(ዘ-ሐበሻ) በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሥር ባለችው ዘንዘልማ ከተማ አካባቢ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::
ይህ ከባድ አደጋ የደረሰው ከባህርዳር ወደ ወረታ በሚጓዝ ሚኒባስ እና ከጎንደር ወደ ባህርዳር በሚጓዝ አይዙ መኪናዎች በመጋጨታቸው ነው:: ለአደጋው መንስ ኤም የአይሱዙው መኪና ሹፌር በፍጥነት በማሽከርከሩና መንገድ ጥሶ ሚኒባሱ ላይ በመግባቱ ነው ተብሏል::
በዚህ ከባድ የመኪና አደጋ ላይ የ2 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን የሚጠቁሙት ምንጮች 6 ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ:: በተጨማሪም ሌሎች ከ6 የማያንሱ ሰዎችም እንዲሁ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል::
I every time used to read article in news papers but now as I am a user of
ReplyDeletenet thus from now I am using net for articles, thanks to web. rental mobil bogor