Friday, April 22, 2016

ይህችን ቀን ማን ይረሳል!!!! – ጠና ዪታየው


 


ሸክማችን ቢከብድም ዓመቱ እንደጉድ ይሮጣል። በየዓመቱም ዜጎቻችንን ለሞት ለእስርና ለእንግልት እየሰጠን መሪ ባውጣን በነጋታው ለአውሬው ስርአት እየገበርን፣ ስርአቱን ከመታገል ይልቅ ከሰማይ አንዳች ነገር ወርዶ ይህንን ስርአት እንዲገነድስልን የውሸት ጸሎት እየጸለይን መኖርን ትርጉም እንዳለው ነገር ቆጥረን ትላንት በዛሬ እየተካን ሸክማችንም ከቀን ወደቀን እየከበደ እንዲሁ እንዳለን 2007 ዓ.ም ሚያዚያ 14 በ2008 ዓ.ም ሚያዚያ 14 ተተካ። በሚያሳዝን ሁኔታ ለሚያዚያ ወር የሰው ግብር የተሳልን ይመስል ዘንድሮም የሰውን ቁጥር ጨምረን ለንሱ ብዙ ሰው ገብረን አሳለፍነው። እግዚኦ!!! የተነሳሁበት ዋናው አላማየ ስለዚህ ወር ለማውራት ሳይሆን በዚህ ወር መንግስት( ወሮ በላ የሚሏቸውም አሉ) ስለፈጸመብን ነውረኛ ተግባር እና ስለተፈጸመባቸው ጓዶቻችን ጥቂት ለማስታወስ ነው። አወ ይህችን ቀን ማን ይረሳል እርጉም ሚያዚያ 14። በዚህ እለት መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝተው ለእስር ለእንግልት ለድብደባ የተጋለጡትን መዘርዘር ከባድ ቢሆንም የምናውቃቸውን እንዲህ እንዘረዝራቸዋለን። የሰማያዊ ቆራጥ ወጣቶች በጥቂቱ እነሆ
1. ወይንሸት ሞላ ታስራ የተፈታች
2. ብሌን መስፍን በገደብ የተፈታች
3. ሜሮን አለማየሁ ቅጣት ጨርሳ የተፈታች
4. ንግስት ወንድይፍራው ቅጣት””””
5. ናትናዔል የአለምዘውድ በእስር የሚገኝ
6. ማቲያስ መኩሪያ በእስር የሚገኝ
7. ተዋቸው ዳምጤ በእስር የሚገኝ
8. ቴወድሮስ አስፍው በእስር ላይ ያለ
9. ኤርሚያስ ፀጋዬ በእስር ላይ ያለ
10 ዳንዔል ተስፋዬ በእስር የሚገኝ
11 ፍሬው ተክሌ በእስር የሚገኝ
12 ምእራፍ ይመር በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ ህክምና ገብታ ከእስር የተረፈች
13.እኔ ራሴ ለውሸቱ ምርጫ በተሰጠኝ ተወዳዳሪነት መብት ከእስር ተርፌያለሁ
14. ይድነቃቸው አዲስ ለውሸቱ ምርጫ በተሰጠው ተወዳዳሪነት መብት የተረፈ
15 እስክንድር ጥላሁ ” ” ” ”
16 ስንታየሁ ቸኮል እስሩን ጨርሶ የተፈታ
17.ደሳለኝ ፈቃዴ ታስሮ የተፈታ
ከሰማያዊ ፓርቲ ውጭ እኔ የማውቃቸው እና የሌሎች ፓርቲ አባላት
1.አለነ ማህፀንቱ
2 ዳዊት አስራደ
3.ዘመነ ምህረቱ
4. ማሙሸት አማረ
የማስታውሳቸውን እንዲህ ዘርዝሬያለሁ። በነገራችን ላይ በዚያ ሰልፍ ጣጣ ብዙወች ከስራ ተባረዋል። መንቀሳቀስ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እርጉም ሚያዚያ 14። ወንበዴው መንግስታችንም ከ1000 በልይ ሰወችን አስሬያለሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment