Thursday, April 14, 2016

መንግስት በረኃቡ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከሰስ ይችላል


  


ምግብ የመብት ጉዳይ ነው። መንግስት በረኃቡ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከሰስ ይችላል። የዩንቨርስቲ ተማሪዎች፣የከተማ ነዋሪዎች እና ገበሬዎች ሁሉ ለተራበው ሕዝብ መጮህ ካለባቸው ወቅቱ አሁን ነው! (የጉዳያችን ማስታወሻ)

የተባበሩት መንግሥታት የምግብ መብት ጉባኤ (Photo:- srfood.org)
የተባበሩት መንግሥታት የምግብ መብት ጉባኤ (Photo:- srfood.org)
እንደ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ዘገባ በኢትዮጵያከሚኖረው ሕዝብ ከአምስቱ አንዱ ርኃብ አደጋ ላይ ነው። ዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት – ዩኒሴፍም ዘገባውን ስያጠናከር በኢትዮጵያ የስድስት ሚልዮን ሕፃናት ሕይወት አደጋ ላይ ነው ብሏል።በሌላ በኩል በከተማ የሚኖረው ሕዝብ የኑሮ ውድነቱጣርያ ነክቶበታል።የብሔራዊ ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው የዋጋግሽበቱ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 12% ደርሷል።ዓለም አቀፍየረድኤት ድርጅቶች የ90 ቀናት የእርዳታ ማሰባሰብያ መርሃ ግብርአዘጋጅተዋል።በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን በይፋእንዳይጠይቁ ታግደዋል። (Ethiopian government stops fundraising campaign by UN agencies)
ይህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ወንጀልም ነው።ምግብ ከመኖር ህልውናበላይ የሰብአዊ መብት ጉዳይም ነው። መንግሥታት፣ግለሰቦች እናኩባንያዎች ሰዎች ምግብ እንዳያገኙ ለሚያደርጉት ማናቸውም እንቅስቃሴ እና ኃላፊነት ያለመወጣት ተግባር ሁሉ በሕግእንዲጠየቁ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጥቂትአመታት ተቆጥረዋል።
ምግብ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው (Right to food) የሚለውንመመርያ በአገራቸው ለተግባራዊነቱ ሥራ ከሚሰሩት አገራትውስጥ ኤልሳ ልቫዶር፣ዮርዳኖስ እና ህንድ  ይገኙበታል።የምግብ መብት ዓለም አቀፍ ሕግ የማድረግ እንቅስቃሴ የመነጨው ከተባበሩት መንግስታት የምጣኔ ሀብት፣የማኅበራዊ እና የባሕል መብት ፅንሰ ሃሳብ ሲሆን እኤአቆጣጠር በ2012 ዓም 160 አገራት ጉዳዩን ከፍ ወዳለ ዓለም አቀፍ ሕግ ቅረፃ ለማሳደግ የመግባብያ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።የመግባብያ ሰነዱ አገራቱ ምግብ የመብት ጉዳይ መሆኑን የሚያሳይ ፖሊሲ በአገራቸው እንዲያወጡ እና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተግባራዊ እንዲሆን ያሳስባል።
በእዚህም መሰረት በ20013 እኤአ ህንድ የምግብ መብት ሕግን በብሔራዊ ሕግ ውስጥ አካተተች።ምግብ የመራብ እና አለመራብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መንግሥታት ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግዴታቸውን የመወጣታቸው እና ያለመወጣታቸው ጉዳይም ጭምርም ነው።ለአንድ ሕዝብ ምግብ እንዳይደርሰው ማድረግ ከዘር ማጥፋት ወንጀል እኩል ያስጠይቃል።የምግብ ጉዳይ የኢትዮጵያቴሌቭዥን ሲመቸው ስለረሃብ ሳይመቸው ዘፈን የሚያቀርብበት ጉዳይ አይደለም።በኢትዮጵያ የሰው መብት ከሚታሰበው እና ከሚገመተው በላይ በአምባገነኑ ስርዓት ስለተረገጠ ጉዳዩን አቅልሎ የማየት አዝማምያ ይስተዋላል።ሆኖም ግን ጉዳዩ ቀላል ጉዳይ አይደለም። የሚወራው ስለ ሚልዮኖች ሕይወት ነው።የተራበው የኖርዌይን ሕዝብ ሶስት እጥፍ የሚሆን ሕዝብ ነው።ይህ ሕዝብ እንደ ምንም ነገር ዝም ሊባል አይገባም።
የምግብ መብት ጉዳይ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ በአገራት የውስጥ ፖሊሲከመግባት ባለፈ መንግሥታት ፍርድ ቤት አስቁሞ አስፈርዷል።በኔፓል1998 የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መንግስቱን ምግብ ለሕዝቡባለማዳረሱ ምግብ እንዲያከፋፍል ፈርዶበታል።በህንድም በተመሳሳይመልክ የእርዳታ ድርጅቶች ተሰብስበው የህንድን መንግስት  ለሕዝቡ  ምግብባለማድረሱ  የሚል ክስ መስርተው አስፈርደውበታል።
በመጨርሻም  ምግብ ለሕዝብ እንዳይደርስ የማድረግ ሂደት ከቢሮክራሲያዊድክመት ባለፈ በአገር ውስጥ የሚፈጥረው የውስጥ ቅራኔ ቀላልአይደለም።በአሁኗ በህወሓት የጎሳ ፖለቲካ የተከፋፈለች ኢትዮጵያውስጥ ምግብ እንዳይደርስ የተደረገው አካባቢ ከጎሳ ጭቆና አንፃርሊመለከተው ስለሚችል ጉዳዩ ውስብስብ ችግር ይዞ መምጣቱአይቀርም።በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት እየደበቀ ያለውን ርኃብበግልፅ በአደባባይ በመቃወም የተሻለ ብሔራዊ መግባባት እና አንድነትመፍጠር ይችላል።የተራበው አካባቢ ሕዝብ በርቀት የሚኖረው ወገኑእንደሚያስብለት የማሳያው እና ሌላው አንድነትየመፍጠርያ አጋጣሚም ነው።ስለተራበው ሕዝብ የዩንቨርስቲተማሪዎች፣ምሁራን፣የከተማ ነዋሪዎች እና ገበሬዎች ሁሉ መጮህካለባቸው ወቅቱ አሁን ነው።ሚልዮኖች ከመርገፋቸው በፊት ለኢትዮጵያሕዝብ እንድረስለት።
ጉዳያችን Gudayachn

No comments:

Post a Comment