Tuesday, April 19, 2016

በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ከመላው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል | ነገ ጠዋት የዪኤስ ኮንግረስ የኢትዮጵያን ጉዳይ ያዳምጣል




(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሕወሓት በሚመራው መንግስት የተወሰዱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ነገ ማክሰኞ ጠዋት በዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ገለጻ እንደሚደረግ ታወቀ:: ይህን ተከትሎ በአሜሪካ እና በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቶም ላንቶስ ሂውማን ራይት ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ አጭር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደዋሽንግተን ዲሲ እንዳመሩ ታውቋል::
በዚህ አጭር ጉባኤ ላይ በፓናሊስትነት ተገኝተው ገለጻ የሚያደርጉት የኦክላንድ ኢኒስቲትዩት መስራችና ዳይሬክተር አኑራዳ ሚታል; የአልጀዚራ አሜሪካ ጋዜጠኛ ማህመድ አደሞና የአሜሪካው አመነስቲ ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አዶሲ አከዘ-ሐበሻ መቀመጫ ሚኒያፖሊስ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሲያመሩ በኤርፖርት ተገኝተን የተመለከትን ሲሆን ከሌሎች ከ30 የማያንሱ ስቴቶችም እንዲሁ በዚሁ ዝግጅት ላይ ለመታደም እና አጋርነታቸውን ለማሳየት እንዳመሩ ዛሬ ማምሻውን በዋሽንግተን ዲሲ እየተደረገ ባለው ስብሰባ ላይ ተገልጿል::
በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ ፖይንት ሆቴል ስለነገው የኮንግረሱ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰ አዊ መብት ጥሰት የሚያዳመጥበት አጭር ጉባኤና ያንን ተከትሎም ስለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ከየ ስቴቱ ለመጡ ኢትዮጵያውያን ገለጻ እየተደረገ ነው:: በተለይም በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት የተውጣጡ ወገኖች በዚሁ ስብሰባ ላይ በመገኘት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲነጋገሩ አምሽተዋል::
የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ነገ ማክሰኞ ኤፕሪል 19, 2016 የሚያደምጥበት አጭር ጉባኤ የሚጀመርበት ሰዓት ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ታውቋል:: ከዚያ ቀደም ብሎም በ9 ሰዓት ለጋዜጠኞች ገለጻ ይሰጣል ተብሎ ቀጠሮ ተይዟል:: ይህ አጭር ጉባኤ እንደተጠናቀቀም ከዋሽንግተን ዲሲ ካፒቶል እስከ ኋይት ሃውስ የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ይኖራል ተብሏል:: ሰላማዊ ሰልፉም ከቀኑ በ1:00 ሰዓት እንደሚደረግ የተያዘው መርሃ ግብር ያስረዳል::
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ለማቅረብ ትሞክራለች::
Share2  1635  1 
 Share5

No comments:

Post a Comment