Saturday, April 16, 2016

መንቃት ያለብን ወሳኝ ወቅት – የምንፈልገውን ነጻነት ለማረጋገጥ ጊዜው በፍጹም አረፈደም !!!

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደተምኔት ሳይሆን እንደተጨባጭ ነገር ማስተዋል ይገባናል፡፡ ፅንፍና ፅንፍ እየቆሙ፣ ማዶና ማዶ የጎሪጥ እየተያዩ፣ በደፈረሰ ልብ እያሰሉ፣ የምንመኘውን ዓይነት ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ከቶውንም፤ በትንሹ የምንመኛቸውን ነገሮች እንኳ በእጃችን ማስገባት አዳጋች ይሆናል፡፡
Minilik Salsawi's photo.
እንደሶስተኛው ዓለም ባለ አገር፤ ከፍስኩ ፆሙ ይበዛል። ዲሞክራሲን ከፈሰከው የፆመው ይበዛል፡፡ ፍትህን ካየው ያላየው ይበዛል፡፡ ሀቅን ካገኘው የፆመው ይበረክታል። መልካም መስተዳድርን ከተጎናፀፈው የተራቆተው ይበዛል፡፡ ዞሮ ዞሮ መፆም ተለምዶ ፍስክን አርቆ ማየት ልክ እየመሰለ መጥቷል፡፡ መንገድ ከመጀመራችን በፊት የመንገዱን እርቀት እንመትር ቢባል የሚሰማ ጠፍቷል – ከሁሉም ወገን! አንዴ “እናሸንፋለን”፤ ካሉ “ተነጋግረን እንስማማለን” “እንደሰለጠነ ሰው ተቀራርበን እንፈታዋለን” ማለት እርም ሆኗል፡፡ ስለአገር ምን አገባን”፣ “ስለህዝብ ምን አስጨነቀን?” ማለት ወግና ልማድ የሆነ ይመስላል – በተግባር የለምና!
የምንፈልጋቸውና የምንጓጓላቸው ነገሮች ጥቂት፤ የምንፈራቸው ግን ብዙ ሲሆኑ፣ የአዕምሮ ደረጃችን ጎስቋላ ሆነ ማለት ነው፡፡ግባችንን በውል ለመምጣት የእኛን መንገድ ብቻ “አንደኛ ነው!” የእነ እገሌ ውራ ነው” እያልን በአፈ ቀላጤዎቻችን ብናወራ ራስ-በራስ መሸነጋገል እንጂ ሁነኛ ፍሬ የሚያፈራ ጉዞ አይሆንም፡፡ ምንጊዜም ሁሉም የየራሱን እንቅፋት መደርደሩ አይቀርም፡፡ በየዘመኑ የምናየው ነው፡፡ የበላይም ይናገር የበታች ለሀገራችን የሚጠቅመው መደማመጥ ነው፡፡ በአንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሚኬድበት መንገድ አንሁን፡፡ የሚነገረንን እንስማ፡፡ ሌላው ሰው ድንገት ከእኔ የተሻለ ሀሳብ ቢያቀርብስ? እንበል፡፡ የመጨረሻዋን ነጠብጣብ ጭማቂ ሂሳብ የሚያሰላ ሰው ባገኘን እንዴት በታደልን ስንቱ በተጋለጠ! በጋራ እና በአንድነት በመቆም ብዙ ስራዎችን መስራት እንዲሁም ዋና ጠላታችን የሆነ ወያኔን ደምሥሰን ለውጥ ማምጣት እንደምንችል በማወቅ ለጋራ ጉዞ መንቃት ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ ነን:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment