Monday, April 18, 2016

April 18, 2016 | Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: Zehabesha Share0 164 0 Share0 ፍካሬ ዜና



ሚያዚያ 9 ቀን2008 ዓ.ም.
 የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በተለይም ካታር በአሰብ የባህር የጦር ሰፈር እየሰእራች ለመሆኗ በቂ ማስረጃ ተገኝቷል ያሉ ክፍሎች በወደቡ የሚገኙት የኤሚራቷ መርከቦች ብቻ ሳይሆኑ የሌላም ሀገር መርከቦች ታይተዋል ብለው አያይዘውም ሳውዲ አረቢያ ልትሆን መቻሏን ጠቁመዋል ፡፡ ሳውዲና ቃታር በኤርትራ ጦር ሰፈሮች መሰጠታቸውን፤ ቃታር አሰብን መግዛቷን የተነገረ ሲሆን ሳውዲን ለመርዳት ወደ የመን ወታደር የላከው ሻዕቢያ ግን ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወቃል ።ሻዕቢያ ኤርትራን ለሳውዲና ካታር መሸጡ ለኢትዮጵያ እያመጣ ያለውን አደጋ ሕዝብ በግምት ማስገባትና መጠንቀቅም አለበት ተብሏል ።
 የሀገርን ህልውና በአደጋ ከሚጥሉት አንዱ ሁኔታ ግብጽን የሚመለከት መሆኑ ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን በቅርቡ እየጠነከረ የመጣው የግብጽና የሳውዲ አረቢያ ወዳጅነት ደግሞ አካባቢያችንን ለከፍተኛ አደጋ መጣሉ እየተነገረ ነው ። ግብጽ ሁለት ደሴቶቿን ለሳውዲ መለገሷን በመቃወም የግብስ ተራማጅና ዴሞክራቶች ተቅውሞ እያሰሙ መሆናቸው ም ታይቷል ።ሳውዲ ቀደም ስትል ጸረ ሲሲ የሆኑትን የሙስሊም ወንድማማቾች ስትረዳ የቆየች ቢሆንም በአሁኑ ጊዜከግብጹ አምባገነን አል ሲ ጋር መዛመድን መምረጧ ይታያል ። የሳውዲ ጥቃት በየመን ላይ፤ ሳውዲ በጦር ደረጃ ወደ ኢርትራ መግባት፤ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ያላት ጣውንትነት–ይህ ሁሉ መጪውን አደጋ ይጠቁማልም ተብሏል ።በቅርቡ በአዲስ አበባ የግብጽ አምባሳደር ልዑክ ይዞ የበርበራ ወደብ የሚገኝባትን ሶማሊላንድን መጎብኘቱና ከመሪዎቹ ጋር መገናኘቱ ም አንደምታው አስጊ ነው መባሉም ተጠቅሷል ።

አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን መንግስት ወታደሮችና የሙርሌ ጎሳ አባላት ታጣቂዎች በአንድ ላይ ወደኢትዮጵያ ግዛት ገብተው 10 የሚሆኑ መንደሮችን ማጥቃታቸውና 170 የኑዊር ጎሳ አባላትን መግደላቸውን ሱዳን ትሪቡን የተባለው ጋዜጣ በአርብ ዕለት እትሙ ዘግቧል። ከተገደሉት ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸው ተነግሯል። የተገደሉት የኑዌር ጎሳ አባላት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በወረራው ወቅት የሚደርስላቸው ኃይል ባለመኖሩና መሳርያ አልባ በመሆናቸው ሊጠቁ ችለዋል ተብሏል። ዘግይቶ በደረሰው ዜና የተገደሉት የተገደሉት ዜጎች ከ200 በላይ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ያለ ሲሆን ህጻናት ታፍነው የተወሰዱ መሆናቸውም ተነግሯል:: በግጭቱ ቢያንስ 51 የሚሆኑ የሙርሌ ጎሳ አባላትም የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል።
 እውቁ የማሲንቆ ተጫዋችና ድምጻዊው ጌታ መሳይ አበበ በተወለደ በ 72 ዓመቱ በዚህ ሳምንት ማረፉ ተነግሯል። አርቲስት ጌታ መሳይ ከልጅነቱ ጀምሮ በሙዚቃና የኪነት ላይ የነበረ ሲሆን በአዲስ አበባ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የባህል ማዕከል በኋላም በሀገር ፍቅር ትያትር በሙዚቀኛነት በድምጻዊነት አገልግሏል። የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አምባሰደር በመሆንም በተለያዩ የዓለም አገሮች በመዘዋወር በማሲንቆ ተጫዋችነትና በድምጻዊነት ተመልካቹን ሲያስደስት ቆይቷል ። አርቲስት ጌታ መሳይ አበበ በሕይወት ዘመኑ ከ 200 በላይ ዜማዎችን የተጫወተ ሲሆን ከአስር በላይ ትያትሮችንም በመድረክ ላይ ከውኗል። በኪነት ዓለም ውስጥም በማሲንቆ ተጫዋችነት በድምጻዊነት በመህርነትና በኃላፊነት አስተዋጽኦ ያደረገውና የኢትዮጵያን ባህል በዓለም ያስተዋወቀው አርቲስት ጌታ መሳይ አበበ ከ 966 ዓ ም ድምጽ ባደረበት የጭንቅላት ህመም የተነሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የኮሚፒዩተር ግንኙነቶችን ለመቆጣጠር አዋጅ ሊወጣ መሆኑ ታወቀ
