Tuesday, April 26, 2016

በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ወጣቱ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው ለኩላሊት ሕክምና የሚሆን ገንዘብ በኢንተርኔት እየተሰባሰበ ነው


0

አቶ ሃብታሙ አያሌው
አቶ ሃብታሙ አያሌው
(ዘ-ሐበሻ) የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት በ እስር ቤት ከቆየ በኋላ በቅርቡ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የተፈታው የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌው በ እስር ቤት እያለ የጀመረው የኩላሊት እና የሄሞሮይድስ በሽታ እየጠናበት በመሄዱ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ በኢንተርኔት እየተዋጣ መሆኑ ታወቀ::
“ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ…” በሚል መርህ ወጣቱን ታጋይ ሃብታሙ አያሌውን ሕይወት ለማትረፍና በተለይም እያሰቃየው ካለው የሁለቱም የኩላሊት ሕመሙ እንዲድና ይህም ለከፋ ሁኔታ ሕይወቱን ከማጋለጡ በፊት የተጀመረው የኢንተርኔት ገንዘብ ማሰባሰብ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ $6500 መድረሱ ታውቋል:: ይህን በጎ ተግባር ላይ ከሚገኙት የዘ-ሐበሻ ድረገጽ አዘጋጆች መረጃ ማግኘት እንደተቻለው ለሃብታሙ አያሌው የህክምና ወጪ ሕዝብ እንዲያዋጣ የታሰበው ከ$30,000 በላይ ነው::
ሃብታሙ አያሌው ከሁለቱም ኩላሊቶቹ ህመም በተጨማሪም በሄሞሮይድስ ህመምም እየተሰቃየ ሲሆን በአስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው በመሆኑ ሕዝብ ማንኛውንም የፖለቲካ ልዩነቱን ትቶ በሰብአዊነት ሕይወቱን ለማትረፍ እንዲሯሯጥና ያለውን እንዲያዋጣ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::
በኢንተርኔት በሚከተለው ሊንክ ውስጥ በመግባት ገንዘብ ማዋጣት የሚቻል ሲሆን ስማቸውን መጥቀስ የማይፈልጉም የብዕር ስም መጠቀም እንደሚችሉ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
ከሊንኩ በታች የሃብታሙ አያሌውን ንግግር ከስር አስቀምጠነዋል:: ዛሬውኑ የተቻለዎትን በማድረግ ይህን ወጣት ሕይወት እንታደገው::
እዚህ ጋር ገብተው ይርዱ>>>>>>> https://www.gofundme.com/2zgseemk

No comments:

Post a Comment