወታድራዊ መፈንቅለ  መንግስት በስልት ከስልጣናቸው የተነሱት ሞርሲ ከዚህ ቀደም በሶስት የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የሞት ፍርድ፤ የእድሜ ልክ እስራትና የሃያ አመታት እስራት የተበየነባቸው መሆኑ ሲታወቅ ይህኛው ክስ አራተኛው መሆኑ ነው። ሞርሲ እና ሌሎች አስር ሰዎች የግብጽ የጸጥታ ሁኔታን የሚመለከቱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብለው ከካታር ሸጠዋል የሚል ክስ አቃቤ ህጉ ያቀረበባቸው መሆኑ ታውቋል።

Ø በዚህ ሳምንት በማሊ በአማጽያን ታግተው የነበሩ ሶስት የቀይ መስቀል ሠራተኞች አለምንም ቅደመ ሁኔታ የተለቀቁ መሆናቸው ተነገረ። በሰሜን ማሊ የሚንቀሳቀሰውና ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው አንሳር ዲን የተባለው ድርጅት ባለፈው ሐሙስ በሰጠው መግለጫ ሰራተኞቹን ያገተው ድርጅቱ መሆኑንና ሊፈቱ የሚችሉት በፈረንሳይ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ያለው ሚያቴን አግ ማያሪስ የተባለው የድርጅቱ አባል ሲፈታ ብቻ መሆኑን ገልጾ እንደነበር ይታወሳል። አርብ ዕለት ታግተው የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች መለቀቃቸው የተነገገረ ሲሆን ሊለቀቁ የቻሉትበፈረንሳይ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው ግለሰብ ስለተለቀቀ ይሁን አይሁን አልታወቀም። ሰላም በማስከበር ስም ፈረንሳይ በሰሜን ማሊ ከ3500 በላይ የሆኑ ወታደሮች እንዳላት ይታወቃል።

Ø በምስራቅ ሊቢያ ራሱን መንግስት ነኝ የሚለው ክፍል ፓርላማ በተመድ አማካይነት የተቋቋመውን መንግስት ለመደገፍ ውደ ኋላ ሲል መቆየቱ ይታወሳል። ባለፈው ሐሙስ 198 ከሆኑት የምክር ቤቱ አባላት መካከል 108 የሚሆኑት የአንድነት መንግስቱን መደገፋቸውን በመግለጽ መግለጫ ያወጡ ቢሆንም በዙዎቹ በግል ማስፈራሪያ ስለደረሳቸው ድምጽ ሊሰጥበት የሚችል ስብሰባ ማካሄድ ያልቻሉ መሆኑ ተገልጿል። አርብ ሚያዚያ 14 ቀን የምዕራብ መንግስታት አምባስደሮች በሰጠቱ መግለጫ ማስፈራሪያውን በጽኑ አውግዘው አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት የተደረገባቸውን ተጽእኖ ተቋቁመው ድምጻቸውን ለማሰማት መቻላቸውን አወድሰዋል። ምከር ቤቱ ተሰብቦ ውሳኔዎችን በህጋዊ መንገድ እንድያስወስንም ተማጽነዋል።

No comments:

Post a Comment