 ወያኔ በእጅ ስልክና በኮምፒዩተር የሚደረጉ የጽሁፍና የድምጽ ግንኙነቶች ላይ እስከ ዛሬ እያካሄደ ያለውን ህገ-ወጥ ስለላ ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ረቂቅ አዋጅ ለወያኔ ፓርላማ መቅረቡ ታውቋል፡፡ በዚህ ፀረ-ሕዝብ አዋጅ በኮምፒዩተር ሕዝብን ለፀረ-ወያኔ ትግል የሚያነሳሳ ጽሁፍና ተንቀሳቃሽ ምስል ያሰራጨ፣ የወያኔን የሚስጥር ቁልፎችን ሰብሮ በመግባት የጠለፈ፣ የፖሊስ፣ የደህንነት፣ የመከላከያ ኃይሉን ሰነዶች ጠልፎ ያጋለጠ በሃያ አምስት አመታት እስራት የሚያስቀጣ አዋጅ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ወያኔ የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሀሳብን በነፃነት በጽሁፍም ይሁን በንግግር የመግለጽ መብቶች ሙሉ በሙሉ ማፈኑ ይታወቃል፡፡ ይህ የኮምፒዩተር ግንኙነቶችን ለመግታት ሆን ተብሎ የታለመና አገሪቱን እስካሁን ካለችበት የጨለማ ሁኔታ ወደ ፍጹም ደይን የሚወስድ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡
ኢትዮጵያ በመረጃ ልማት ሰንጠረዥ የመጨረሻ ሶስተኛ ቦታ ላይ እንደምትገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ግልጽ አድርጓል። የኢንፎርሜሽን ዲቨሎፕመንት ኢንዴክስ ባለፈው ዓመት በ1967 የዓለም አገሮች ያደረገውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ጥናቱ በየአየገሮቹ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ስፋትና ጥራት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭትና ኔትወርክ የማግኘት አቅም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትን ለኢንተርኔት የደረሱ ዜጎች ቁጥርን ግምት ውስጥ ያስገባ እንደነረ ሲታወቅ በውጤቱ በሰንስጠረዥ መጨርሻ 167 ኛ ያወጣቸው ቻድ ስትሆን 166ኛ የሻዕቢያዋ ኤርትራ 165 ኛ ደግሞ ወያኔ በዘረኛንት የሚገዛት ኢትዮጵያ ሆናለች በጥናቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጆ ለዜጎቻቸው በአስተማማኝ መንገድ ብቻ ሳይሆን በጥራት በማቅረብ ኮሪያ ቀዳም ስትሆን ዴንማርክና አይስላንድ አንደ ቅደም ተከተላችው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በጥፋቱ ሰንጠረዥ ትናንት ነጻነት አገኘሁ ያለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ በልጣና ተሽላ መገኘቷዘረኛዎቹ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሸርቡን ደባ ሸርና በግልጽ አሳይቷል።
በተያያዘ ዜና የወያኔ ቡድን ባለስልጣኖች በከፊል ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ በደቡብ አካባቢ ለሚገኘው ተጠቃሚ የትዊተር የዋትስ አብፕ ና የሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ዘግቶ የነበረ መሆኑ ብሉመርግ የተባለ የዜና ወኪል አጋልጧል። የወያኔ አገልጋይ የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒከሽን መስሪያ ቤት የአገሪቷን የኢንተርኔት አገልግሎት በሞኖፖል የያዘ ሲሆን ተቀጣጥሎ ከተያያዘው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የኢንተርኔት አገግልጎትን በተለይም የሞባይል አገልግሎት ለመግዛት ማቀደቀዱ ቀደም ብሎ የተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣኖች የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆን ነው እንጅ ሆን ተብሎ የተወሰደ የመንግስት እርምጃ አይደለም ብለው በማለት መግለጫ ለመስጠት ቢሞክሩም አፈናው እንቅስቃሴውን ለማዳከም የተጠቀሙበት እርምጃ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑና ብሶት የገፋፋው የሕዝብ አመጽ በማናቸውም ዓይነት አፈና ሊዳከም እንደማይችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ወያኔ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ምዝገባ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ
