Thursday, April 21, 2016

ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA



ሚስትና ልጁን ያጣ፣ እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣ እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ እማኞችን አነጋግሮ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
ከዚህ አደጋ የተረፉት 41 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ሃይል ተርፈው ወደ ግሪክ ተሻግረው ነበር። የአውሮፓ ህብረትና የግሪክ መንግስት በአሁኑ ሰዓት ስደተኞችና ፍልሰተኞች በመበራከታቸው፤ ወደየሃገራቸው እንዲመለሱ ማዘዣ እየሰጡ ነው።
ሶሪያዊያንም ወደ ቱርክ ወደሚገኝ የስደተኞች ጣቢያሲመለሱ ቆይተዋል። ጽዮን ግርማ ከጀልባ አደጋ በህይወት ተርፈው ግሪክ ከገቡ መካከል ጥቂዎቹን አነጋግራለች

No comments:

Post a Comment