አቤል አሜሪካ የመጣው የ5 ልጅ እያለ ነበር። ትምህርቱን ቀጥሎ በወጣት አፍላነት እድሜ ሲደርስ አብራው ትማር ከነበረች ሀበሻ ፍቅር ይጀምራሉ። ልጅት በድንገት ፅንስ ትቋጥርና ትወልዳለች። ቆንጆዎቹ ሀበሻ ጥንዶች በልጅ ታጅበው ፍቅራቸውን ይቀጥላሉ።
አቤል ከ12 አመት በፊት ኢትዮጵያ ያመራል። የአሜሪካና ኢትዮጵያን ባህል ሲመለከት ውስጡ ይነካል። ገዳማትና ቤ/ክርስቲያ ይዞርና የፈጣሪን መንገድ ይይዛል። አቤል ከተመለሰ ከአመት በኋላ ልጅ የወለደችለት ፍቅረኛው ሄለን ወደ አገር ቤት ታመራለች። በሚኒባስ እየሄደች መኪናው ተገልብጦ ህይወቷ ያልፋል። አቤል ሲናገር “ፍቅሬን አፈር አለበስኳት። ወደመቃብር ስትወርድ ፍቅርና መውደዴን ይዛው ሄደች። አብሬ ቀበርኩት። 10 አመት አንድ ሴት ሳልቀርብ የብቸኝነት ኑሮ እገፋለሁ። በየአመቱ አገር ቤት እየሄድኩ መቃብሯን እጎበኛለሁ። እግዚአብሔርን ማወቅ በጀመርኩ ማግስት ፍቅሬን ነጠቀኝ። ግን እምነቴን አልተውኩም! በወጣትነቴ ተጎዳሁ። ልጄን ባየሁ ቁጥር ፍቅሬ ድቅን ትላለች! የፍቅር ቁስሌን ለብቻዬ አስታምማለሁ!”
ሀዘን በሸረሸረው ገፅታ በዝምታ ተመሰጠ። በግምት 29 አመት እድሜ የሚሆነው አቤል የ10 አመት የብቸኝነት ህይወቱ ያሳዝናል! በእንባና ሀዘን የተከበበ ህይወት!
No comments:
Post a Comment