 ወያኔ ዓለም አቀፍ የሆነውን “ቫይበር” የተሰኘውን የነጻ የስልክ መደወያና መቀበያ አገንግሎትንና እንደ “ኋትስ አፕ” የተሰኙት የነፃ የአጭር መልዕክት መላኪያዎችን ማስከፈል የሚያስችለውን መሳሪያ እንደገጠመና በቀርቡ በተግባር እንደሚያውል ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ምዝገባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለማካሄድ እንዳቀደ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ድርጊት ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ስልኮች ላይ ቀረጥ በመጣል ለማስከፈል እንደሆነና ከዚህ በተጨማሪም በተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ላይ የሚደረገውን ክትትል ጠበቅ ለማድረግ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ይህንን ምዝገባ የማያኬሄድ ማንኛውም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ሲም ካርዱ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ይደረግበታል፡፡ ይህንን ሁኔታ በአንክሮ ያጤኑ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ይህ የወያኔ ዘመቻ በመጀመሪያ ደረጃ እየበረታበት በመሄድ ላያ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማዳከም ሲሆን በተጓዳኝም ከደረሰበት የገንዘብ ኪሳራ ለማንሰራራት እንዲረዳው ታስቦ የተደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ድረ- ገጾች ማለትም የኢሕአፓን፣ ደብተራውን፣ አሲምባን፣ እንዲሁም የሌሎች ድርጅቶችንና ፀረ-ወያኔ የሆኑ ድረ-ገጾችን በቻይናዎቹ አጋሮቹ መዝጋቱ የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በተላይት የሚሰራጩ የቴሌቪዥንና የሬድዮ እንደ ፍኖተ ዲሚክራሲ የመሳሰሉትን ማዘጋቱ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ንግድ ላይና ጥገና ላይ የተሰማሩ እንደሚያስረዱት እንደ አይ ፎንና የመሳሰሉ ስልኮች ለመጥለፍ አስቸጋሪ በመሆኑና የቻይናው ሁዋዌ ተንቀሳቃሽ ስልክ በቀላ ሊጠለፍ ስለሚችልና ለኩባንያው ገበያ ለመክፈትና የጥቅሙ ተጋሪ ለመሆን የታለመ መሆኑን አበክረው ያስረዳሉ፡፡
ድርቁ እየከፋ በመሄድ ላይ መሆኑ ተጋለጠ
 ይህ በወያኔ የዘር ፖለቲካና የኤኮኖሚ ስርዐት ሳቢያ የተከሰተው ድርቅና ርሀብ እንደ ቆላ ሰደድ እሳት መላ ሀገሪቱን እያዳረሰ ይገኛል፡፡ ከወሎና ከትግራይ ርሀብ ከጎጇቸውና ከቀያቸው ያሳደዳቸው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ርሀብተኞች በደብረብረብርሀን ከተማ በየቤቱ እየዞሩ ቁራሽ እየለመኑ ህይወታቸውን እየታደጉ እንደነበር ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ ይሀ ሁኔታ መልከ ጥፉው ወያኔ ሁኔታው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊያስነሳበት እንደሚችል በመስጋት ርሀብተኞቹን እያፈሰ የሚላስ የሚቀመስ ወደ ሌለበት ቀያቸው መልሷቸዋል፡፡ ርሀቡ በጂግጂጋ፣ በቀብሪደሀር፣ በቀላፎ፣ በሽንሌ፣ ከዘጠና አምስት ከመቶ በላይ ከብቶችን ፍጅቷል፡፡ ሴቶችና ህፃናት በጠኔ እየተሰቃዩ መሆናቸውን እርዳታ ከሚሰጡ ድርጅቶች ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ጥረት ያደረጉ ከወሎ የተሰደዱ ረሃብተኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ተከልክለው በፖሊስ ተወስደዋል። በዘንድሮ ድርቅና ረሃብ የተጎዱና ዕርዳታ ማግኘት ባለማቻላቸው ወደ አዲስ አበባ በስደት ያቀኑ ተረጅዎች አዲስ አበባ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸው ታውቋል። ለመከልከላቸው ዋና ምክንያት የሆነው የወያኔን ገጸታ ታበላሻላችሁ የሚል ነው።
በዚህ ሳምንት ተመድ ይፋ ባደረገው መግለጫ በኢትዮጵያ አሁን የዕርዳታ ፈላጊው ቁጥር ወደ 20 ሚሊዮን መጠጋቱና ይህ አሀዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት አንድ አምስተኛውን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል። በረሃብና በድርቅ የተጎዱት አካባቢዎች ከ186 ወደ 219 ክፍ ያሉ ሲሆን ተረጅዎችም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በአንዳንድ አካባቢ ስደት መጀመሩና በዚህ ከቀጠለ የረሃብ አደጋ ዕልቂትን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመሆን በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ኢትጵያውያንና በጦርነት ለተጎዱ ሶርያውያን 2.2 ሚሊዮን ዕርዳታ እየተማጸኑ ሲሆን 480 ሚሊዮን ዶላር በድርቁና በረሃንብ ሳቢያ ጤንነታቸው ለተዛባ ኢትዮጵያውያንና በጦርነት ለተጎዳ ሶርያውያን ይውላል ተብሏል። የወያኔ ባለስልጣኖች በወደብ የተከማቸ የእርዳታ እህል ለማንሳት ከመረባረብ ይልቅ በረሃብተኞች ህይወት ቁማር እየተጫወቱ መሆናቸው እየተጋለጠ ነው ተብሏል
ከሀገር ውስጥ በስውር የወጣ ገንዘብ በቻይና አውሮፕላን ጣቢያ ተገኘ፡፡
 በወያኔ ቁንጮዎች እየተዘረፈ ያለው የሀገር ገንዘብና ንብረት ወደ አሜሪካን ዶላር እየተቀየረ ከአገር ውስጥ እየወጣና በዓለም ዙሪያ እንዲህ ያለ ገንዘብ በአደራ የሚያስቀምጡ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀመጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፈው ሰሞን በደቡባዊ ቻይና ጉዋንግዡ ክፍለ ሀገር ቦዩን በተባለ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ 370 ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የወረቀት ከረጢት ውስጥ በሁለት ቻይናውያን መገኘቱን ቻይና ዴይሊ የተባለ ተቋም ካሰራጨው መረዳት ተችሏል፡፡ የገንዘቡ ባለቤቶች ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ ቱርሲቶች ተብለው ተገልጸዋል ። ይህን ያህል ዶአል ይዞ የሚጓዝ የኢትዮጵያ ሀገር ጎብኚ ማነው ? ባለገንዘቦቹ ወያኔዎች መሆናቸው ከቶም አያጠራጥርም ያሉ ታዛቢዎች የኢትዮጵያ ገንዘብ በወያኔ በየአቅጣቻው እየተጓዘና በየባንኩ እየተቀመጠ መሆኑ ምስጢር አይደለም ብለዋል ።
የመምህራንን ብሶት ለማቀዝቀዝ የቤት ኪራይ አበል ክፍያ ላይ ጭማሪ ሊደረግ እንደሆነ ተሰማ፡፡

የወያኔ ስርዐት በከፋ መልኩ እያጠቃቸው ከሚገኙ የህብተሰብ ክፍሎች ከመጀመሪያ ተርታ የሚሰለፉት መምህራን ናቸው፡፡ የመምህራን ደሞዝ እንኳ አጠቃላይ የኑሮ ወጮዎችን ሊሸፍን ቀርቶ በቀን አንዴ ለሚሆን የምግብ ወጪ ከመሸፈን እንደማልፍ እራሳቸው መምህራኑ በቁጫት ያስረዳሉ፡፡ ይህ ማለት የመምህራን ደሞዝ ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮም እጅግ የወረደ መሆኑ ነው፡፡ መምህራን በተለያዩ አጋጣሚዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ለወያኔ ሹማምንት በተናጠል ጥያቄ ቢያቀርቡም ወያኔ ጆሮ ዳባ ልበስ ምላሽ ከመስጠት ባለፈ እስከ ዛሬ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጭማሬዎች ሁሉ ከይስሙላነት የሚያልፉ አልሆኑም፡፡ የደሞዝ ጭማሪ ጭምጭምታ በተሰማ ቁጥር የቤት ኪራይ ከሃያ ከመቶ በላይ ይጨምራል፡፡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች እንደ ተማሪዎች በስፋትና በተደጋጋሚ ባይከሰትም በጠኔ የሚወድቁ መምህራን ታይተዋል፡፡ ወያኔ ትምህርትን ሲገድል አብሮ መምህራንን እየገደለ መሆኑን የሚያስረዱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህንን የተረዱ የወያኔ አጋሮች የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅትና የመሳሰሉት ትምህርትን መደጎሚያ ካዋሉት ገንዘብ ውስጥ ለመምህራን ከሦስት መቶ እስከ ሦስት መቶ ሃምሳ ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ይከፈል የነበረውን በእጥፍ ለመጨመር መታቀዱ ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚያስተምሩ
መምህራን እንደሆነ የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ ወያኔ ለመምህራን ከመደበኛ ደሞዛቸው ውጪ የቤት ኪራይ ድጎማ የሚለውን አንድ ሺ ብር ቢያደርሰውም ስም እንጂ የመምህራንን ኑሮ ኢምንት እንደማይደጉም ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡
የውጭ አገር ዜናዎች
 ቅዳሜ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም በደቡብ አሜሪካ ግዛት በኢኩዌደር ውስጥ የኃይሉ መጠን 7.2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በመከሰቱ 77 ሰዎች ሲሞቱ ከ500 በላይ የሆኑ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት በኢኩዌደር ይህን ያህል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲደርስ ይኸኛው የመጀመሪያው ሲሆን በመሬት መንቀጥቀጡ ዋና ከተማዋን ኩዌቶን ጨምሮ ምእራባዊ የባህር ዳርቻ ያሉ ኣካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዋና ከተማዋ በርካታ የመኖሪያ ህንጻዎችን የተደረመሱ ሲሆን መንገዶችና ድልድዮች ፈራርሰዋል፤ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተበጣጥሰዋል። በጣሊያን አገር የሚያደርጉትን ጉብኝት አቋርጠው ወደ አገራቸው እየተመለሱ ያሉት የኢኩዌደር ፕሬዚዳንት በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል። ፍርሃትና ስጋት በከፍተኛ ደረጃ በመስፈኑ ምክንያት አለመረጋጋት በመኖሩና በአንዳንድ ቦታዎችም ዝርፊያዎች በመካሄዳቸው ምክንያት መንግስት የተቻለውን እንደሚያደርግና መረጋጋት እንዲፈጠር ተማጽነዋል። ከ 10 ሺ በላይ የሚሆኑ ወታደሮችና ከ3000 በላይ ፖሊሶች በእርዳታ ተግባር እንዲሰማሩ ወደ ቦታው ተልከዋል።
 ከፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዶ በምትገኘው ጃፓን ደግሞ በዚ ሳምንት ሁለት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሷል። በመሀሙስ ሚያዚያ 6 ቀን በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመታውና ገና በማገገም ላይ የነበረው የደቡብ ጃፓን ግዛት ነዋሪ ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. መጠኑ 7.3 በሆኑ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመቷል። በሁለቱም ቀናት በደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች 41 ሰዎች መሞታቸውና በመቶ የሚቆጠሩ መቁሰላቸው ተዘግቧል። በርካታ ህንጻዎች በመድርመሳቸው ከህንጻዎች ስር ብዙ ሰዎች ከእነህይወታቸው ተቀብረው ይገኛሉ የሚል ስጋት አለ። በአካባቢው የሚገኙትን ፖሊሶችና የእርዳታ ሰጭ ሠራተኞችን ለመርዳት 20 ሺ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተልከዋል። መንገዶች የፈራረሱ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የመሬት መድርመስ የደረሰ መሆኑም ታይቷል። መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ዝናም ይዘንማል የሚል ግምት ስላለም የመሬት መደርመሱ በስፋት ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከ200 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ መሆናቸውም ተነግሯል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ሚያዚያ 6 ቀን ከደረሰው ጠንካራ ሲሆን ያጠቃቸው ክልሎችም ሰፊ እንደሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሆስፒታል አገልግሎት እየተሰጣቸው ሲሆን ከ92 ሺ ሰዎች በላይ ቤታቸው ለቀው በመጠለያ ካምፖች መቆየት ተገደዋል። ሰንዴ በሚባለው ቦታ ላይ የሚገኘው የኑክሊየር ቦታ የመፍረስ አደጋ ያላጋጠመው መሆኑ ተገልጿል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ከአምስት ዓመት በፊት ከደረሰውና ሱናሚ አስነስቶ በተለይ በፉኪሽማ በሚገኘው የኑክሊየር ቦታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚበልጥ መሆኑን አዋቂዎች ይናገራሉ።
 የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ጀንቲሎኒ ለሊቢያ የአንድነት መንግስት የፖሊቲካና የዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ለማድረግ ማክሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ትሪፖሊ ገብተዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግፊትና አስተባባሪነት የተቋቋመው የአንድነት መንግስት በባህር በኩል ትሪፖሊ ከተማ ከገባ ጀምሮ አንድ የአውሮፓ ባለስልጣን በሊቢያ ጉብኝት ሲያደርግ ጀንቲሎኒ የመጀመሪያ መሆናቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአንድነት መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚስተር ፋየዝ ሴራጅ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ አገሮች አዲሱን መንግስት ለመርዳት እና ለማጠናከር ሙሉ በሙሉ የቆረጡ መሆናቸውን ገልጸው ከእሳችው በኋላ በርካታ ባለስልጣኖች ወደሊቢያ በመምጣት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዋናው ቁልፉ አይሲስ እንዳይጠናከርና እንዲወገድ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ኢምባሲዎቻቸውን በትሪፖሊ ሊከፍቱ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እሳቸውንም ተከተሎ ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2008 ዓም. የፈረንሳይ አምባሰደር እንዲሁም የእንግሊዝ እና የስፔን ከፍተኛ የልኡካን ከየሚገኙበት የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቡድን ሊቢያ ገብቶ ከአንድነት መንግስት አባሎች ጋር ተነጋግሯል።
 በሰሜን ናይጄሪያ ቺቦክ ከተባለችው ከተማ 276 የሚሆኑ በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ልጃገረዶች ቦኮ ሃራም በተባለው አሸባሪ ቡድን ተጠልፈው ከተወሰዱ ሁለት ዓመት ያለፋቸውሲሆን ባለፈው ታኅሳስ ወር በተደራዳሪዎች አማካይነት ከቦኮ ሃራም ተገኘ ከሚባለውና ባሰለፍነው ሳምንት የሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ካሳየው የቪዲዮ ቅጅ በርከት ያሉት ልጃገረዶች በህይወት መኖራቸው ታውቋል። ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም ሲ ኤን ኤን ያሳየው ቪዲዮ ተቀረጸ የተባለው ታኅሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በፈረጆቹ የገና በዓል ዕለት ሲሆን ከተጠለፉት ልጃገረዶች መካከል 15 ቱ በቪዲዮ ላይ ታይተዋል። ቪዲዮን የተመለከቱት አንዳንድ እናቶችና በዚያን ወቅት ያመለጡና ጓደኞቻችው የተመሰቃቀለ ስሜት ያደረባቸው መሆኑንና በአንድ በኩል ልጆቹ በህይወት መኖራቸው ሲያስደስታቸው በሌላ በኩል ያሉበት ሁኔታ በጣም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ቦኮ ሃራም የተባለው አሸባሪ ድርጅት ለዓመታት ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የቆየ ቢሆንም ልጃገረዶችን በጅምላ ጠልፎ ሲወስድ በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት የደረሰበት መሆኑ ይታወሳል፡፤ በወቅቱ የነበረው የናይጄሪው የሚስተር ጉድላክ ጆናታን መንግስት በመጀመሪያ ልጃገረዶቹ መጠለፋቸውን ቢክድም በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ግፊት ለመቀበል ተገዷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ልጆቹን ለማስፈታት በድርድርም ሆነ በሌላ መልክ ጥረት ቢደረግም እስካሁን የተገኘ መፍትሄ እንደሌለ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራም ከሚቆጣጠራቸው ቦታዎች 11698 ሰላማዊ ሰዎችን ነጻ ማውጣቱን ቢገልጽም ነጻ ወጡ የተባሉት ሰዎች ከቺቦክ የተያዙ ልጃገረዶችን አያካትቱም። ላለፉት ሁለት ዓመታት በቺቦክና በአካባቢው ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት ከ20 ሺ በላይ ህጻናት የትምህርት ዕድል ተነፍገው ይገኛሉ።
በዚህ ሳምንት በዚምባዌ በደቡብ አፍሪካ እና በግብጽ ህዝባዊ የተቃውሞ ስልፎች ተደረገዋል። ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ዚምባብዌ ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲ የተደራጀና የተቀነባበረ ከፍተኛ ተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ መሆኑ ታውቋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንቱ ሚስተር ሙጋቢ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ መፈክሮችን ይዘው የነበረ ሲሆን በርካታ ሴቶችና ወጣቶች እንደነብሩበት ለማወቅ ተችሏል። ስልፉን ቀደም ብሎ የጸጥታ ኃይሎች ከልክለው የነበረ ቢሆንም ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም የዚምባብዌ ፍርድ ቤት የፖሊስ እገዳ እንዲነሳ ትእዛዝ በመስጠቱ ምክንያት ሰልፉ ሊካሄድ ችሏል። ሙጋቤ የሚመሩት የዚምባብዌ ገዥ ፓርቲ አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ ተቃዋሚዎችን የሚጠይቁትን ጥያቄ አውግዞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ትክክለኛው መንገድ ምርጫ ነው ብሏል። ከሶስት አመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሚስተር ሙጋቤ በድጋሚ የተመረጡ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በወቅቱ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የምዕራብ አገሮች ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አይደለም በማለት ድምጽ ማሰማታቸው ይታወሳል።
አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በጆሃንዝበርግ ከተማ ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ትእይንተ ህዝብ ያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል። ሰላማዊ ሰልፉና ያዘጋጁት የተቃዋሚ ድርጅቶች ሲሆኑ ሰልፈኞቹ ” ሙስና ይቁም” ” ለለውጥ ድምጻችንን እንሰጥ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው እንደነበር ማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቱ ለገጠር ቤታቸው ማስፋፊያ በርካታ የመንግስት ገንዘብ መውሰዳቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጾ ገንዘቡን እንዲመልሱ መወሰኑ ይታወሳል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዋቂ ግለሰቦችና የሃይማኖት ድርጅቶች
መሪዎች ሚስተር ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ከገዥው ፓርቲ አባላት በኩል ያላቸው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ በምክር ቤት ውስጥ እሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ የቀረበው ሕዝበ ውሳኔ ውድቅ መሆኑ ይታወቃል።
እንዲሁም አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ የፕሬዚዳንት ሲሲን አስተዳደር በመቃወም ቁጥራቸው ከ 1000 በላይ የሚሆኑ ግብጻውያን የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ሰልፉ የተጠራው ቀደም ብሎ ሁለት የግብጽ ደሴቶች ለሳኡዲ አረቢያ መሰጣቸውን ለመቃወም ቢሆንም ሰልፈኞች ያሰሙ በነበረው መፈክር ውስጥ የሲሲ መንግስት የሚያወግዙና ሲሲ ባስቸኳይ ከስልጣን እንዲወገዱ የሚጠይቁ እንደሚገኙበት ታውቋል። ስልፉ እስከምሽት ድረስ የቆየ ሲሆን አብዛኛው ሰልፈኛ ከሄደ በኋላ የቀሩትን ጥቂት ሰዎች ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ የተጠቀመ መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ብሎ በሌላው የከተማው ክፍል የተደረገውን ስልፍ ለመበተን ፖሊስ እርምጃ የወሰደ ሲሆን 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውም ተዘግቧል።
 የምእራብ ሳህራ ግዛትን አስመልክቶ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በሞሮኮ መንግስት ላይ ተገቢውን ተጽእኖ ማድረግ ካልቻሉ ሞሮኮ በምእራብ ሳህራ ሕዝብ ላይ የምትፈጸመው አፈናና በደል ሊፋፋም እንደሚችል የፖሊሳሪዮ ግምባር መሪ ሚስተር ሞሃመድ አብዱላዚ በዚህ ሳምንት አስታውቀዋል። በሕዝብ ላይ የሚካሄድ አፈናና በደል የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ ይህን ለመቋቋም ከትጥቅ ትግልን ጀምሮ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንገደዳለን በማለት ጦርነት እንደገና ሊጀመር የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁመዋል። ማስጠንቂቂያው የተሰጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በምእራብ ሳህራ ስለሚገኘው የተመድ ተል እኮ የወደፊት እጣ እየመከረ ባለበት ወቅት ነው። ባለፈው ወር ሞሮኮ በተመድ ዋና ጸሐፊ መግለጫ በመቆጣት ከአገሩዋ ዲፕሎማቶችን ማስወጣቷ ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት ከ1983 ዓም የምእራብ ሳህራን ጉዳይ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ጥረቱ እስካሁን ጥረቱ ያልተሳካ መሆኑ ይታወቃል። የአገሪቱን የወደፊት እጣ ለመወሰን ውሳኔ ሕዝብ ይደረግ ቢባልም በፖሊሳርዩ ግምባርና በሞሮኮ መካከል በጉዳዩ ላይ ልዩነት በመፈጠሩ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል። ግዛቱ የሞሮኮ ነው የሚለውን ሀሳብ ፈረንሳይና ሴኒጋል የሚደግፉት ሲሆን ሌሎች የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የሚቃወሙት መሆኑ ይታወቃል።
 ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ሱዳን ሁለት የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሠራተኞች በታጣቂ ኃይሎች የተገደሉ መሆናቸው ተገድለዋል። ዳኒሽ ዲማይኒንግ ግሩፕ (Dannish Demining Group) ለሚባለው የቦምብ አምካኝ የሰብአዊ መብት ድርጅት ይሰሩ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የደቡብ ሱዳን ዜጎች ሲሆኑ ወደስራ ከሚሄዱበት መኪና በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተገድደው በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆናቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በደቡብ ሱዳን በታጣቂዎች የተገደሉ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች አባላት 51 የደረሰ ሲሆን ግጭቱ እስከቀጠለ ድረስ ቁጥሩ ሊቀጥል እንደሚችል ተገምቷል፡፡
 በተያያዘ ዜና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ኃይል ምክትል መሪ ሚስተር አልፍሬድ ላዱ ጎሬ በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የገቡ መሆናቸው ተነግሯል። በተደረገው ስምምነት መሰረት የጸጥታውን ሁኔታ የሚያስከብር 1300 የሚሆኑ የአማጽያኑ ኃይል ወታደሮችና የጸጥታ ኃይሎች ቀደም ብለው ጁባ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ዋና መሪ ሚስተር ሪክ ማቻርም በሚቀጥለው ሰኞ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክትል መሪው ጁባ መግባት በእርግጥም በአገሪቱ ላይ ሰላም እየሰፈነ ነው የሚለውን ግምት ከፍ አድርጎታል ተብሏል። ሚስተር ጎሬ ጁባ ሲገቡ በተናገሩት ቃል ከእንግዲህ ሰላም አይቀለበስም የሚል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን 16 የአማጽያኑ ኃይል አባላት በመንግስት ኃይሎች መታሰራቸውንና ተደብድበው መለቀቃቸውን አውግዘዋል። ከዚህ ሌላ አንድ የአፍሪካ ህብረት የመልክተኛ ቡድን በደቡብ ሱዳን የአንድነቱን የሽግግር መንግስት ለማጠናከር ጁባ የገባ መሆኑ ተገልጿል

No comments:

Post a Comment